Репост из: ከመፅሐፍ ገፅ ®
ያወቅነው ግን ያላወቅነው!
===============
- አንድ ሰው ከብዙ ዓመታት በኋላ ከቀድሞ የትምህርት ቤት ጓደኛው ጋር በመንገድ ይገጣጠማል፣ ለማመን እስኪያዳግተው ድረስ ጓደኛው አዲስና የቅርብ ሞዴል የሆነች መኪና እንደያዘ ይመለከታል። ታዲያ ወደቤት ሲመለስ ፊቱ በሃዘን ተሞልቶ ይተክዝና ያዝን ጀመር። እርሱ ወደ ኋላ እንደቀረ/እንደከሰረ አስቧልና። ይሁንና ያላወቀው ነገር ቢኖር፥ ጓደኛው የመኪና ሾፌር ሲሆን፣ ለመስክ ሥራ በአለቃው መኪና መላኩን ነው።
*
- ሮዛ ሁልጊዜም ፍቅር አትሰጠኝም/አታቀማጥለኝም/ በሚል ሰበብ ከባለቤቷ ጋር ትጋጫለች። ይኸውም፤ በመኪና ካደረሳት በኋላ እንደጓደኛዋ ሄለን ባል ከመኪና ወርዶ፡ ዞሮ፡ በር ከፍቶ እርሷን አለማውረዱን እንደምክንያት ታነሳለች። ሮዝ ያላወቀችው ነገር፡ የነሄለን መኪና፡ የፊት በሩ ላይ ብልሽት ስላለው ከውጪ ካልሆነ በስተቀር ከውስጥ መከፈት አለመቻሉን ነው።
*
- አንዲት ሴት ከረጅም ጊዜ ቆይታ በኋላ፣ የብዙ አመት ጓደኛዋን ልትጎበኝ በሄደችበት፡ ሶስት የሚያማምሩና ለዓይን የሚያሳሱ ልጆች ሲቦርቁ ዐይታ ስሜቷ ይረበሻል። የመጀመሪያ ልጇን ከወለደች በኋላ ለረጅም አመታት ሌላ ልጅ ለማርገዝ ብትጥርም ሳይሳካ /እየጨነገፈ/ ቀርቷልና። ይሁን እንጂ ያላወቀችው ነገር፡ የጓደኛዋ ልጅ በካንሰር በመያዙ መኖር የሚችለው ለአንድ አመት ብቻ ሲሆን ቀሪዎቹ ሁለቱ ልጆች ደግሞ የማደጎ ልጆች ናቸው።
* * *
ህይወት ሁሉንም አንድ ዓይነት በሆነ መንገድ የምታስተናግድ መድረክ አይደለችም። ካወቅነው ይልቅ የማናውቀው ብዙ ነው። ዐይነቱና መጠኑ ይለያይ እንጂ ሁሉም ሰው የራሱ ጉድለት አለው። ይሁንና ደስታ የምርጫ ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም ሰው ግን በህይወቱ ደስተኛ አይደለም።
ይኸውልህ፤ ኤሊ ምን ዓይነት ሸክም እንደተሸከመች ካወቅክ ለምን በጥንቃቄ እንደምትራመድ አትጠይቅም። ከሚታየው ምቾት ባሻገር የማይታዩ ብዙ ሸክሞች፣ ከሚማርኩ ፈገግታዎች ጀርባ ብዙ የልብ ቁስልና ህመሞች እንዳሉ እወቅ። ከሩቅ ያማረ ኑሮ ሁሉ የስኬት ምልክት፣ ከውጭ የሚታይ አንጸባራቂ ነገር ሁሉ ወርቅ አይደለምና። ስለዚህ ያወቅነው 'ደስታውን' ሲሆን ያላወቅነው ደግሞ 'ጉድለቱን/ችግሩንና ድካሙን/' ነው።
"ለምን እኔ ብቻ?" እያልክ ትጠይቅ ይሆን?
እኩዮቼ አግብተዋል።
እኩዮቼ ልጆች አፍርተዋል።
እኩዮቼ ጥሩ ሥራ ይዘዋል።
እኩዮቼ ስኬት ተጎናጽፈዋል።
እኩዮቼ ውድ ቤትና መኪና አሏቸው።
እኩዮቼ በማኅበረሰቡ የተከበሩ ናቸው።
እኩዮቼ እንዲህ ናቸው፤ እንዲያ ናቸው...!!!
ትክክል ብለሃል። ይሁንና ይህንን ጨርሰህ መርሳትህ ያሳፍራል...
እኩዮችህ ሆነው በህይወት የሌሉትን።
እኩዮችህ ሆነው በህመም የሚሰቃዩትን።
እኩዮችህ ሆነው በአእምሮ መታወክ በማህበረሰቡ እንደ እብድ የተቆጠሩትን።
እኩዮችህ ሆነው መንገድ ዳር የሚያድሩትን።
እኩዮችህ ሆነው ወላጅ አልባ የሆኑትን።
እኩዮችህ ሆነው የለት ጉርስ ያጡትን።
እኩዮችህ ሆነው አንተ የምትኖረውን ኑሮ የሚናፍቁና ባንተ ህይወት የሚቀኑ መሰል የሰው ዘርን...ረስተሃል።
ምናልባት የምትፈልገው ስፍራ ላይ አልተቀመጥክ ወይንም የምትመኘውን ነገር አላገኘህ ይሆናል፡ ይሁን እንጂ ከብዙዎች በላይ ደስተኛ ነህ። ስለዚህም ፈጣሪህን ባለህ ነገር አመስግን።
አንተ ለብቻህ የሆነብህ ነገር የለም። አንተ ጋር የጎደለህን ሌላው ጋር ስታይ 'ሁሉ የሞላለት' መስሎህ ነው። ባወቅኸው ልክ የሰውን ህይወት አትመዝን፣ የራስህንም አታቃል። ያወቅክ የመሰለህ ያላወቅኸው ብዙ አለና። ስለዚህ በምንም አይነት የህይወት ትግል ውስጥ ብትሆን ደስታን ምርጫህ አድርግ። ሰላምንም ውደዳት። ሁልጊዜም በፈጣሪህ ደስ ይበልህ!
Credit Samuel geda
http://t.me/ewuketmad