KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Новости и СМИ


Kotebe University of Education Community / አዲስ ነገር መረጃ /

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций




የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያን ይፋ አደረገ።

የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ በሚያስተምሩ መምህራን ላይ ተፈጻሚ የሚሆን "የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1148/2018" አውጥቷል።

ሚኒስቴሩ በአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1368/2017 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ያዘጋጀው ይህ መመሪያ፣ በማስተማር ሥራቸው የላቀ ውጤት የሚያስመዘግቡ መምህራንን ለማበረታታት፣ የሥራ ተነሳሽነታቸውን ለማሳደግ እንዲሁም አጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በመመሪያው ድንጋጌ መሠረት የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የእድገት መሰላል በሰባት ደረጃዎች የተከፋፈለ ሲሆን፤ እነሱም ፦
- ጀማሪ መምህር፣
- መለስተኛ መምህር፣
- መምህር፣
- ከፍተኛ መምህር፣
- ተባባሪ መሪ መምህር፣
- መሪ መምህር እና ከፍተኛ መሪ መምህር ናቸው።

በመመሪያው የተቀመጠው የቆይታ ጊዜም ከጀማሪ ወደ መለስተኛ መምህርነት ለመሸጋገር 2 ዓመት፣ በቀጣዮቹ ደረጃዎች ደግሞ በእያንዳንዱ እርከን የ3 ዓመታት ቆይታ የሚጠይቅ ነው።

ይሁን እንጂ አንድ መምህር በተከታታይ ወይም በተለያየ ጊዜ በውድድር ሁለት ጊዜ እድገት ማግኘት ካልቻለ ለሦስተኛ ጊዜ የመወዳደር ዕድል እንደማይኖረው በመመሪያው ተደንግጓል።

መምህራን ለደረጃ እድገት ውድድር ብቁ ለመሆን ማሟላት ከሚገባቸው የጋራ መስፈርቶች መካከል በመምህርነት ሙያ ዕውቅና ካለው ተቋም የተመረቁ መሆን፣ የሙያ ፈቃድ ምስክር ወረቀት መያዝ፣ እንዲሁም ለጀማሪ መምህራን የመውጫ ምዘና ማለፍ በዋናነት ተቀምጠዋል።

ከዚህ በተጨማሪም አንድ መምህር ለደረጃ እድገት ለመብቃት ከሚያስተምራቸው ተማሪዎች ውስጥ ቢያንስ 75 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው በገለልተኛ አካል መረጋገጥ እንዳለበት ሰነዱ ያትታል።

በተጨማሪም ጀማሪ መምህራን ቢያንስ የ40 ሰዓታት፣ ከመለስተኛ መምህር ጀምሮ ያሉት ደግሞ የ60 ሰዓታት ሙያ ተኮር አጫጭር ሥልጠናዎችን መከታተልና የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ (CPD) ዕቅዳቸውን በአግባቡ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል።

ወደ ከፍተኛ የእድገት እርከኖች ለመሸጋገር የተቀመጡት መመዘኛዎች የማስተማር ብቃትን ብቻ ሳይሆን የምርምርና የማኅበረሰብ አገልግሎት ተሳትፎንም ያካተቱ ናቸው።

በዚህም መሠረት መምህራን ከደረጃ ወደ ደረጃ ሲሸጋገሩ ከ70 እስከ 90 በመቶ የሚደርስ የሥራ አፈጻጸም ውጤት ማስመዝገብ፣ የተደራጀ ማኅደረ-ተግባር (Portfolio) መያዝ፣ ጀማሪ መምህራንን በአማካሪነት መደገፍ እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸውንና ተጋላጭ ተማሪዎችን መርዳት ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

በተለይም ከመካከለኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉት ከፍተኛ እርከኖች ለመወዳደር የመማሪያና የመምሪያ መጻሕፍትን መገምገም፣ አጋዥ የትምህርት ጽሑፎችን ማዘጋጀት እና በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ ተግባራዊ ጥናትና ምርምሮችን (Action Research) ማካሄድ የግድ እንደሚል ሰነዱ በዝርዝር አስቀምጧል።

አዲሱ መመሪያ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ መምህራን የተፋጠነ የደረጃ እድገት የሚሰጥበትን አሠራርም አስተዋውቋል።

በዚህም መሠረት ከመምህርነት እስከ መሪ መምህርነት ባለው እርከን የሚገኝ ማንኛውም መምህር የሚያስተምራቸው ተማሪዎች በሙሉ 85 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት በተከታታይ ሁለት ዓመታት እንዲያስመዘግቡ ካደረገ እና ይህም በገለልተኛ አካል ሲረጋገጥ፣ የሦስት ዓመት የቆይታ ጊዜውን ሳይጠብቅ በሁለት ዓመት ውስጥ እንዲያድግ ይደረጋል።

በተመሳሳይም የተማሪዎቹን ውጤት 90 በመቶ እና ከዚያ በላይ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ያደረሰ መምህር አንድ የደረጃ መሰላል ዘሎ እንዲያድግ የሚፈቀድ ሲሆን፤ በከፍተኛ መሪ መምህርነት ደረጃ ላሉት ደግሞ የሁለት እርከን ደመወዝ ጭማሪ እንደሚሰጥ ተመላክቷል።

በሌላ በኩል መመሪያው የወሊድ ፈቃድ ላይ ያሉ መምህራንን፣ በጤና እክል ምክንያት በቦርድ ውሳኔ ከክፍል የተገለሉ ባለሙያዎችን እና በመምህራን ማኅበራት በአመራርነት የሚያገለግሉ አባላትን የደረጃ እድገት አፈጻጸም በልዩ ሁኔታ አካቷል።

የደረጃ እድገቱ በየዓመቱ በሁለት ዙር ማለትም በጥር አንድ እና በሐምሌ አንድ ቀን ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ ሂደቱም በትምህርት ቤት ቴክኒክ ኮሚቴና በደረጃ እድገት ኮሚቴ ተጣርቶ በወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት አማካይነት ይጸድቃል።

አሠራሩ ፍትሐዊና ገለልተኛ እንዲሆን የጥቅም ግጭትን የሚከላከሉ ድንጋጌዎች የተካተቱበት ሲሆን፣ በውሳኔው ላይ ቅሬታ ያላቸው መምህራንም ደብዳቤው በደረሳቸው በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተደንግጓል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም








በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ አባላትን ያሳተፈ አጠቃላይ ስብሰባ ተካሄደ
*** *** *****

(ኮትዩ፣ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም) በውይይቱ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ፣ ተሰብሳቢዎችን እንኳን ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አደረሳችሁ በማለት፣ የውይይት መድረኩ የዓመቱ የአካዳሚክ ሥራ መጀመሩን ለማብሰር፣ በባለፈው ዓመት የታዩትን ውጤቶች በመፈተሽ ለ2019 ዓ.ም የተሻለ ተስፋና ተነሳሽነትን የምንሰንቅበት ነው ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲያችን የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሆኖ በመመረጡ ዕድለኛ ነው ያሉት ፕሬዘዳንቱ፣ ከዚህ አንጻር ባለፈው ዓመት የተከናወኑት ዋና ዋና የሪፎርም፣ የአወቃቀር እና የአሠራር ተግባራት ዩኒቨርሲቲውን ወደ ስፔሻላይዝድ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እና ወደ ስፔሻላይዝድ ኦቶኖመስ ዩኒቨርሲቲ የሚወስዱ መሆናቸውን፤ በዚህ ሂደትም የተዘጋጁት ስትራቴጂክ ዕቅድ፣ የሴኔት ሌጂስሌሽን፣ የዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ ደንብ፣ የአካዳሚክ ሪፎርም፣ የደብል ሜጀር፣ የግንባታና መሰል በርካታ ስኬታማ ሥራዎች መሠራታቸውን፣ በ2019 የትምህርት ዘመንም እነዚህን ተግባራት አጠናክሮና አሻሽሎ የማስቀጠል ተግባራት እንደሚከናወኑም በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የስትራቴጂክ ጉዳዮች ጽ/ቤት ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስናቀ ጉዲሳ የ2018 ዓ.ም ቁልፍ የውጤት አመላካቾችን (KPIs) ሪፖርት እና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ያቀረቡ ሲሆን፣ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በተፈረመው መሠረት በተመረጡ አምስት የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ውጤታማ ሥራዎች መሰራታቸውን፣ ፈጠራን እና አዳዲስ ሙከራዎችን በመሞከር፣ በቀጣይም አሰራሮቻችንን ቁልፍ የውጤት አመላካቾች (KPIs) አካል በማድረግ አፈጻጸሙን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር አለባቸው ኬሚሶ፣ የምርምርና የማኅበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር ቴዎድሮስ ሙሉጌታ፣ የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሽመልስ ዘውዴ ትኩረት ተሰጥቶ በተሠራባቸው የአካዳሚክ፣ የምርምር፣ የመሠረተ ልማት ግንባታ፣ የአሠራር ለውጦች ላይ የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ፣ እንዲሁም በበጀት ዓመቱ ምን ይጠበቃል፣ ምን ምንስ ይከናወናል በሚሉ ጉዳዮች ገለጻ አድርገው ውይይት ተካሄዷል፡፡

በውይይቱም፣ የቀረቡት የሪፎርም እና የግንባታ ሥራዎች የዩኒቨርሲቲውን ለውጥ የሚያሳዩ እንደሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የኦንላይን ኮርሶችን፣ ያልፀደቁ የትምህርት ፕሮግራሞችን የማየት፣ የትምህርት ጥራት ከማምጣት እንዲሁም የመምህሩን የቤት ችግሮች በፍጥነት ከመፍታት ጎን ለጎን በቀጣይ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተነሳሽነትን በመጨመር ሥራ መሥራትና የተሻለ ውጤት ማስማዝገብ እንደሚያስፈልግም ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

- የህዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

#Kotebe_University_ofEducation_committed_to_excellence_in_Education

ለተጨማሪ መረጃ ይፋዊ ገጾቻችንን ይከታተሉ:
Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.et
Website: https://www.kue.edu.et/
YouTube: https://youtube.com/@kueducation
Facebook (https://web.facebook.com/www.kue.edu.et)
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook






ማስታወቂያ

የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይመለከታል

በትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመመደብ ሂደትን አጠናቋል።
ምደባው ፍትሐዊነትን፣ ግልጽነትን፣ እኩል ዕድልን እና ሚዛናዊ ስርጭትን በሚያረጋግጥ መልኩ፣ የተማሪዎችን ውጤትና ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም እንዲሁም ሌሎች የምደባ መስፈርቶችን ታሳቢ በማድረግ ተከናውኗል።

1. የምደባው ዋና መስፈርቶች

1.1. የተማሪዎች አጠቃላይ ውጤት እና የዩኒቨርሲቲ ምርጫ

የተማሪዎች አጠቃላይ የብሔራዊ ፈተና ውጤት የምደባው ዋና የቅደም ተከተል መስፈርት ሆኖ ተወስዷል። በዚህም መሠረት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በምርጫቸው መሠረት የመመደብ ቅድሚያ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በተቻለ መጠን ከመረጧቸው የመጀመሪያ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል።

1.2. የዩኒቨርስቲዎች የተማሪ ቅበላ አቅም

የእያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ የተማሪ ቅበላ አቅም በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል። በመሆኑም የተማሪው ውጤትና ምርጫ ከዩኒቨርስቲዎች የቅበላ አቅም ጋር በማጣጣም ምደባው ተከናውኗል።

1.3. የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ እና የትምህርት ቤት ስርጭት

በዩኒቨርሲቲዎቻችን ህብረ ብሄራዊነትን የሚያጸና እና የተማሪዎችን ሚዛናዊ ስርጭት ለማረጋገጥ፦
• 70 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ከተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውጭ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ፤

• 30 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ደግሞ በተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል። በተጨማሪም የዞን፣ የወረዳ እና የትምህርት ቤት ስርጭት በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል።

1.4. የፆታ ሚዛን

በዩኒቨርሲቲዎች የሴትና የወንድ ተማሪዎች ስብጥር ሚዛናዊ እንዲሆን በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል።

2. ልዩ ምደባ

2.1. ማየት እና መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች

ማየት እና መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርትና የድጋፍ አገልግሎት ሊያገኙ በሚችሉባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል።

2.2. 500 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች

በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ600 ነጥብ 500 እና ከዚያ በላይ አጠቃላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች፣ ላስመዘገቡት የላቀ የአካዳሚክ ውጤት ልዩ ታሳቢነት በመስጠት፣ በመጀመሪያ ምርጫቸው ተመድበዋል።

ይህ ልዩ የምደባ አሠራር ተማሪዎቹ በብሔራዊ ፈተናው ላስመዘገቡት የላቀ ውጤት ዕውቅና ለመስጠት እና ከፍተኛ አፈጻጸምን ለማበረታታት የተደረገ ነው።

3. የምደባ ውጤትን ስለመመልከት

ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት በመጠቀም ማየት ይችላሉ።

የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለማየት ማስፈንጠሪያ፦ https://student.ethernet.edu.et/view-placement

4. ቅሬታ ስለማቅረብ

በምደባው ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት ብቻ ይህ ምደባ ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን መረጃና ማስረጃ በማያያዝ እንዲያቀርቡ እናሳስባለን።

የቅሬታ ማቅረቢያ ማስፈንጠሪያ፦ https://student.ethernet.edu.et/complaints
• በአካል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በመምጣት የሚቀርብ የምደባ ቅሬታ የማይስተናገድ መሆኑን ተማሪዎችና ወላጆች እንዲገነዘቡ እናሳውቃለን።

5. ማሳሰቢያ

ቅሬታ በሚቀርብበት ወቅት የሐሰት መረጃ፣ የተሳሳተ ማስረጃ ወይም የተጭበረበረ ሰነድ ማቅረብ በፍጹም የተከለከለ ነው። በቅሬታ ሂደት የሚቀርቡ መረጃዎችና ሰነዶች ትክክለኛነት የሚረጋገጥ ሲሆን፣ የሐሰት መረጃ ወይም ሰነድ አቅርበው የተገኙ ተማሪዎች ምደባቸው ሊሰረዝ ይችላል።

በመሆኑም ሁሉም ተማሪዎች ቅሬታቸውን በእውነተኛና በተረጋገጠ መረጃ ላይ ብቻ በመመሥረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲያቀርቡ እናሳስባለን።
የትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እያለ፣ በቀጣዩ የከፍተኛ ትምህርት ጉዟችሁ ስኬታማ እንድትሆኑ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

የትምህርት ሚኒስቴር








#KUE

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ አንድ ለመምህርነት የሚሰለጥን ተማሪ፥ በሁለት አይነት የትምህርት ዲሲፕሊን እንዲሰለጥን የሚያስችል ፕሮግራም ሊጀምር ነው።

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የተከለሱና በአዲስ መልክ የተዘጋጁ የአካዳሚክ ፕሮግራሞችን መርምሮ አፅድቋል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲው ቀደም ሲል በአንድ አይነት የሜጀር ፕሮግራም ሲያካሒድ የቆየውን መማር ማስተማር በማሻሻል፣ "የደብል ሜጀር" መርሐግብር እንዲጀመር ወስኗል።

መርሐግሩ የሀገሪቱን የትምህርት ጥራት ከፍ ለማድረግ፣ የመምህራንን አቅም ለማሳደግ እና የመምህራንን እጥረት ለመቅረፍ የሚያግዝ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተሾመ ነቃጥበብ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

Ethio Education And Career Hub




JAMK University of Applied Sciences Delegates Visit KUE
*** *** *****

(KUE, September 7, 2026) — A delegation from JAMK University of Applied Sciences, Finland, comprising Mr. Graham Burns, Mrs. Sanna Paananen, and Mr. Jarkko Blomqvist, visited Kotebe University of Education (KUE) to explore opportunities for collaboration in digital transformation, digital pedagogy, and technology-enhanced education. During the visit, the delegation held discussions with KUE senior management and members of the Gaming for Ethiopia (G4ET) project team, focusing on strengthening institutional cooperation and advancing KUE’s digital transformation agenda.

The welcoming address was delivered by Dr. Teshome Nekatibeb, President of KUE, who highlighted the University’s long history and its transformation into a specialized university of education. He noted that KUE has undertaken significant institutional reforms in recent years, including curriculum revision, initiatives to strengthen internationalization, and the development of innovative academic programs, including double-major opportunities.
Dr. Teshome emphasized the growing importance of digital transformation to the future of higher education and expressed KUE’s commitment to working closely with JAMK and other partners to successfully implement the proposed initiatives.

Dr. Alebachew Kemisso, Vice President for Academic Affairs, highlighted the alignment between KUE’s digital transformation agenda and Ethiopia’s broader Digital Ethiopia 2030 vision. He explained that KUE has been reviewing its curriculum and introducing new approaches to strengthen technology-supported teaching and learning. He further noted that collaboration with JAMK presents an important opportunity to accelerate these efforts and enhance the quality of education at the University.

Speaking about the project, Dr. Fekede Tuli, a KUE lecturer and member of the project team, emphasized the importance of digital technology in contemporary education. He noted that the G4ET project could contribute significantly to KUE’s digital transformation, strengthen institutional collaboration, and support the establishment of a Digital Technology Center at the University. Such a center could also enable KUE to share digital expertise and provide technical and professional support to other educational institutions.

During the meeting, the JAMK delegation presented the G4ET project concept, outlining its strategic objectives, planned activities, expected outcomes, responsibilities, and implementation approaches. The participants also discussed KUE’s ongoing digital transformation journey, including the review and implementation of its Digital Transformation Strategy.
As part of the visit, the delegation toured KUE’s digital and educational facilities, including classrooms, ICT laboratories, the library, and the proposed site for the Pedagogical Innovation Hub. The tour provided the JAMK team with an opportunity to assess KUE’s existing digital infrastructure and identify potential areas for collaboration and further development.

The discussions concluded with a shared commitment to strengthening the partnership, exploring areas of synergy, and advancing practical steps toward the implementation of the G4ET project and KUE’s broader digital transformation agenda.
Kotebe University of Education remains committed to building strategic international partnerships that promote innovation, digital transformation, quality teaching and learning, and excellence in teacher education.

- Public and International Relations Executive Office

#Kotebe_University_of Education_committed_to_excellence_in_Education
For more information, follow our official pages:
Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.et
Website: https://www.kue.edu.et/
YouTube: https://youtube.com/@kueducation
Facebook (https://web.facebook.com/www.kue.edu.et)
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook




በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የቆየው የወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን የአሰልጣኝነት ሙያ ማሻሻያ ስልጠና ተጠናቀቀ
*** *** *****

(ኮትዩ፣ ዿግሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም) - በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ከነሐሴ 26 እስከ ዿግሜ 01/2018 ዓ.ም ድረስ ሲሰጥ የቆየው የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን የአሰልጣኝነት ሙያ ማሻሻያ ስልጠና ለሰልጣኖች ሰርተፍኬት በመስጠት ተጠናቋል፡፡

በመዝጊያ ሥነስርዓቱ ላይ የተገኙት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር አበባ አማረ ለሰልጣኞች ሰርተፍኬት ከሰጡ በኋላ እንደተናገሩት፣ ወርልድ ቴኳንዶ እጅግ ተወዳጅ የስፖርት ዓይነት በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶን ለመጠበቅ፣ በሂደት የሚገጥሙትን ችግሮች በመፍታት ለማሳደግ ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ መስራት የሚያስፈልግ መሆኑን በመግለፅ፣ ሰልጣኞች ስልጠናችሁን ስኬታማ በሆነ መልኩ በማጠናቀቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሰውነት ማጎልመሻና ስፖርት ኢንስቲትዩት ዲን ዶ/ር ጥላሁን በረደድ በበኩላቸው፣ ትምህርትና ስልጠና የዩኒቨርሲቲያችን ዋና ተግባር በመሆኑ በቀጣይም ተመሳሳይ ስልጠናዎችን በማዘጋጀትና የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ባለሙያዎችን በማብቃት የስፖርት ዘርፉ ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን ከማድረግ በተጨማሪ ቴኳንዶ ትውልዱን በስነምግባር እንዲያንፅ ለማድረግ በተጀመረው አግባብ በትብብር እንሠራለን ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ዋና ጸሐፊ ማስተር ሞቱማ ጌታቸው፣ ወርልድ ቴኳንዶን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማሳደግና ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች ለማፍራት በዲፕሎማና በዲግሪ ደረጃ ትምህርት እንዲሰጥ፣ ባለሙያዎችን ከማብቃት ጎን ለጎን ቴኳንዶንም በየተቋማቱና በየትምህርት ቤቱ እንዲተዋወቅና እንዲስፋፋ፣ እንደሌላው የስፖርት አይነት የተለያዩ ውድድሮችም እንዲዘጋጁ ተከታታይ ስራዎች እንደሚሰሩ በማመልከት ይህ ስልጠና የተሳካ እንዲሆን ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ለነበረው ድርሻ አመስግነዋል፡፡

በስልጠናው ላይ የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚዎች፣ አሰልጣኞች እና ሰልጣኞች በሰጡት አስተያየት፣ ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ ስልጠና በእጅጉ ጠቃሚ በመሆኑ፣ በቀጣይም ከዘመኑ ሳይንስ ጋር በማስተሳሰር መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

- የህዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

#Kotebe_University_ofEducation_committed_to_excellence_in_Education

ለተጨማሪ መረጃ ይፋዊ ገጾቻችንን ይከታተሉ:
Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.et
Website: https://www.kue.edu.et/
YouTube: https://youtube.com/@kueducation
Facebook (https://web.facebook.com/www.kue.edu.et)
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook




የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የተከለሱና በአዲስ መልክ የተዘጋጁ የአካዳሚክ ፕሮግራሞችን መርምሮ አጸደቀ
**** ** ****

(ኮትዩ፣ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም) - በሴኔት ስብሰባው ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ እንደገለጹት፣ ዩኒቨርሲቲው ቀደም ሲል በአንድ ዓይነት የሜጀር ፕሮግራም ሲያካሂድ የቆየውን መማር ማስተማር በማሻሻል፣ አንድ ለመምህርነት የሚሰለጥን ተማሪ በሁለት ዓይነት የትምህርት ዲሲፕሊን እንዲሰለጥን የሚያስችል በመሆኑ በዩኒቨርሲቲው ሕይወትም ሆነ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ኃላፊነት ነው ብለዋል፡፡
እንደ ፕሬዘዳንቱ ገለጻ ይህ የደብል ሜጀር መርሐግብር የሀገራችንን የትምህርት ጥራት ከፍ ለማድረግ፣ የመምህራንን አቅም ለማሳደግ፣ የመምህራንን እጥረት ለመቅረፍ፣ የመማር ማስተማሩ ሂደት ሳይበደል ውጤታማ ሥራዎችን ለመስራት የሚያግዝ ነው፡፡
የሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞችን ለማጠናከርና ለማስጀመር የሚያስችል አስፈላጊው ውይይት ተደርጎባቸው እንደሚፀድቁም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ ተናግረዋል፡፡

የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር አለባቸው ኬሚሶ በበኩላቸው፣ የዛሬው የሴኔት ስብሰባ በዩኒቨርሲቲው ታሪክ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው የዩኒቨርሲቲውን ፕሮግራሞች የበለጠ ሳቢ፣ ተፈላጊ እና ዩኒቨርሲቲው ሀገራዊ ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ የሚያግዙ ፕሮግራሞችን ከዲፓርትመንት ካውንስል ጀምሮ እስከ የሴኔት ስታንዳርድ ኮሚቴ ድረስ ደረጃ በደረጃ ውይይት በማድረግ፣ በመከለስና በማሻሻል እንዲሁም የውጪ ገምጋሚዎችን በማስገምገም በሰፊው እየታዩ የመጡና ለዛሬው የውሳኔ ቀን የደረሱ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

በዚሁ መሠረት ለሴኔት የቀረቡት 83 ፕሮግራሞች ሲሆኑ፣ ከነዚህም 23 የባችለር ኦፍ ኢጁኬሽን፣ 33 የማስተርስ ኦፍ ኢጁኬሽን፣ ወደ 19 የሚጠጉት ደግሞ የሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች መሆናቸውን ዶ/ር አለባቸው አስረድተዋል፡፡
ሴኔቱ በቀረቡለት ፕሮግራሞች ላይ ሰፊና ገንቢ ውይይት በማድረግ እንደገና መሻሻል ያለባቸውን የማሻሻያ ሃሳብ በማቅረብ የአካዳሚክ ፕሮግራሞቹን አጽድቋል፡፡

- የህዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

#Kotebe_University_ofEducation_committed_to_excellence_in_Education

ለተጨማሪ መረጃ ይፋዊ ገጾችችንን ይከታተሉ:
Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.et
Website: https://www.kue.edu.et/
YouTube: https://youtube.com/@kueducation
Facebook (https://web.facebook.com/www.kue.edu.et)
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

Показано 19 последних публикаций.