አንቺ ካለሽበት
አንቺ ካለሽበት ቢሆን ምንም ቦታ
ፂሆን ይሆናል የፍቅር ገለታ
አንቺ ካለሽበት ሲኦልም ይደላል
እድልም ይቀናል በርባኖስ ይበራል
ምንም ቢያስፈራ የትኛውም ስፍራ
አንቺ ካለሽበት ነው እንደተራ
ሊማሊሞን ቢወጡ ወደታች ቢወርዱ
ሰማዩ ባይጠራ በጉም ቢጋረዱ
አንቺ ካለሽበትበውሃ እንደመፍሰስ
ገደላ ገደሉም ያሰኛል የደስ ደስ
አንቺ ካለሽበት መቃብር ይሞቃል
ሞትም ይቀልና ሞቶ ይሳቀቃል
አንቺ ካለሽበት ምድርም ራማ ናት
ወይም ሬማ አልያም ፀባኦት
አንቺ ካለሽበት የበረዶ ግግር
ለመላፋት ቢሆን ይመቻል ለፍቅር
አንቺ ካለሽበት ኤርታሌን ቢዋኙት
ይልቁን ይበርዳል ፍቅርን ቢቀኙት
አንቺ ካለሽበት ልቤም ይጠብሻል
ለቤም እንዲሰፋ ልብ ይገዛልሻል
✍️✍️✍️✍️✍️ገጣሚ አቤል(ያኖስ)
https://t.me/legtm_tm
አንቺ ካለሽበት ቢሆን ምንም ቦታ
ፂሆን ይሆናል የፍቅር ገለታ
አንቺ ካለሽበት ሲኦልም ይደላል
እድልም ይቀናል በርባኖስ ይበራል
ምንም ቢያስፈራ የትኛውም ስፍራ
አንቺ ካለሽበት ነው እንደተራ
ሊማሊሞን ቢወጡ ወደታች ቢወርዱ
ሰማዩ ባይጠራ በጉም ቢጋረዱ
አንቺ ካለሽበትበውሃ እንደመፍሰስ
ገደላ ገደሉም ያሰኛል የደስ ደስ
አንቺ ካለሽበት መቃብር ይሞቃል
ሞትም ይቀልና ሞቶ ይሳቀቃል
አንቺ ካለሽበት ምድርም ራማ ናት
ወይም ሬማ አልያም ፀባኦት
አንቺ ካለሽበት የበረዶ ግግር
ለመላፋት ቢሆን ይመቻል ለፍቅር
አንቺ ካለሽበት ኤርታሌን ቢዋኙት
ይልቁን ይበርዳል ፍቅርን ቢቀኙት
አንቺ ካለሽበት ልቤም ይጠብሻል
ለቤም እንዲሰፋ ልብ ይገዛልሻል
✍️✍️✍️✍️✍️ገጣሚ አቤል(ያኖስ)
https://t.me/legtm_tm