የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ማሻሻያ !
የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በድሬደዋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። መርሃ ግብሩን እስከ 13ኛ ሳምንት በድሬደዋ ለማካሄድ ፕሮግራም ቢወጣም በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ላለበት የቻን የማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅት ምክንያት ሊጉ ከ11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በኋላ ይቋረጣል። ነገር ግን የአንደኛ ሳምንት ተስተካካይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ የፊታችን እሁድ ታህሳስ 06/2017 በድሬዳዋ ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል።
ከ12ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ጀምሮ ያለውን የ2017 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዳማ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ሲሆን ከታህሳስ 25/2017 በኋላ ያለውን መርሃ ግብር በቀጣይ ቀናት የምናሳውቅ ይሆናል።
©️የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ