ሂዳያ መልቲሚዲያ | ʜɪᴅᴀʏᴀ ᴍᴜʟᴛɪᴍᴇᴅɪᴀ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


- አንዳንድ ማስታወሻና ምክሮች
- ዳዕዋዎች እና ፈታዋዎች
- ምርጥ ግጥሞች
- አጫጭር የዳዕዋ ቪድዮዎች
- የተለያዩ ደርሶችና ታሪኮች
-ጥያቄና መልስ ፕሮግራሞች የሚጋሩበት የሆነ ቻናል ነው።
Join እና Share በማድረግ አጋርነታችሁን ግለፁ!!
🔘በተጨማሪም የዩቱብ ቻናላችን ይቀላቀሉ!
https://www.youtube.com/@hidaya_multi
🗳ለአስተያየት @annafiabot ይጠቀሙ!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций








📚#የሀዲስ_ትምህርት

📖الحديث التاسع والثلاثون

عن ابن عباس رضي الله عنهما - أن رسول الله ﷺ قال: «إن الله تجاوز لي عن أمتي الخطأ والنسيان وما استكرهوا عليه.» حديث حسن رواه ابن ماجة، والبيهقي في السنن، وغيرهما.

📔ሐዲስ ቁጥር 39

ከኢብኑ ዓባስ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና; የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል; «አላህ ለኔ ከህዝቦቼ ተሳስተው፤ ረስተውና ተገደው የሚሰሩትን ወንጀል ምሮልኛል።»

ሐዲሱ ሀሠን ነው። ኢብኑ ማጃህ: በይሀቂይ ሱነናቸው ላይ: እና ሌሎችም ዘግበውታል።

🖇ከሐዲሱ የምንይዛቸው ቁምነገሮች

📍አላህ ለነቢዩ የዋለውን ውለታ

📍የነቢዩ ኡመት የታዘነለት ኡመት መሆኑን

📍የሰው ልጅ ተሳስቶ፣ ረስቶና ተገድዶ በሚሰራው ነገር እንደማይጠየቅ

📍የአላህ እዝነት ሰፊ መሆኑን


والله أعلم

© ሂዳያ መልቲሚዲያ

🗓 ረቡዕ | ህዳር 2/2017

♡     ⎙ ㅤ ⌲         🔕           📢
ˡⁱᵏᵉ  ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ    ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ    ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ


📚#የሀዲስ_ትምህርት

📖الحديث الثامن والثلاثون

عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول اللهﷺ: إن الله تعلى قال: « من عادى لي وليا فقد آذنته بالحرب، وما تقرب إلي عبدي بشيئ أحب إلي، مما افترضته عليه، ولا يزال عبدي يتقرب إلي بالنوافل حتى أحبه، فإذا أحببته، كنت سمعه الذي يسمع به، وبصره الذي يبصر به، ويده التي يبطش بها، ورجله التي يمشي بها، ولئن سألني لأعطينه، ولئن استعاذني لأعيذنه. »رواه البخاري

📓ሐዲስ ቁጥር 38

አቡ ሁረይራህ እንዲህ ብለዋል; የአላህ መልእክተኛ ﷺእንዲህ ብለዋል; «አላህ እንዲህ ብሏል; ❝የኔን ወዳጅ ጠላት አርጎ የያዘ፥ በሱ ላይ ጦርነትን አውጄበታለሁ፤ ባሪያዬ እኔ ዘንድ የተወደደ በሆነ ባንዳችም ነገር ወደኔ አይቀርብም፥ ግዴታ ያረኩበትን ነገር በመፈፀም ቢሆን እንጂ፤ ባሪያዬ ሱና ዒባዳዎችን በመፈፀም ወደኔ ከመቃረብ አይወገድም፥ እኔ ብወደው እንጂ፤ እኔ ከወደድኩት፥ መስሚያ ጆሮው፤ የሚያይበት አይኑ፤ የሚሰራበት እጁ፤ የሚሄድበት እግሩ እሆንለታለሁ፤ ቢጠይቀኝ እሰጠዋለሁ፤ ጥበቃዬን ቢፈልግ እጠብቀዋለሁ።❞»ቡኻሪ ዘግበውታል።

📌ማስታወሻ

- ጆሮው፣ አይኑ፣ እጁ፣ እግሩ እሆነዋለሁ ማለት፦ በነዚህ አካላት ኸይርን እንጂ ሌላ ነገር እንዳይሰራ አደርገዋለሁ ማለት ነው።

-ወሊይ(የአላህ ወዳጅ) የሚባለው፦ ማንኛውም አማኝ የሆነና አላህን የሚፈራ ሰው ነው።


📎ከሐዲሱ የምንይዛቸው ቁምነገሮች

📍የአላህ ወዳጆች ያላቸው ደረጃና እነሱን ጠላት አርጎ መያዝ ያለውን አደጋ

📍ግዴታ ዒባዳዎች ከምንም እንደሚበልጡና ወደ አላህ እንደሚያቃርቡ

📍ሱና ዒባዳዎች የአላህን ውዴታ እንደሚያስገኙ

📍አላህ ለወደደው ባሪያው ምን እንደሚያደርግለት

📍አንድ ሰው አላህ እንደወደደውና እንዳልወደደው በምን እንደሚያውቅ



والله أعلم

© ሂዳያ መልቲሚዲያ

🗓 ሰኞ | ህዳር 30/2017

♡     ⎙ ㅤ ⌲         🔕           📢
ˡⁱᵏᵉ  ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ    ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ    ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ


اصبر فوالله إن الله أرحم بك من نفسك، والله سبحانه وتعلى لا يمكن أن يبتليك بشر إلا لحكمة منه،

إذًا الله عز وجل من رحمته ما يجعل حياتك كلها بلاء. إن أخذ منك الشيء أعطاك أشياء أخرى. لا يمكن، هذا هو من رحمة الله، ولذالك...
قال النبي ﷺ: « إنَّ عِظَمَ الجَزَاءِ مَعَ عِظَمِ الْبَلَاءِ، وَإنَّ اللهَ إذَا أَحَبَّ قَومًا ابتِلاهُم، فَمَن رَضِيَ فَلَهُ الرِّضا، وَمَن سخِطَ فَلَهُ السُّخْطُ »
أخرجه الترمذي، وابن ماجه

ታገስ! አላህ ላንተ ካንተ ነፍስ የበለጠ አዛኝ ነው። አላህም አንተን በመጥፎ አይፈትንህም ለጥበብ ቢሆን እንጂ።

አላህ በእዝነቱ ሙሉ ሀያትህን በላእ አያደርግብህም። የሆነ ነገርን ቢይዝብተህ(ቢወስድብህ) ብዙ ነገራትን ሰጥቶሀል(ትቶልሀል)። ለዚህም ሲባል ነብዩ ﷺ እነዲህ አሉ: ❝የአጅር መብዛቱ ከበላእ መብዛቱ ነው። አላህ የሆኑ ሰዎችን በወደዳቸው ጊዜ ይፈትናቸዋል። ወዶ የተቀበለ(ሰብር ያደረገ)ለሱ የአላህ ውዴታ አለቀለት። የተቆጣ(ያማረረ) ደግሞ ለሱ የአላህ ቁጣ አለበት።❞

ቲርሚዚይና ኢብኑ ማጃ ዘግበውታል

@hidaya_multi


እነሆ ዲመሽቅ ተከፍታለች‼

ታሪካዊ ቀን‼

አንዱና ዋነኛው የዐረብ አብዮት ውጤት‼

🇸🇾🇸🇾🇸🇾🇸🇾🇸🇾🇸🇾🇸🇾🇸🇾🇸🇾🇸🇾🇸🇾🇸🇾

أيتها الأمة العظيمة.... الليلة فُتحت دمشق

2024/12/8.

من ثمر ربيع العربي

በመጨረሻው ዘመን ሃገረ ሻም የኢስላምና የሙስሊሞች መሸሸጊያ ትሆናለች‼

አቢ ኡማማህ (አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና) ውዱን ነቢይ ﷺ ስለ ኑብዋቸው አጀማመር ሲጠይቃቸው «የአባቴ የኢብራሂም ዱዓእ፣ የዒሳ ብስራት (ነኝ)። እናቴ የሻምን ግንቦች ያበራ ኑር ከርሷ ሲወጣ አይታለች።» አሉ።

[ሲልሲለቱ-ል-አሓዲሢ-ስ'ሶሒሓህ: 1545]


ኢብኑ ከሢር በተፍሲራቸው ላይ «በኑራቸው መታየት ሻምን ለብቻ ለይተው መጥቀሳቸው፤ በሻም ምድር ላይ ዲናቸውና ነቢይነታቸው ዘውታሪ ሆኖ እንደሚቀጥል ማሳያ ነው!
ለዚህም ሲባል ሻም በመጨረሻው ዘመን የኢስላምና ባለቤቶቹ መሸሸጊያ ትሆናለች። በርሷም ውስጥ የመርየም ልጅ ዒሳ ይወርዳል። (ደጃልንም ይገድላል!)» ብለዋል።

[ተፍሲር ኢብኑ ከሢር: 1/444]

وعن أبي أمامة رضي الله عنه قال: قلت : يا نبي
الله! ما كان أوّل بدء أمرك؟ قال: "دعوة أبي إبراهيم، وبشرى عيسى، ورأت أُمّي أنه يخرج منها نور أضاءت منها قصور الشام"

قال ابن كثير رحمه الله : "وتخصيص الشام بظهور نوره : إشارة إلى استقرار دينه، ونبوته ببلاد الشام .
ولهذا تكون الشام في آخر الزمان معقلاً للإسلام وأهله، وبها ينزل عيسى ابن مريم" انتهى .


© Murad Tadese

https://t.me/hidaya_multi

🤲አላህ ለሙስሊሞችናቸዉ ለሙስሊም ሀገራት ድልን ይወፍቃቸው!


🔷መሰል መልእቶች ለማግኘት ተ🀄️ላ🀄️ሉ

📢 t.me/hidaya_multi

🔕 𝔧𝔬𝔦𝔫 𝔞𝔫𝔡 𝔲𝔫𝔪𝔲𝔱𝔢


📚#የሀዲስ_ትምህርት

📖الحديث السابع والثلاثون

عن ابن عباس - عن رسول الله - فيما يرويه عن ربه تبارك وتعلى قال: «إن الله كتب الحسنات والسيئات، ثم بين ذلك، فمن هم بحسنة فلم يعملها، كتبها الله عنده حسنة كاملة، وإن هم بها فعملها، كتبها الله عنده عشر حسنات إلى سبع مئة ضعف، إلى أضعاف كثيرة، وإن هم بسيئة فلم يعملها، كتبها الله عنده حسنة كاملة، وإن هم بها فعملها، كتبها الله عنده سيئة واحدة.» رواه البخاري ومسلم في صحيحيهما بهذه الحروف.

📘ሐዲስ ቁጥር 37

ከኢብኑ ዓባስ እንደተላለፈው; የአላህ መልእክተኛﷺ ከጌታቸው በሚዘግቡት ነገር(ሐዲስ አል ቁድስ) ውስጥ; አላህ እንዲህ ብሏል; «አላህ መልካም እና መጥፎ ስራዎችን(ከምንዳቸው ጋር) ደንግጓል፤ ከዛም ይህን ተናግሯል፤ መልካምን ለመስራት ያሰበና የወሰነ ከዛም ያልሰራው፥ አላህ እሱ ዘንድ የተሟላ አጅርን ይፅፍለታል፤ እሷን(መልካም ስራን ለመስራት) ወስኖ የሰራት፥ አላህ እሱ ዘንድ ከ10 - 700 እጥፍ ከዛም በላይ(አጅሩን) ያበዛለታል፤ መጥፎ ስራን ለመስራት ያሰበና የወሰነ ከዛም ያልሰራው፥ አላህ እሱ ዘንድ የተሟላ አጅርን ይፅፍለታል፤ እሷን(መጥፎ ስራን ለመስራት) ወስኖ የሰራት፥ አላህ እሱ ዘንድ አንድ ወንጀል ይፅፍበታል።»

ቡኻሪና ሙስሊም ሶሒሓቸው ላይ በዚህ መልኩ ዘግበውታል።


📌ማስታወሻ

- መልካምን ለመስራት ወስኖ ያልሰራ ሲባል፦ በዑዝር ምክንያት ለማለት እንጂ ሐሣብ ቀይሮ ማለት አይደለም

- መጥፎን ለመስራት ወስኖ ያልሰራ ሲባል፦ አላህን በመፍራት ከተወው እንጂ ስላልተመቻቸለት ያልሰራ አይደለም

🔗ከሐዲሱ የምንይዛቸው ቁምነገሮች

📍መልካምና መጥፎ ስራዎች(ከነ ምንዳቸው) የተፃፉ መሆናቸውን

📍የኒያን ደረጃ፦ አንድ ሰው መልካምን ለመስራት አስቦና ወስኖ በዑዝር ምክንያት መስራት ባይችል በኒያው አንድ አጅር ስለሚፃፍለት

📍ወንጀልን ለአላህ በሎ መተው ምንዳን እንደሚያስገኝ

📍አላህ ችሮታው ሰፊ መሆኑን፥ መልካም ስራ ስንሰራ እጥፍ አርጎ መክፈሉ።

📍መልካም ስራ ያለውን ደረጃ

📍የአላህን እዝነት፦ ወንጀልን የሰራ ሰው በአንድ ብቻ መፃፉ


والله أعلم

© ሂዳያ መልቲሚዲያ

🗓 ጁሙዓ | ህዳር 27/2017

♡     ⎙ ㅤ ⌲         🔕           📢
ˡⁱᵏᵉ  ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ    ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ    ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🌍ይቺ ዱንያ ናት!!🌏

🎙 الشيخ سعود الشريم


📍 የቀብር ቦታና የጀናዛ ሽኝት ላይ የሚስተዋሉ 11 ስህተቶች

🎙 ኡስታዝ አህመድ አደም

© ሂዳያ መልቲሚዲያ

በቪድዮ ለመመልከት ▼
https://youtu.be/vTgy0zQIrzU?si=wSjrR2XhPzVBqrit




📚#የሀዲስ_ትምህርት

📖الحديث السادس والثلاثون

عن أبي هريرة رضي الله عنه - عن النبيﷺ قال: «من نفس عن مؤمن كربة من كرب الدنيا، نفس الله عنه كربة من كرب يوم القيامة، ومن يسر على معسر، يسر الله عليه في الدنيا والآخرة، ومن ستر مسلما، ستره الله في الدنيا والآخرة، والله في عون العبد، ما كان العبد في عون أخيه، ومن سلك طريقا يلتمس فيه علما، سهل الله له به طريقا إلى الجنة، وما اجتمع قوم في بيت من بيوت الله، يتلون كتاب الله، ويتدارسونه بينهم، إلا نزلت عليهم السكينة، وغشيتهم الرحمة، وحفتهم الملائكة، وذكرهم الله فيمن عنده، ومن بطأ به عمله، لم يسرع به نسبه.»رواه مسلم بهذا اللفظ.


📗ሐዲስ ቁጥር 36

ከአቢ ሁረይራህ እንደተላለፈው; ነቢዩﷺ እንዲህ ብለዋል; «ከአንድ አማኝ ችግርን ያስወገደ, አላህ ከየውመል ቂያማ ችግሮች አንድን ችግር ያስወግድለታል፤ የተጨናነቀን(በዕዳ ወይም በሌላ ነገር) ያቃለለ፤ አላህ በዱንያም በአኸራም ያቃልልለታል፤ የሙስሊምን ነውር የደበቀ አላህ የሱን ነውር ይደብቅለታል፤ አላህ አንድን ባሪያ በማገዝ ላይ ነው፥ ባሪያው ወንድሙን እስካገዘ ድረስ፤ እውቀትን ፈልጎ መንገድ የጀመረ አላህ (እውቀትን ፈልጎ በመጓዙ ሰበብ) የጀነትን መንገድ ያቀልለታል፤ ሰዎች ቁርአንን ሊቀሩ እና ሊማማሩ ከአላህ ቤቶች በአንዱ አይሰባሰቡም፥ አላህ እርጋታን ቢያወርድባቸው፣ የአላህ እዝነት ቢያካልላቸው፣ መላኢኮች ቢከቧቸው(ዱዐ ሊያደርጉላቸው)፣ አላህ እሱ ዘንድ ያሉ(መላኢኮች) ጋር ቢያወሳቸው እንጂ፤ ስራው ወደ ኋላ(ጀነት ከመግባት) ያስቀረው ዘሩ አያፈጥነውም(ጀነት አያስገባውም)።»

ሙስሊም በዚህ መልኩ ዘግቦታል

📎ከሐዲሱ የምንይዛቸው ቁምነገሮች


📍የሙእሚንን ችግር ማስወገድ፣ ማቃለልና ነውሩን መደበቅ ያለውን ደረጃ

📍ሙእሚንን ማገዝ አላህ እንዲያግዘን እንደሚያረግ

📍እውቀትን መፈለግ ያለውን ደረጃ

📍አንድ ሰው ለኸይር ስራ የሚያደርገው ጉዞ እንደሚያስመነዳው

📍ቁርአንን መስጂድ ውስጥ መማማር ያለውን ደረጃ

📍አላህ ከዐርሽ በላይ መሆኑን


والله أعلم

© ሂዳያ መልቲሚዲያ

🗓 ረቡዕ | ህዳር 25/2017

♡     ⎙ ㅤ ⌲         🔕           📢
ˡⁱᵏᵉ  ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ    ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ    ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ


💡 ከሞት በኋላ ላለው ህይወት የሚጠቅሙ ነገሮች!

💦 ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

﴿سبعٌ يَجري للعبدِ أجرُهُنَّ، وهوَ في قَبرِه بعدَ موتِه: مَن علَّمَ علمًا، أو أجرى نهرًا، أو حفَر بِئرًا، أوغرَسَ نخلًا، أو بنى مسجِدًا، أو ورَّثَ مُصحفًا، أو ترَكَ ولدًا يستغفِرُ لهُ بعد موتِه﴾

“ሰባት ነገሮች ለአንድ ባሪያ ከሞት በኋላ በቀብር ውስጥ እያለ የሚመነዳው ናቸው። እነሱም፦ እውቀትን ያስተማረ እንደሆነ፣ ወይም ወንዝን (ምንጭና የመሳሰሉትን በመስኖም ሆነ በቧንቧ ለሰው እንዲጠቅም) እንዲፈስ ያደረገ፣ ወይም የጉድጎድ ውሃ የቆፈረ፣ ወይም የተምር ዛፍ የተከለ፣ ወይም መስጂድ የገነባ፣ ወይም መፅሀፍ ያወረሰ፣ ወይም እሱ ከሞተ በኋላ ለሱ ምህረት የሚጠይቅለት መልካም ልጅ ናቸው።”

📚 ሶሂህ አልጃሚ፡ 3602

🔎 እነዚህ ሰባት ነገራትን በሌላ ሀዲሳቸው በሶስት ዋና ዋና ተግባራት ጠቅልለው ይነግሩናል።

عن أبي هريرة أن رسول الله ﷺ قال:
«إذا مات ابن آدم انقطع عمله إلا من ثلاث; صدقة جارية،أو علم ينتفع به، أو ولد صالح يدعو له»

የአደም ልጅ ሲሞት ከእነዚህ ሶስቱ በቀር ስራው ይቋረጣል;

ቀጣይነት ያላት ሰደቃ (ጥቅሙ ከሞተ በኋላ ቀጣይነት ያለው)

የሚጠቀሙበት እውቀት (ሰዎች የሚጠቀሙበት የሆነ እውቀትን ያስተላለፈ)

ለሱ ዱዓ ሚያደርግለት ሷሊህ ልጅ( በመልካም አስተዳደግ ልጁን አሳድጎ እሱ ሲሞት ለአባቱ ምህረትን የሚጠይቅለት ልጅ)

አንድ ሰው ከሞት ቦሀላ ለሱ አጅርን መሸመቻ ሚሆኑት ነገራት ናቸው። ዱንያ ላይ ብዙ ኸይር ሳይሰራ ቢሞት በነዚ ተግባራት ከቅጣት ሊድን ይችላል።

ቴሌግራም: t.me/hidaya_multi


በቲክቶክ ፣ ቴሌግራም እና ዩቲዩብ ፕላትፎርም ሂዳያ መልቲሚዲያ ይከታተሉ ያሰራጩ ይደግፉ!

➝ ቲክቶክ
➝ ቴሌግራም
➝ ዩቲዩብ

ይሄን ፖስት ሼር በማድረግ እንቅስቃሴውን ደግፉ!

👍      ⌲         🔕          📢
ˡⁱᵏᵉ     ˢʰᵃʳᵉ    ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ    ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ


📚#የሀዲስ_ትምህርት

📖الحديث الخامس والثلاثون

عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول اللهﷺ ؛ «لا تحاسدوا، ولا تناجشوا، ولا تباغضوا،  ولا تدابروا، ولا يبع بعضكم على بيع بعض، وكونوا عباد الله إخوانا، المسلم،لا يظلمه، ولا يخذله، ولا يكذبه، ولا يحقره، التقوى هاهنا، ويشير إلى صدره ثلاث مرات، بحسب امرئ من الشر أن يحقر أخاه المسلم، كل مسلم على ميلم حرام، دمه، وماله، وعرضه.» رواه مسلم

📕ሐዲስ ቁጥር 35

አቢ ሁረይረህ እንዲህ ብለዋል: የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል; «አትመቃቀኙ፣ አትቦጫጨቁ፣ አትጠላሉ፣ ጀርባ አትሰጣጡ፣ አንዳችሁ የወንድሙ ገበያ ላይ አይገበያይ፣ ወንድማማች የአላህ ባሮች ሁኑ፤ ሙስሊም ለሙስሊም ወንድሙ ነው። አይበድለው፤ እርዳታን አይንፈገው፤ አይዋሸው፤ አያዋርደው(አሳንሰው)፤ “አላህን መፍራት እዚህ ጋር ነው” 3 ጊዜ አሉ(በእጃቸው ወደ ደረታቸው እያመለከቱ)፥ አንድ ሰው ሙስሊም ወንድሙን አሳንሶ ማየቱ ወንጀል ላይ ለመውደቅ(ጀሀነም ለመግባት) በቂው ነው፥ ሁሉም ሙስሊም በሌላ ሙስሊም ላይ ደሙ፣ ገንዘቡ፣ ክብሩ ሀራም ነው።»

ሙስሊም ዘግበውታል።

📌ማስታወሻ

- አትቦጫጨቁ ማለት፦ ሁለት ሻጮች ተባብረው ገዥን እንዳይበሉ፥ ይህም፦ ሻጭ እና ገዥ ሲደራደሩ የሻጭ ጓደኛ ገዥ መስሎ እቃውን ማዋደድና ገዢው ጨምሮ እንዲገዛ ማድረግ።
ወይም ሁለት ገዢዎች ተባብረው ሻጭን እንዳይበሉ፥ ይህም፦ ሻጭ እና ገዥ ሲደራደሩ የገዥ ጓደኛ ሌላ ገዥ መስሎ እቃውን ማራከስና ሻጩ ቀንሶ እንዲሸጥ ማድረግ።
- በወንድሙ ንግድ ውስጥ አይነግድ ማለት፦ ሻጭ እና ገዥ ተደራድረው ሳይለያዩ ሌላ ሻጭ ወይም ገዥ ጣልቃ አይግባ ማለት ነው።


📎ከሐዲሱ የምንይዛቸው ቁምነገሮች

📍ሐዲሱ ላይ የተጠቀሱ ነገሮች እንደተከለከሉ

📍ሙስሊሞች ወንድማማች እንደሆኑ

📍የወንድማማችነት መስፈርት እስልምና መሆኑን

📍አላህን የመፍራት መሰረት ልብ መሆኑን

📍ሙስሊምን አሳንሶ የማየት አደጋነት

والله أعلم

© ሂዳያ መልቲሚዲያ

🗓 እሁድ | ህዳር 22/2017

♡      ⎙ ㅤ ⌲         🔕         📢
ˡⁱᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ   ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ




1➝10 ሰለዋት


عن عبد الله بن عمرو بن العاص رضي الله عنهما أن النبي صلى الله عليه وسلم قال : (مَنْ صَلَّى عَلَيَّ صَلَاةً صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشْرًا). رواه مسلم

አብደላህ ቢን አምር ቢን ወቃስ እንዳስተላለፈው:-
ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:-
«እኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ አላህ እሱ ላይ አስር ሰለዋት ያወርድበታል።»
📚ሙስሊም ዘግቦታል



Показано 20 последних публикаций.