🍀ድንግል_ማርያም_የውርስ_ኃጢያት_ይመለከታታልን ?
ክፍል ሦስት
ከዚህ ቀደም ተከታታይ ባቀረብናቸው ጽሑፎች #ወላዲተ_አምላክ_ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት እንደማይመለከታት ከብዙ በጥቂቱ ለማየት ሞክረናል።በክፍል ሁለት ጽሑፋችን #ወለደት_ድንግል_ዘፀንሰቶ_እንዘ_ኢተአምር_ብእሴ_በሥጋ_ዘፈጠሮ_ለርእሱ_ወወለደቶ_ዘእንበለ_ደነስ_ወሕማም_ወኢረሰስሐት_በሐሪስ_ሐፀነቶ_ዘእንበለ_ፃማ_ወድካም_ወአጥበቶ_ዘእንበለ_ድካም_ወአልሐቀቶ_በሕግ_ዘሥጋ_ዘእንበለ_ትካዝ ።ሃይማኖተ አበው ዘአትናቴዎስ 28፥19
••●◉ ✞ ◉●••
#ለተዋሕዶ_የፈጠረውን_ሥጋ_ያለ_ወንድ_ዘር_ያለ_ኃጢአት_ያለምጥ_ወለደችው_የአራስነት_ግብርም_አላገኛትም_ያድካም_ያለመታከት_አሳደገችው_ያለድካም_አጠባችው_ለሥጋ_በሚገባ_ሕግ_ምን_አበላው_ምን_አለብሰው_ሳትል_አሳደገችው። ሃይማኖተ አበው ዘአትናትዮስ 28፥19 ትርጉም ማብራሪያውን በቀጣዩ ጽሁፋችን እንመለከታለን ብለን ነበር ያቆምነው።
👉ሐዋርያዊው ቅዱስ አትናቴዎስ ካስተማረው ትምህርት እመቤታችን የጥንተ አብሶ ፍዳ እንደማይመለከታት በሚገባ ማስተዋል ይቻላል ግልጽ ለማድረግም የሚከተሉትን ነጥቦች መመልከት ይቻላል፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
👉፩. ያለ ኃጢአት ከሚለው ቃል ወላዲተ አምላክ ጌታን ምንም ምን ኃጢአት ሳያገኛት እንደወለደችው ያስረዳናል
••●◉ ✞ ◉●••
፪. ያለምጥ የአራስነት ግብርም ሳያገኛት ከሚለው ደግሞ ሌሎች ሴቶች በጥንተ አብሶ ፍዳ ምክንያት በምጥ በአራስነት የሚወልዱ ሲሆን እርሷ ግን ከመርገመ ከእዳ ከበደል የተለየች በመሆኗ ምጥና አራስነት አልነበረባትም ይህም ከመልአኩ የምስጋና ንግግር ተስማሚነት ያለው ነው #ቅዱስ ገብርኤል ሲያበሥራት ከላይ ከተጠቀሱት የመርገም ምልክቶች እመቤታችን የተለየች መሆኗን ሲያስረዳ #አንች_ከሴቶች_መካከል_የተባረክሽ_ነሽ ሉቃ 1፥28 በማለት አመሰግኖአታል።ለመሆኑ እርሷ በሌሎች ሴቶች ያለ የመርገም ፍዳ ካለባት ከሌሎች ሴቶች መለየቷ ምን ላይ ሊሆን ነው ❓ ስለዚህ እመቤታችን የመርገም ፍዳ ይመለከታታል ብሎ ማስተማር ፍጹም ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮ የራቀ ትምህርት ነው ማለት ነው ። ወላዲተ አምላክ የጥንተ አብሶ ፍዳ እንደማይመለከታት ቅዱስ አትናቴዎስ ብቻ ሳይሆን በርካታ ቅዱሳን አበውም መስከረዋል
👉ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ #ድንግል_ማርያም የጥንተ አብሶ ፍዳ እንደማይመለከታት ሲያስረዳ በሚደንቅ ንግግር እንዲህ ይላል #ከመገባሪ_ጠቢብ_ሶበ_ይረክብ_ግብሮ_ዘይትጌበር_ይገብር_እምኔሁ_ንዋየ_ሰናየ_ከመዝ_እግዚእነ_ሶበ_ረከበ_ሥጋሃ_ቅዱስ_ለዛቲ_ድንግል_ወነፍሳ_ቅድስት_ፈጠረ_ሎቱ_መቅደስ_ዘቦቱ_ነፍስ » ሐይ አበ ዘአፈወርቅ 66 ፡14
••●◉ ✞ ◉●••
#ጥበበኛ_ንጹሕ_አፈር_ባገኘ_ጊዜ_ጥሩ_እቃ_እንደሚሰራበት_ጌታችንም_የድንግልን_ንጹሕ_ሥጋዋን_ንጹሕ_ነፍሷን_ባገኘ_ጊዜ_ይዋሐደው_ዘንድ_ነፍስ_ያለውን_መቅደስ_ሰውነቱን_ፈጠረ
••●◉ ✞ ◉●••
👉መቼም የቀናች የተረዳች ርትዕት የሆነች የተዋሕዶ ምዕመን ሆኖ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን የማያውቅ አለ ማለት ይከብዳል ምንም በማያሻማና ግሩም በሆነ አገላለጽ ሊቁ እነዳስቀመጠልን አምላክ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው የሆነው ምንም ምን እንከን ከሌለው ሰውነቷ ነው ሊቁ #የእመቤታችንን ነፍስና ሥጋዋን በንጹሕ አፈር መስሎታል በዚህ አገላለጹ ከሰው ወገን ተመርጣ #የለጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ እናትነት የበቃች መሆኗን አስረዳን ምክንያቱም የሰው ሁሉ ተፈጥሮው ከአፈር ነውና ። #ወላዲተ_አምላክ እንደሰው ሁሉ ተፈጥሮዋ ከአፈር ቢሆንም ቅሉ ሊቁ እንደተናገረው ንጹሕ አፈር የሚለው አገላለጽ በሰዎች ከደረሰ አዳማዊ መርገም የተለየች መሆኗን ያስረዳናል
👉ቅዱስ ኤፍሬምም በማክሰኞ ውዳሴ ማርያም #ዘር_ያልተዘራባት_እርሻ በማለት በንጹሕ እርሻ መስሎአታል
👉ልበ አምላክ ዳዊትም #እንደ_ዝናብ_በንጹሕ_እርሻ_ላይ....ይወርዳል መዝ 71፥6 በማለት #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን በዝናበ ሕይወት እመቤታችንን ደግሞ አረም ተዋስያን በሌሉት ንጹሕ መሬት መስሎ ትንቢት ተናግሮአል ይህም ምንም ተፈጥሮዋ ከሰው ወገን ብትሆንም የኃጢአት አረም ህዋስ ያልነካት ንጽሕት ዘር መሆኗን ያስረዳናል። ለዚህም ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በንጹሕ አፈር የመሰላት ።
••●◉ ✞ ◉●••
👉ሊቁ በመቀጠልም #ንጹሕ_ሥጋዋን_ንጹሕ_ነፍሷን_ባገኘ_ጊዜ በማለት #የወላዲተ አምላክ ነፍሷ ሥጋዋ ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ ንጹሕ ቅዱስ መሆኑን ይመሰክራል ባገኘ ጊዜ አለ እንጂ ሊዋሐደው ሲል አነጻው አላለም ስለዚህም እውነተኞች ቅዱሳን አበው በጥንቃቄ የመሰከሩትን #የእመቤታችንን ንጽሕና ዛሬ ማንም ተነስቶ ሊያስተባብል አይችልም ተቀባይነትም አይኖረውም ።
👉ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረን #እኛ_ብንሆን_ወይም_የሰማይ_መልአክ_ከሰበክንላችሁ_ወንጌል_የሚለይ_ወንጌል_ቢሰብክላችሁ_የተረገመ_ይሁን።ገላ 1፥8 ባለው መሠረት ዛሬ ማንም ተነስቶ ሊሽረው ወይም ሊለውጠው አይችልም። ቢሞክር እንኳን የተለየ የተረገመ ነው።#ቅድስት_ቤተክርስቲያን የምትመራው ቀደምት ቅዱሳን ባስተማሩን እውነተኛ ትምህርት እንጂ አዲስ ዛሬ የሚፈጠር ምንም የለም ስለዚህ ከአንዳንድ የዘመናችን ሰዎች የተሳሳተ ትምህርት ብንሰማ እነሱ የተለዩ ይሆናሉ እንጂ የሰማይ መልአክ ነኝ የሚል ቢመጣ እንኳን የቤተክርስቲያን አስተምሮ አይለወጥም፡፡
++++++++++++++++++++++++++++++
የመጨረሻ ክፍል አራት ይቀጥላል
"እምነትክን እወቅ እንዳቶን መናፍቅ"
++++++++++++++++++++++++++++
የቻናሉ ሊንክ👉@haymanote1
👉@haymanote1