አይኔ ቢጠፋ ምንም ማየት ቢሳነኝም አልጠራጠርም እሷን ለማየቴ፣👁️👁️
ጥርሷ ድርብርብ ነው አንዴ ፈገግ ስትል የሚስቅ ሁለቴ፣
የምድር መከራ ሲበዛባት እንኳን ሁሉ ያልፋል እያለች፣
በአንዱ ጥርስ አልቅሳ በአንዱ ትስቃለች፣
እኔ አይቻለሁ ትርፍ አለሽ ይሏታል፣
ኧረ ትርፍ የለኝም ሁል ጊዜ መልሷ ነው መልኬ ነው ሁለቱም፣
ልንቀልልሽ ለሚላት ውበቱ ላልገባው ግን ከቶ አይከፍቱም፣
አንዱ ከንፈሯ ተገልጦ ፈገግ ሲል በሷ፣
መንታ ነው መንገዱ ነገም ስቅ ይሆናል ይላል ሌላ ጥርሷ፣
ባለመንታ ጥርሷ ባለ ድርብርብ ጥርሷ ማቅ ክንብንብ ደስታ እያነቡ እስክስታ፣
በድርብ ጥርሷ ላይ ደምቆ እንደ ተፃፈ ደምቆ እንደ ተሳለ ያያት፣
ባይገባውም እኔ አይቻለሁ ፈገግ ባለችበት እንባዋ ደረቀ ።
@gellaposs@Naod_123https://t.me/gellaposs_1እንዲ አይነት ምርጥ ምርጥ ግጥሞች እንዲለቀቁ የምትፈልጉ ከሆነ like ና share + comment እንዳይለያችሁ