'' ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ''
'' ኢየሱስም፡— ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።''
- ማርቆስ 10:18 -
ይህንን ቃል የተናገረው ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። አንዳንድ ወገኖች ይህንን ቃል በመጥቀስ ኢየሱስ ክርስቶስ ቸር አይደለም ፤ ቸር እግዚአብሔር ብቻ ነው ፥ ስለዚህ እርሱ እግዚአብሔር አይደለም ( ሎቱ ስብሐት) ይላሉ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ቸር እግዚአብሔር እንደሆነ ምንም ጥርጥርም የለው። እንኳን ጌታችን፤ ብዙ ሰዎችም ሳይቀር ቸር ተብለዋል...እኛ ቸሮች እንድንሆንም ታዘናል።
🌿 '' ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤'' (መዝ 17:25)
🌿 '' ቸር ሰው ይራራል ያበድራልም፥ በፍርድም ነገሩን ይፈጽማል።'' ( መዝ 110:5)
🙌 የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ሰው እንኳ ከሚሰራው ሥራ አንዱ የቸርነት ሥራ ነው።
'' የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፣'' (ገላ 5:22)
እንዲህ ከሆነ የጌታችን ንግግር እንዴት ይታያል?
ጌታችን ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር
አምላክ ነውና በሰዎች ልቡና ያለውን ተንኮልና ቀናነት በራሱ ስለሚያውቅ ( ዮሐ 1፡49 ፣ ዮሐ 4፡18 ) የዚህንም ሰው የልቡን ሐሳብ አወቀ። ይህ ሰው በልቡ የኢየሱስን እግዚአብሔርነት ሳያምን እንዲሁ በአፉ #ቸር_መምህር-ሆይ ብሎ የተጠራው። ጌታችንም ከእግዚአብሔር በቀር ሰው በባሕርዩ ቸር ሊባል አይገባውም አለው ( ቅዱሳን ቸር ቢባሉ በጸጋ ነውና)
ጌታችንን ቸር ያለው ሰው እርሱ ክርስቶስ እግዚአብሔር አምላክ እንደሆነ ሳያውቅ - ሳያምን ነበርና እንዲሁ ቸር ብሎ የጠራው።
ስለዚህ አምላክነቴን እግዚአብሔርነቴን ሳታውቅ ሳትረዳ ስለምን ቸር ትለኛለህ? አምላክነቴን ተረድተህ ቸር በለኝ። ከእግዚአብሔር( ከእኔ) በቀር ቸር ማንም የለምና ማለቱ ነው።
👏 ኢየሱስ ቸር እንደሆነ
'' የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ።'' (2 ቆሮ 8:9)