Hawassa's Memory-የሐዋሳ ትዝታ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Транспорт


ሐዋሳ የፍቅር ሐገር! መልካም ገፅታዋን ለማስጠበቅ የትም የሚኖር፣ ሐዋሳ የተወለደ፣ ያደገ፣ ለስራ ወይም ለመዝናናት የመጣ እንዲሁም ለሚያውቃትና ሊያውቃት ለሚፈልግ ትዝታውን በፍቅር ይለዋወጣል

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Транспорт
Статистика
Фильтр публикаций


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram






#የድረሱልኝ_ጥሪ| በIC ውስጥ ነች
#hawassa| አባይነሽ ዳጊሶ
    አባቴን ለማሳከም አዳሬ በነበርኩበት ጊዜ አግኝቻት ነበር። ደህና ነኝ ብላኝ ተጨዋውተን ተለያየን። በተለያየ ጊዜ በቺሻየር በሚካሄዱ መርሐግብሮች ከሰራተኝነት እስከ በጎ ተግባሮቿ ቅን አመለካከቷ ያላት ስብዕና ያስደንቃል። ዛሬ ግን በከፍተኛ ሁኔታ ታማ ICU ገብታ በጭንቅ ውስጥ እንዳለች እናታችን ላቀች እና የስራ ባልደረቦቿ መልዕክቱ ደረሰኝ።
    ቤተሰቦቿ፣ እንዲሁም ለነገ ብላ የቆጠበቅውን በህክምና ወጭ ጨርሳለች። በጓደኞቿና በስራ ባልደረቦቿ ድጋፍ ዛሬ ድረስ ለመቆየት ችላለች። ይሁን እንጅ የህክምና ወጭው ከሷና ከቤተሰቦቿ አቅም ያለፈ ሆነና እነሆ የኛን ድጋፍ ፍለጋ መጥታለች። በፈጣሪ ስም እርዱኝ እኔም ጤናዬ ተመልሶ ለመርዳት ያብቃኝ እያለችን ነው። ፈጣሪ ይጠብቅልን። እባካችሁ እንርዳት።

1000019993322 Lakech Adugna የቴሻየር ኢትዮጵያ የስራ ባልደረባ ከሆኑት መካከል በወ/ሮ ላቀች አዱኛ ስም ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ 🙏


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
Solon blind school






የቸ ሻየር ኢትዮጵያ ሀዋሳ ቢሮ ለጉዳተኞች መቆያ የሚሆኑ የመኝታ ክፍሎችን አስመረቀ።

👉አካል ጉዳተኞችና ቤተሰቦቻቸው
ሰው ሰራሽ የአካል ድጋፍ እንዲሰራላቸው ከሀዋሳ ውጭ ሲመጡ ሂደቱ እስከ 15 ቀን የሚያቆይ በመሆኑ ለተጨማሪ ወጪ እና እንግልት ይዳረጉ ነበር። ይህንን ከግንዛቤ በማስገባት ነው እንግዲህ የእነዚህ ማረፊያ ቤቶች መገንባት የታሰበው ። በእዚህም መሠረት ከለጋሽ ድርጅቶችና ከሀገር ውስጥ በተገኘ ሀብት ዛሬ የተመረቀው ቤት እውን ሊሆን ችሏል።
በበዚህም አለም አቀፍ ቀይ መስቀል ድርጅት እና ከኮንቴይነር ድጋፍ ጀምሮ አልጋ፣ ፍራሽ፣ አንሶላና ብርድልብስ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን በማሟላት
ሀዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ
ታቦር ሴራሚክ
ኤሎናይ የጉዞ ወኪል
መንግስቱ ፈርኒቸር
ሴንተር እፍ ኮንሰርን
ሞዳኖቫ ጨርቃ ጨርቅ
ዘሪሁን ጨርቃ ጨርቅ
ሀያት የመድሃኒት አከፋፋይ እና ሌሎችም የድጋፍ ተባባሪዎች ነበሩ።
👉አቶ ፋሲል አየለ የቸ ሻየር ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር
👉አቶ ሀጂ የአለም ቀይ መስቀል ማህበር ተወካይ
👉ዶ.ር ግርማ አባቢ የሊያና -ያኔት ጤና ማዕከል ባለቤት እና የቸ ሻየር ኢትዮጵያ የቦርድ ሰብሳቢ
👉አቶ መሠረት ኪዳኔ የቸ ሻየር ኢትዮጵያ የአማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ እና
👉የሀዋሳ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳግም ጌታሁን
👉አቶ ባንታየሁ ቀፀላ የሲዳማ ክልል ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ተወካይ
የታየውን ትብብር በማድነቅ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን በአካል ጉዳት ውስጥ የሚገኘውን ህብረተሰብ ይበልጥ ለመድረስና ለማገዝ አሁንም ከማህበረሰቡ ጋር በቅርበት መሰራት እንዳለበት አስምረዋል።
አካል ጉዳተኝነት ለጉዳተኛው ህይወቱ፡ ለጉዳት አልባው ስጋቱ መሆኑን ልብ ይሏል!










#የዝክረ_ደራ| የመዝግያ መርሐግብር
#hawassa| ነገ በ10 ሰዓት በሴንትራል ሆቴል
  በቅድሚያ ለዛሬው ቀን ላደረሰን ፈጣሪ ምስጋና እያቀረብን በዝክረ ደራ (በመኪና አደጋ ላጣናቸው ወንድሞቻችን ቤተሰቦች ማቋቋሚያና ቀላልና ከባድ ጉዳት ለደረሰባቸው ህክምና ወጭ በሐገር ውስጥና በውጭ ሐገር ኮሚቴ ተቋቁም የገቢ ማሰባሰብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ መደረጉ ይታወቃል። በዚህም እናንተ ከማፅናናት ባለፈ ላሳያችሁን ቤተሰባዊ ፍቅርና ላደረጋችሁት የገንዘብ ድጋፍ አክብሮታችንን ለመግለፅ እንወዳለን። ለሟቾችም ነብስ ይማር ለቤተሰብ መፅናናትን፣ ለቆሰሉት መሻርን ያድልልን ዘንድ እንመኛለን።
      በመሆኑም ዝክረ ደራ የገቢ አሰባሰብ ኮሚቴ ያከናወናቸውን ተግባራትና ሌሎች አጠቃላይ ሂደት ለናንተ ለማቅረብ የመዝጊያ ፕሮግራሙን የፊታችን አርብ በሴንትራል ሆቴል በ10:00 ሰዓት ያከናውናል። በእለቱ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የሐይማኖት መሪዎች፣ የሟች ቤተሰቦች፣ በፈጣሪ ፍቃድ ከአደጋው  የተረፉ ወንድሞች፣ የደራ ዘይት ጤና ስፖርት አባላት፣ ወዳጅ ዘመድ በተገኘበት ይከናወናል።
     ኮሚቴው ሁላችሁንም በሴንትራል ሆቴል በ10 ሰዓት እንድትገኙ ጥሪውን ያቀርባል።
የዝክረ ደራ አስተባባሪ ኮሚቴ
01/9/2016
ሐዋሳ




በመጨረሻም ከተማችንን ስላገለገሉ እናመሰግናለን አልናቸው፡፡ እርሳቸውም አይ ለራሴ ጥቅም ሰራሁ እንጂ ህዝብን መች አገለገልኩ ብለሽ ነው አሉኝ፡፡ ያኔ ትዝ ይለኛል በአብዛኛዎቻችን ቤት የቡታጋዝ ተጠቃሚ በነበርንበት ጊዜ ከ1 ሌትር ጀምሮ ነጭ ጋዝ ይሸጡ ነበር፡፡ እሳቸው በአቅራቢያው ለዝቅተኛው ማሕበረሰብ ባያቀርቡ ከየት እንጠቀም ነበር? ብቻ ብዙ የሰሩ ሰዎች ብዙ ማውራት አይፈልጉም፡፡ ለእሳቸውም ለሚወዷቸው ባለቤታቸው እዲሁም በአጠቃላይ ለቤተሰቦቻቸው መልካም ምኞታችንን ተመኝተን ከእሳቸውም ከወይንዬም ምርቃትን ተቀብለን ለቀጣይ ሳምንት ጋቢ ለምናለብሰው አባት ቤት መንገጃችንን አቀናን፡፡ መልካም ዕለተሰንበት!

ሊዲያ /የሚኬ ባለቤት/ ስለቅንነትሽና ስለመልካም ትብብርሽ ሳላመሰግንሽ ማለፍ ንፉግነት ነው፡፡ ነፍፍፍፍፍ አመት ኑሪልኝ እህቴ፡፡

ምስጋና፡ ለፍቅሩና ጓደኞቹ እንዲሁም ለዶ/ር ዘነበ (አልፋኬር መካከለኛ ክሊኒክ) Zenebe Mekonnen

በሐና በቀለ
*
የፍቅር የሰላምና የአንድነት አርበኞች!

Показано 17 последних публикаций.

185

подписчиков
Статистика канала
Популярное в канале