ማኅበረ መድኀኔዓለም መዝሙር ጥናት


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


✝️ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮን ስርዓትን የጠበቁ መዝሙሮች እና ግጥሞችን ከነዜማቸው እንለቃለን ✝️
🙏🙏🙏 (መዝሙር ጥናት) 🙏🙏🙏

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций




ናና አማኑኤል

ናና አማኑኤል ና መድኃኒቴ
ጽድቅህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ /2/
ናና አማኑኤል ና መድኀኒቴ
ፍቅርህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ /2/
አዝ

የምሕረት አባት     አማኑኤል
የቸርነት ጌታ          ''
ፊትህ የተመላ        ''
ሁሌ በይቅርታ        ''
ካለው ፍቅር በላይ  ''
አባት ለአንድ ልጁ   ''
አምላክ ይወደናል      ''
አይጥለንም ከእጁ     ''
አዝ

መድኃኒቴ ልበል        አማኑኤል
ድኛለው በሞትህ         ''
ቁስሌ ተፈውሷል         ''
በቁስልህ በሞትህ        ''
ስሸጥህ አቀፍከኝ         ''
ስወጋህ አይኔ በራ         ''
በፍቅርህ አወጣኽኝ       ''
ከዚያ ከመከራ               ''
አዝ

አንተ ከኔ ጋር ነህ          አማኑኤል
አዎ ከኔ ጋራ                    ''
ድል አርገህልኛል             ''
የጭንቄን ተራራ               ''
በጉባኤ መሀል                ''
አፌ አንተን አወጀ             ''
የከበረ ደምህ                 ''
ነፍሴን ስለዋጀ                ''
አዝ

የድንግሏ ፍሬ                አማኑኤል
የበላቴናዋ                       ''
የቤቴ ምሰሶ                     ''
የነፍሴ ቤዛዋ                    ''
መሠረቴ አንተ ነህ              ''
ያሳደገኝ እጅህ                  ''
አተወኝም አንተ                  ''
ስለሆንኩኝ ልጅህ               ''

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አድርሱ
@mahberemedhaniyalem


✞ #ታህሳስ_ወር_የንግስ_በዓላት ✞

ማክሰኞ ታህሳስ 1 - የነብዩ ኤልያስ ልደቱ - በእንጦጦ እና በጎፋ ገብርኤል

ሐሙስ ታህሳስ 3 - ባዕታ ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ቀን
                      -ቅዱስ ፋኑኤል - በዓለም ባንክ
      
                      -ዜና ማርቆስ - በጣፎ

እሁድ ታህሳስ 6 - ቅድስት አርሴማ ቅዳሴ ቤቷ - የቅድስት አርሴማ ታቦት ባለበት

ማክሰኞ ታህሳስ 8 - አባ ኪሮስ ልደታቸው - አለምባንክ ጀሞ ተራራ መድኃኔዓለም ቤ/ክ - በጣፎ

ረቡዕ 9 - እስትንፋሰ ክርስቶስ ልደታቸው - በቦሌ ቡልቡላ ዋሻ ተክለሃይማኖት

አርብ 11 - ቅዱስ ያሬድ - ጎተራ አጎና ሲኒማ ፊት ለፊት

ቅዳሜ ታህሳስ 12 - አባ ሳሙኤል እረፍታቸው - በአቃቂ አባ ሳሙኤል ቤተ ደናግል ገዳም ፣ በቦሌ ቡልቡላ አባ ሳሙኤል እና በሲኤሚሲ ሚካኤል

እሁድ ታህሳስ 13 - ቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱ - በሸጎሌ

ረቡዕ ታህሳስ 16 - ፍቅርተ ክርስቶስ ቃልኪዳን የተቀበለችበት እለት - በአንቆርጫ መድኃኔዓለም ከፈርንሳይ ጉራራ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ጋር ባጃጅ እና ታክሲ አለ የአንቆርጫ

ቅዳሜ ታህሳስ 19 - ቅዱስ ገብርኤል - ሶስቱን ህፃናት ያዳነበት

ማክሰኞ ታህሳስ 22 - ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እደምትወልድ ያበሰረበት - በብስራተ ገብርኤል

ሐሙስ ታህሳስ 24 - አቡነ ተክለሃይማኖት - ልደታቸው

ሰኞ ታህሳስ 28 - ቅዱስ አማኑኤል - የልደቱ መታሰቢያ - በመሳለሚያ

ማክሰኞ ታህሳስ 29 - ባለወልድ - የኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱ መታሰቢያ በዓል - በ4 ኪሎ ባለወልድ ቤተክርስቲያን - በለቡ መብራት አብርሃም ገዳም

✞ መምጣት የማትችሉ #Share በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ ✞

         ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


ማክሰኞ ህዳር 24 - ሃያራቱ ካህናተ ሰማይ(ሱራፌል) - በቦሌ ጎርጎርዮስ ቤተክርስቲያን

                      - አቡነ ተክለሃይማኖት - 25ተኛ ሆነው የሥላሴ መንበር ያጠኑበት መታሰቢያ ዕለት

ረቡዕ ህዳር 25 - ቅዱስ መርቆሬዎስ - በዓለ እረፍቱ - በደብረ አባይ ቅድስት አርሴማ - በጎፋ መብራት ሀይል ቅዱስ መርቆርዮስ ቤተክርስቲያን

- በካሳንቺስ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን

- በአዲሱ ገበያ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን

ሐሙስ ህዳር 26 - አቡነ ሃብተማርያም - በዓለ እረፍታቸው

እሁድ ህዳር 29 - አቡነ እጨጌ ዮሐንስ - በዓለ ልደታቸው - በወይራ ሰፈር

✞ መምጣት የማትችሉ #Share በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ ✞


ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን

ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን /2/
ውስተ አፍላገ ባቢሎን
ኅየ ነበርነ ወበከይነ
እንዚራቲነ ሰቀልነ ውስተ ኲሓቲሃ
ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን /2/
በባቢሎን ወንዞች አጠገብ
ተቀምጠን አለቀስን
መሰንቆአችንን ሰቀልን በዛፎቿ ላይ
አዝ

ፅኑ መከራን ተቀበልን ተጨነቅን በፈተና
የደዌ ሞት በላያችን እንደዝናብ ወርዷልና
አሕዛብም ዘበቱብን እንዲህ ብለው በየተራ
ዘምሩለት ለአምላካችሁ ቢያድናችሁ ከመከራ
እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
አዝ

የማረኩን በጦራቸው በኃይላቸው የተመኩ
በጽዮን ደጅ ያለፍርሃት የጽዮንን ክብሯን ነኩ
ይህን ያየ ከላይ ሆኖ በደመና ተሸፍኖ
ባቢሎንን አሻገረ የማረኩንን በትኖ
እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
አዝ

ስጋችንን ሊገንዘን የሞት ጥላ ቢያጠላም
እናልፋለን ሁሉን ባንቺ
የአምላክ እናት ድንግል ማርያም
ቅድስት ሆይ ከባረክሽን
እንድናለን ከደዌያችን
ለስጋና ለነብሳችን መድኃኒት ነሽ እናታችን
እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግስቱ መርጧታልና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታልና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን

መጋቤ ምሥጢር ሰሎሞን ተስፋዬ
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem


ደስ ይበለን

ደስ ይበለን /2/
አምላክ አለ መሀላችን
ምን ይከፈል ለዚህ ሥራህ
ገናና ነው አምላክ ክብርህ
አዝ

ምሕረቱን አይተናልና
አድርሶናል አምላክ በጤና
ይህችን እድሜ የጨመረልን
ለንስሐ ጊዜ የሰጠን
አዝ

ኃጢአትህን ይታገስሃል
በቸርነት አምላክ ያይሃል
ደስታ ነው በሰማያት
በአንድ ኀጥእ የጽድቅ ሕይወት
አዝ

እልል በሉ የጎበኛችሁ
በምሕረት አምላክ ያያችሁ
በችግር ቀን ያሰበን ሁሉ
አመስግኑ ዝምም አትበሉ
አዝ

ድንግል ማርያም ትጸልያለች
ኃጥኡን ሰው ማረው እያለች
በድንግል ክብር እንኖራለን
በጽኑ ፍቅር አንድ እንዲያደርገን

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አድርሱ
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem


የመላእክት አለቃ   

የመላእክት አለቃ ገብርኤል ላከው
ኃያሉ እግዚአብሔር በሰማያት ያለው
የባህርይ ልጄ ወዳንቺ ይመጣል
ብለህ ለጽዮን ልጅ ንገራት ለድንግል
አዝ

ኃይለ ልዑል ወልድም ስጋሽን ይለብሳል
በተለየ አካሉ ወደ አንቺ ይመጣል
ከስጋሽም ስጋን ከነፍስሽም ነፍስ ነስቶ ይዋሃዳል
በገጸ ህጻናት ከአንቺ ይወለዳል
አዝ

ደንቆሮ ሊሰማ ዲዶች ሊናገሩ
በጌታ ታምራት  ዕውራን ሊበሩ
ሙታን ይነሱ ዘንድ በማህጸንሽ ፍሬ
ከእግዚአብሔር ወደ አንቺ ተልኬያለሁ ዛሬ
አዝ

ደስ አሰኛት አለው በልዩ ሰላምታ
ሀሴት እንድታደርግ ምሥራቹን ሰምታ
ድዳ እንዳደረከው ካህን ዘካሪያስን
እንዳታሳዝናት ከእርሷ ጋር ስትደርስ
አዝ

ገብርኤል በደስታ ምሥራቹን ይዞ
ከሰማይ ወረደ በአምላኩ ታዞ
በሊባኖስ መንደር እስኪሰማ ድረስ
ክንፉን እያማታ መጣ ሲገሰግስ
አዝ

ደስ ይበልሽ አላት እየተሳለማት
ሀርን ከወርቅ ጋር ስትፈትል አገኝቷት
እውነተኛው ንጉስ ከአንች ይወለዳል
ለአንች ፍቅርና አንድነት ይገባል

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem


ይኸው ተወለደ

ይኸው ተወለደ የዓለም መድኀኒት /3/
እሰይ ተወለደ የዓለም መድኀኒት /3/
አዝ

ትንቢት ተናገሩ ነቢያቱ ሁሉ /3/
አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ /3/
አዝ

ሰብአ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ /3/
የእስራኤል ንጉሥ ተወልዷል እያሉ /3/
አዝ

ሰብአ ሰገል መጡ እጅ መንሻ ይዘው /3/
ወርቅ ዕጣን ከርቤውን ገበሩለት ሰግደው /3/
አዝ

ምዕመናን እንሂድ ከልደቱ ቤት /3/
ውኃው ሆኗልና ማርና ወተት /3/
አዝ

በሶርያ ታየ ፈጣሪ እንደ እንግዳ /3/
ብሥራተ ልደቱን ለሁሉ ሊያስረዳ /3/

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem




✞ #የህዳር_ወር_የንግስ_በዓላት ✞

እሁድ ህዳር 1 - ዕንቁ ልደታ - ቅዳሴ ቤቷ - ቀበና በኮከበ ጽዕባ ትምህርት ቤት አጠገብ ባለው ቅያስ(ኮብል) ወደ ላይ መውጣት

ማክሰኞ ህዳር 3 - በዓታ ማርያም (ዘንዶ አስራ) - ቅዳሴ ቤቷ - ቦሌ አራብሳ

አርብ ህዳር 6 - ቁስቋም ማርያም - ወደ ደብረ ቁስቋም የገቡበት መታሰቢያ ዕለት

ቅዳሜ ህዳር 7 - ቅዱስ ጊዮርጊስ - ቅዳሴ ቤቱ

እሁድ ህዳር 8 - አርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል ) - በ4 ኪሎ ባለወልድ ቤተክርስቲያን

                    - በጣፎ አባ ኪሮስ ቤተክርስቲያን

- ቶታል ሥላሴ - ምርቃት

ረቡዕ ህዳር 11 - ቅድስት ሐና - በዓለ እረፍቷ

ሐሙስ ህዳር 12 - ቅዱስ ሚካኤል - በዓለ ሲመት

አርብ ህዳር 13 - እግዚአብሔር አብ - እልፍ አእላፍ መላእክት የተሾሙት

እሁድ ህዳር 15 - ቅዱስ ሚናስ - በዓለ እረፍቱ - በድሬ ዳሌ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን

ቅዳሜ ህዳር 21 - ፂዮን ማርያም

እሁድ ህዳር 22 - ፉሪ ቅዱስ ዑራኤል - ቅዳሴ ቤቱ - በሀይሌ ጋርመንት ወደ ገላን በሚወስደው መንገድ ሰፈራን አለፍ እንዳሉ

ማክሰኞ ህዳር 24 - ሃያራቱ ካህናተ ሰማይ(ሱራፌል) - በቦሌ ጎርጎርዮስ ቤተክርስቲያን

                      - አቡነ ተክለሃይማኖት - 25ተኛ ሆነው የሥላሴ መንበር ያጠኑበት መታሰቢያ ዕለት

ረቡዕ ህዳር 25 - ቅዱስ መርቆሬዎስ - በዓለ እረፍቱ - በደብረ አባይ ቅድስት አርሴማ - በጎፋ መብራት ሀይል ቅዱስ መርቆርዮስ ቤተክርስቲያን

- በካሳንቺስ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን

- በአዲሱ ገበያ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን

ሐሙስ ህዳር 26 - አቡነ ሃብተማርያም - በዓለ እረፍታቸው

እሁድ ህዳር 29 - አቡነ እጨጌ ዮሐንስ - በዓለ ልደታቸው - በወይራ ሰፈር

✞ መምጣት የማትችሉ #Share በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ ✞

         ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


❖ አዘክሪ ድንግል አዘክሪ ❖

አዘክሪ ድንግል አዘክሪ
ለልጅሽ አሳስቢ አዘክሪ
ለሐጥዓን አኮ ለጻድቃን /2/


ከአንቺ መወለዱን----------አዘክሪ
በቤተልሔም---------------አዘክሪ
በጨርቅ መጠቅለሉን------አዘክሪ
መኝታው ግርግም----------አዘክሪ
ለሐጥዓን አኮ ለጻድቃን

/አዝ=====

በዚያ በብርድ ወራት------አዘክሪ
የገበሩለትን----------------አዘክሪ
የአድግ እና የላም----------አዘክሪ
እስትንፋሣቸውን-----------አዘክሪ
ለሐጥዓን አኮ ለጻድቃን

/አዝ=====

በግብጽ በረሐ---------አዘክሪ
መሰደድሽን------------አዘክሪ
የአሸዋውን ግለት------አዘክሪ
ርሐቡ እና ጥሙን------አዘክሪ
ለሐጥዓን አኮ ለጻድቃን

/አዝ=====

በመቃብሩ ዘንድ-------አዘክሪ
በዓነባሽው ዕንባ--------አዘክሪ
አሳስቢ ድንግል ሆይ----አዘክሪ
ገነት እንድገባ-----------አዘክሪ
ለሐጥዓን አኮ ለጻድቃን

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
።።።🙏🙏🙏።።


ለምኚ ድንግል

ለምኚ ድንግል ለምኚ (፪)
ለኃጥአን (፫) አይደለም ለጻድቃን

ለምኚ - - - ታላቅ ስጦታዬ
ለምኚ - - - አዛኝ ሩኅሩኅ ነሽ
ለምኚ - - - የጌታዬ እናት
ለምኚ - - - ጸጋን የተመላሽ
ለምኚ - - - የአምላክ ማደሪያ
ለምኚ - - - ለምነሽ አስምሪኝ
ለምኚ - - - አማናዊት ጽዮን
ለምኚ - - - ከእኔ አትለይኝ

ለምኚ - - - ሀዘንሽ ሀዘኔ
ለምኚ - - - ለእኔ ይሁን ድንግል
ለምኚ - - - የተንከራተትሽው
ለምኚ - - - በሀገረ እስራኤል
ለምኚ - - - ትግስትሽን ሳየው
ለምኚ - - - ልቤ ይመሰጣል
ለምኚ - - - የሀዘን እምባ ጎርፍ
ለምኚ - - - አይኔን ይሞላዋል


ለምኚ - - - በቀራንዮ አምባ
ለምኚ - - - በእዛ የፍቅር ቦታ
ለምኚ - - - እግረ መስቀሉ ስር
ለምኚ - - - ከክርስቶስ ጋራ
ለምኚ - - - ለእኛ ተሰጥተሻል
ለምኚ - - - እናት እንድትሆኝን
ለምኚ - - - ልጆችሽ ነንና
ለምኚ - - - ምልጃሽ አይለየን


ለምኚ - - - አንደበቴን ጌታ
ለምኚ - - - በምስጋና ምላው
ለምኚ - - - ደስ ይበልሽ ብዬ
ለምኚ - - - እኔም ላመስግናት

🙏🙏🙏
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem


የጥቅምት ወር አመታዊ በዓላት

ሰኞ ጥቅምት 4 - አብርሃ ወአፅብሃ - በመሪ ሃያት ፋኑኤል - በየካ ተራራ ዋሻ ተክለሃይማኖት - በዘነበ ወርቅ አቡነ አረጋዊ

ማክሰኞ ጥቅምት 5 - አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ

ሐሙስ ጥቅምት 7 - ቅድስት ሥላሴ - በቦሌ አራብሳ ዋሻ ሥላሴ

ረቡዕ ጥቅምት 13 - አቡነ ዘርዓ ብሩክ - በአስኮ ቃሉ ተራራ አቡነ ሃብተማርያም

ሐሙስ ጥቅምት 14 - አቡነ አረጋዊ ወ ገብረ ክርስቶስ

እሁድ ጥቅምት 17 - ቅዱስ እስጢፋኖስ

ማክሰኞ ጥቅምት 19 - አቡነ ሐራድንግል - በሃያት ጣፎ ዋሻ ሚካኤል

አርብ ጥቅምት 22 - ቅዱስ ዑራኤል - ኮተቤ

ረቡዕ ጥቅምት 27 - ቸሩ መድኃኔዓለም

ሐሙስ ጥቅምት 28 - ቅዱስ አማኑኤል

ቅዳሜ ጥቅምት 30 - ቅዱስ ማርቆስ - 6 ኪሎ




#ገሊላ_እትዊ

እመቤቴ እሰከ መቼ
በባዕደ ሀገር ትኖርያለሽ /2/
ገሊላ ግቢ/4/ ሐገርሽ ገሊላ ግቢ/2/

ገሊላ እትዊ/4/ ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/

እመቤቴ ማርያም ገሊላ እትዊ
ሰደቱ ይበቃሽል ገሊላ እትዊ
ሄሮድስ ሞቱልብሉ ገሊላ እትዊ
ገብርኤል ነገሮሽል ገሊላ እትዊ
በእሳት ሰርገላ ገሊላ እትዊ
ዑራኤል የምራሻል ገሊላ እትዊ

ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/

የዝናቡ ጌታ ገሊላ እትዊ
እናቱ ሁነሽ ሳለ ገሊላ እትዊ
ሰይጣን በሰው አደሮ ገሊላ እትዊ
እያስከለከለ ገሊላ እትዊ
ውሃ ጥም ፅንቶብሽ ገሊላ እትዊ
አፈሽ ደርቁ ዋል ገሊላ እትዊ
ይብቃል እናቴ ገሊላ እትዊ
ርሀብ ጥማትሽ ገሊላ እትዊ
ሂጅ ወደ ገሊላ ገሊላ እትዊ
ወደ ዘመድችሽ ገሊላ እትዊ

ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/

የሰማዕታት አክሊል ገሊላ እትዊ
የፃድቃን እናት ገሊላ እትዊ
ባርክሽ ሰጠሽቸው ገሊላ እትዊ
መክራን ሰደት ገሊላ እትዊ
እኛም ይታደገን ገሊላ እትዊ
የአንቺው ብረከት ገሊላ እትዊ

ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/

ገፃሽ ብሩህ መልካም ገሊላ እትዊ
ልክ እንደ ፀሐይ ገሊላ እትዊ
እግዚዕትነ ማርያም ገሊላ እትዊ
እሙ ለአዶናይ ገሊላ እትዊ
አይገባም ለአንቺ ገሊላ እትዊ
መክራ ስቃይ ገሊላ እትዊ

ሐገርኪ ገሊላ እትዊ /2/
ገሊላ ግቢ /4/ አገርሽ ገሊላ ግቢ/2/

ዘማሪ
ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ

መዝሙር (ጥናት)
👇👇👇👇👇

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
።።።🙏🙏🙏።።


ከሊባኖስ 2 ከልጅሽ ጋር ነይ
እመ አዶናይ ከሊባኖስ ወደኛ ነይ

ጥበቃሽ ዘወትር      ከሊባኖስ
እዳይለየኝ              ከሊባኖስ
በኤድኩበት ሁሉ     ከሊባኖስ
ማረፊያ ሁኚኝ         ከሊባኖስ

አዝ

እኔን ባርያሽን         ከሊባኖስ
ድንግል አትርሽኝ    ከሊባኖስ
በፅድቅ ሰሌዳ       ከሊባኖስ
ስሜን ፃፊልኝ         ከሊባኖስ

አዝ

ነፍስ እና ስጋዬን     ከሊባኖስ
አደራ እልሻለው     ከሊባኖስ
በልጅሽ ፅኑ ፍቅር  ከሊባኖስ
ተማፅኜሻለዉ       ከሊባኖስ

አዝ

ከመሞቴ በፊት     ከሊባኖስ
ለንስሀ አብቂኝ      ከሊባኖስ
ለነፍሴ ማረፊያ     ከሊባኖስ
አዘጋጅልኝ           ከሊባኖስ

አዝ

ከአንበሶች መኖሪያ  ከሊባኖስ
ከነብሬ ተራራ          ከሊባኖስ
መተሽ አስደስችኝ    ከሊባኖስ
እናቴ ሙሽራ          ከሊባኖስ

አዝ

የልብስሽ መሀዛ     ከሊባኖስ
የሊባኖስ ሽታ        ከሊባኖስ
ሮማን ናርዶስ ነሽ  ከሊባኖስ
እናቱ ለጌታ          ከሊባኖስ

አዝ

እመቤቴ ስልሽ     ከሊባኖስ
ስምሽን ስጠራ    ከሊባኖስ
ፈጥነሽ ድረሽልኝ  ከሊባኖስ
ከቅዱሳን ጋራ     ከሊባኖስ
ፈጥነሽ ድረሽልኝ  ከሊባኖስ
ከሚካኤል ጋራ    ከሊባኖስ
ፈጥነሽ ድረሽልኝ  ከሊባኖስ
ከገብርኤል ጋራ   ከሊባኖስ


✞ #የመስከረም_ወር_የንግስ_በዓላት ✞

ረቡዕ መስከረም 1 - ቅዱስ ራጉኤል

ሐሙስ መስከረም 2 - መጥምቁ ዮሐንስ - በቤተል ማርያም - ቦሌ መድኃኔዓለም እና ዮሐንስ መጥምቁ በአለበት ሁሉ

ሰኞ መስከረም 6 - ቅድስት አርሴማ - በአቃቂ አባ ሳሙኤል ቤተ ደናግል ገዳም

ማክሰኞ መስከረም 7 - ቅድስት ሐና - በኮተቤ ሀና ማርያም እና በፉሪ(ቀለበት ሀና ማርያም)

አርብ መስከረም 10 - ፀደንያ ማርያም - ዘነበ ወርቅ FM ፀደንያ ማርያም - በቡራዩ

ሐሙስ መስከረም 16 - ቅድስት ኪዳነምህረት - በጎፋ ካምፕ

አርብ መስከረም 17 - ቅዱስ እስጢፋኖስ (መስቀል)

ቅዳሜ መስከረም 18 - አቡነ ኤዎስጣቴዎስ - በሰሚት ኮንዶሚኒየም በበዓታ ማርያም ቤተክርስቲያን

ማክሰኞ መስከረም 21 - እመቤታችን

አርብ መስከረም 24 - አቡነ ጎርጎርዮስ - ከቦሌ ሚካኤል አጠገብ

ሰኞ መስከረም 27 - ቸሩ መድኃኔዓለም - ቅዳሴ ቤቱ - በአለም ባንክ - ትሮፒካል

ረቡዕ መስከረም 29 - ቅድስት አርሴማ

✞ መምጣት የማትችሉ #Share በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ ✞

       

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏።።


የንግስ በዓል ጥሪ 🔔

እንኳን ለገናናው መልዐክ ለቅዱስ ሩፋኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ ።

በዓለ ንግሱ በደብራችን በቤተል ጉለሌ ደብረ መድኀኒት መድኀኔዓለም ቤ/ክ በታላቅ ድምቀት ስለሚነግስ እንዳትቀሩ ስትል ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች ።

📍 ነገ እሁድ ጷጉሜ 3

🙏🏼 ቸር ያገናኘን

#SHARE #SHARE #SHARE


ምን ብትወደኝ ነው | ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

🌼 🌼ምን ብትወደኝነው 🌼 🌼

ምን ብትወደኝ ነው ምን ብታስበኝ
አዲስ ዘመንን ቀን ያሳየኸኝ
ኦ አምላኬ ዘመንን ካየሁ ከተሻገርኩኝ
ኦ ጌታዬ እዘምራለሁ ስቡህ እያልኩኝ/2/

ጠዋትም የለኝ ካንተ በቀር ማለዳዬ ነህ ማምሻዬም አንተ አልሻገርም አንተ ካልፈቀድህ ማዕበል ወጀቡን አሳልፈህ ጨለማውን አብርተህ በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/

             /አዝ 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼

አልፍ እንድትሆን አንተ የባረካት ከመሬት ወድቃ ትላንትናዬን ወዜን ባርከኸው ለዚህ ብበቃ ባጌጠችው የምድር መሀል ሆኜ እቀኛለሁ ስለአዳኜ በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/

              /አዝ 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼

ፍሬ ፈልገህ መጣህ ወደኔ በብርሀን ጸዳል      ፀሐይ አውጥተህ ልትባርከው ጌታ ፈቅደሀል ያንተ ወንዞች ውሃ ከተሞሉ
ተራራዎችም ምስጋናህን ያመጣሉ
በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና
ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/

             /አዝ 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼

ማለፍ በክንድህ አዲስ ዘመንን ላንተ መዋጀት ግዛው ዘመኔን ውረስ አምላኬ የኔን ማንነት አዝማናቱ ስራህን እያሳየ ልሁንልህ
ከዓለም የተለየ በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/

             /አዝ 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼

ቀንን ብቆጥር ዘመን ባሰላ ካልተለወጥኩኝ ከጸጋህ ዙፋን በዕምነት ቀርቤ ካልተፈወስኩኝ ምን ሊረባኝ ካንተ ጋር ካላረጀሁ
ያለቃልህ በዘመን እንዲያው ባውጀው
በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና
ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/


ዘመን ተሠጠን ዘመን በፍቅሩ ሁሉን አልፈን
ዘመን መጣልን ዘመን አንድ ሆነን ልንቆም ታርቀን

የአክሱም የላሊበላ ታሪክ ሊደገም
በፍቅር በልጆቿ ላብ ቁስሏ ሊታከም
ሊደምቅ ዳግም ሊነሣ የኢትዮጵያ ስም /2/
የአምላክ ገፀ በረከት ጊዮን ከቧታል
ስሟን ታሪኳን ሊያድስ ህዝቧ ተነስቷል
ህልሟ በአምላክ ቸርነት በርግጥ ይሆናል /2/

ኢዮሐ ልክ እንዳደዪ /የፈካ ዘመን/2
ክረምቱ ጭጋጉን ገፎ ብርሀን ላሣየን
ኢዮሐ ችቦ ይለኮስ /ይቁም ደመራ/2
እልልታ ዝማሬ ይሁን ለጆቹ ስራ /2/

አዝ----

እጇን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች
በሩቅ ያሉ ልጆቿን አደራ እያለች
አይቀር ቀርቧል ዘመኑ ቀና ትላለች /2/
የፀብ የልዩነቱ ዘመን ይብቃና
በፍቅር ለለውጥ እንገስግስ ባዲስ ጎዳና
ዘመን የጨመረልን ለዚነውና /2/
ኢዮሐ አደይ አበባ /አደይ ኢትዮጵያ/2
መጣልሽ አውደ አመትሽ ነው በዪ ሀሌሉያ
ኢዮሐ ግቢ አዲስ ኪዳን /አዲስ መሐላ/2
በልፅጊ ይነቀልልሽ የችግር ጥላ /2/

እግዚአብሔር ይባርክልን /2/
አመቱን ይባርክልን "" ""
ዘመኑን ይዋጅልን "" ""
በስደት በሩቅ ያሉትን "" ""
በፍቅሩ ይሰብስብልን "" ""
በህመም የተያዙትን "" ""
በምህረት ያስብልን "" ""

ይባርክልን ይባርክልን
የንሰሐ አመት ይሁንልን
ይባርክልን ይባርክልን
የእርቅ ዘመን ይሁንልን
የሰላም አመት የብልፅግና
በረከት ይፍሰስ ይብዛልን ጤና
የፀቡ ምቸት ከሐገር ይውጣና
የፍቅር ምቸት ይግባ እንደገና
ያድርሰን ጌታ ደሞ ለአመቱ
ይሔኛው አልፎ በቸርነቱ

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
።።።🙏🙏🙏።።

Показано 20 последних публикаций.