የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በመምህራችን ኤፍሬም ሀብቴ ሹኩሮ (ረ/ፕ) ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል፡፡
ረዳት ፕሮፌሰር ኤፍሬም ሀብቴ ሹኩሮ በዩኒቨርስቲያችን በነበራቸው ቆይታ ተግባቢ እና አመለሸጋ እንደነበሩ መላው የጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ መህበረሰብ ይመሰክራል፡፡
ረዳት ፕሮፌሰር ኤፍሬም ሀብቴ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ስራዎች ትኩረት እንዲሰጣቸው እና በዘርፉ ሰፊ እንቅስቃሴ እንዲከወን የበኩላቸውን የተወጡ ንቁ እና ሀላፊነት የሚሰማቸው መምህራችን ነበሩ።
ብዙ ያገለግሉናል ስንል በወጣትነታቸው ከጎናችን ለተለዩን የስራ ባልደረባችን ረዳት ፕሮፌሰር ኤፍሬም ሀብቴ ጥልቅ ሀዘናችንን እየገለፅን በዩኒቨርስቲያችን በነበራቸው ቆይታ ያበረከቱትን እልፍ አስተዋፅኦ በማሠብ እናመሰግናቸዋለን!
በባልደረባችን ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለስራ ባለደረቦቻቸው እና ለመላው የዩኒቨርሲቲያችን ማኅበረሰብ መጽናናትን እንመኛለን።