ጓደኝነት
አመለካከታችሁ የምትመርጡትን ጓደኛ ይወስናል አብራችሁ የምትከርሙት ሰውም በተራው አመለካከታችሁን የመወሰን ሀይል ስላለው ወደ ሕይወታችሁ እንዲገቡ የምትፈቅዱላቸውን ሰዎች በጥንቃቄ ምረጡ እንዴት ካላችሁኝ፦
-በልዩነት ውስጥ ያለውን ጥልቅ ውበት ሳንክድ አመለካከትና መርህን አስመልከቶ ግን ተመሳሳይነት ያላቸው ሰዎች መቅረብ ፈሬያማ ያደርጋልና ከእናንተ ጋር ተቀራራቢ አመለካከት ያላቸውን ሰዎች ወዳጅ አድርጉ።
- ስለ ስኬታችሁ ወዳጆቻችሁ ስለመደሰታቸው እርግጠኛ ሁኑ ሲሳካላችሁ ሃሳብ የማይሰጧቹ ከሆነ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ጓደኝነትን ለመጀመርም ሆነ ጓደኝነቱን ስለማስቀጠላችሁ ጉዳይ ደግማችሁ አስቡበት ጥሩ ጓደኞች ለሃዘናችሁ የሚያዝኑላችሁ ብቻ ሳይሆኑ ለደስታችሁ ከእናንተ በላይ የሚደሰቱላችሁ ናቸው ለማዘንማ ማንም መንገደኛ ታሪካቹን ሰምቶ ሊያዝንላችሁ ከንፈር ሊመጥላቹ የአይዞን ጋጋታ ሊያወርድባችሁ ይቻላል ለደስታችሁ የሚደሰትላችሁ ሰው ግን የሚወዳችሁ ለእናንተ ቦታ ያለው ሰው ነውና ይሄንንም አስቡበት።
- ነገሮች መልካቸውን ሲቀይሩ አብረው የሚቀየሩ ሰዎች ከእናንተ ከሚያገኙት ጥቅም አንፃር ብቻ የቀረቧቹ ከእናንተ የሚያገኙት ጥቅም እስካልተቋረጠ ድረስ ብቻ ነው ከእናንተ ጋር ወዳጅ የሚሆኑት የለመዱትን ነገር ሲያጡ ከነመፈጠራችሁ ስለሚረሷችሁ እንደዚህ አይነት ወዳጅነት አይበጃችሁምና ያላችሁን ግንኙነት በሚገባ ፈትሹ።
-ሌላው ደግሞ እናንተ መስማት የማትፈልጉትን ነገር የሚነግሯችሁን ሰዎች ምረጡ ምን ማለት መሰላችሁ እውነተኛ ወዳጅ እየወደዳችሁ እያከበራችሁ ቢያማችሁም በጊዜው እናንተ መስማት የማትፈልጉትን እውነት የሚነግር ነው ከስሜታችሁ አሊያም እናንተ መስማት ከምትፈልጉት ነገር ላይ ተነስተው ሳይሆን በነገሩ ትክክለኝነትና ሀቅነት ላይ በመመስረት ነው ገንቢ ትችት የሚያቀርቡላችሁ እነዚህ ሰዎች የምርም የሰው መስታወት ናቸውና ሕይወታችሁ ውስጥ አቆዩአቸው።
-ሌላው የሚበጃችሁ ጓደኛ በእናንተ ሕይወት ውስጥ መብተኝነት የሚሰማው አይደለም እንደፈለገ ሊነዳችሁ አይቃጣውም በሕይወታችሁ ውስጥ እስከፈቀዳችሁለት ድረስ ብቻ የሚገባ ነፃነታችሁን የሚጠብቅ ነው።
ስለዚህ የምትጓደኑትን በሚገባ እወቁ በአንድ ወቅት ጨውና ውሃ ተገናኝተው ይተዋወቃሉ ጨው ቀደም ብላ "ማነሽ" ትላታለች ውሃም "እኔ ውሃ ነኝ" አለቻት ጨውም አስከትላ ውሃ የሚባል ስም እስካሁን ሰምቼ አላውቅም ስትላት ውሃም ቀበል አድርጋ ግቢና እንተዋወቅ ትላታለች ጨውም ከገባች በውኋላ "አሁን ማን እንደሆንሽ አወኩ "አለቻት ይባላል አያችሁ ክፉ ባልንጀራም እንዲሁ ነው መልካሙን አመላችሁን ሳታውቁት የሚያስጥላችሁ መልካም ጓደኛም እንዲሁ መልካም ነገርን ሕይወታችሁ ላይ መልካም ነገር ስለሚያደርግ ጥንቃቄ አድርጉ።