ሄ ዋ ን 🌺
❣ :¨·...............:¨·.❣
♥️ ክፍል 2
◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
✍ Written by Estifanos tekka
ባለቤቴ እንኳን የሱን ያህል አልተማረረብኝም ነገሮችን ገና መቀበል እንዳልቻልኩና ትንሽ ጊዜ እንዲታገሰኝ ለባሌ ነግሬው መስማማቱን ስነግረው....
እስከመቼ ነው የሚታገስሽ አመት ሊሞላችሁ ምን ቀረ ባይሆን ውለጂና ይሄን ሀብት የሚወርስ ልጅ ሰጥተሽ አስደስችው አለኝ እኔ ብወልድ ሀብቱ የሱ የሚሆን ይመስል ነገሮችን እንደማስተካክል ቃል ገብቼለት ከስንት ጭቅጭቅ በኃላ አሳመንኩት ባሌ ደውሎ የመጨረሻ ልጁ ነገ ከአውስትራሊያ እንደሚመጣ እና የሚያስፈልግ ነገር ካለ ለሰራተኞች ነግሬ እንዲያስተካክሉ በትህትና ጠየቀኝ ፡፡ ሁሉን እንደማሟላና እንዳያስብ ነግሬው አመስግኖኝ ስልኩ ተዘጋ.....ዛሬ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ደስ የሚል ስሜት ተሰምቶኛል! በጠዋት ተነስቼ ቤቱ መስተካከልና አለመስተካከሉን ቼክ አደረኩ ፡፡
ምሳ ምን መዘጋጀት እንዳለበት ነግሬያቸው ተጣጥቤ ፀጉሬን ልሰራ ወደፀጉር ቤት ሄድኩ... ከፀጉር ቤት እንደጨረስኩ የምፈልጋቸውን ነገሮች ገዛዝቼ እቤት ስገባ ነበር ባየሁት ነገር ባለሁበት ደርቄ የቀረሁት... ሀይ እንዴት ነሽ ሄዋን አለኝ ደስ የሚል ቃና ባለው ጎርናና ድምፅ.. .. እ..እንኳን ደህና መጣህ ማክቤል?? አሀ ማክቤል ብሎ ለሰላምታ እጁን ዘረጋልኝ.... ለደቂቃዎች እጁን ሳለቅ ፈዝዤ በቆምኩበት ቀረሁ... ዋው አባቴ ሚስቱ ቆንጆ እንደሆነች ቢነግረኝም እንደዚህ አልጠበኩሽም ነበር አለ እጁን ከጄ እያላቀቀ...
እ...አመሠግናለሁ እባክህ አረፍ በል መኝታ ቤት ገብቼ መጣሁ ብዬው የመሮጥ ያህል ካጠገቡ ጠፋሁ....
አልጋዬ ላይ በጀርባዬ ተኝቼ የማክቤልን ውበት ከፎቶ ይበልጥ በአካል እንደሚያምርና የኔ ሳየው መደንገጥ እያሰብኩ ነበር ድንገት በሬ የተንኳኳው... ሄዋን... የባሌ ድምፅ ነበር...አቤት አልኩት በድንጋጤ ካልጋዬ እየተነሳው ...
ነይ እንጂ ምሳ እየጠበቅንሽ ነው አለኝና ወደታች ወረደ .... ሊያምርብኝ የሚችለውን ቀሚስ በመምረጥና እራሴን በማስዋብ ጊዜ ወሰደብ... ልክ ወደ ታች ስወርድ ማክቤል ፊት ለፊት ነበር የተቀመጠው እግሬ ሲተሳሰር ታወቀኝ እንደምንም እራሴን አረጋግቼ ስላስቆየኃቹ ይቅርታ ብዬ ከባሌ አጠገብ ተቀመጥኩ....ባሌ ዛሬም እንደሁልጊዜው አምሮብሻል አለኝ እጄን እየሳመኝ ... ለመጀመሪያ ጊዜ ነው እንዲ ሲያረግ !
ደንግጬ እጄን ከእጁ መነጨኩትና የማክቤልን ገፅታ ተመለከትኩ ምንም አልመሠለውም.... ሚስትህ ቆንጆ ናት አባዬ ለራስህ ታውቅበታለህ አለው እየቀለደ.... ለምን እንደሆነ ባላውቅም በንግግሩ ተናደድኩ ብሽቅ አልኩ በውስጤ.... ምን ነካሽ ሄዋን አንቺ ያገባሽ ሴት ነሽ...አልኩ ለራሴ
ምሳ ተበልቶ እንዳለቀ ማክቤል ማረፍ እንደሚፈልግ ተናግሮ ወደክፍሉ ገባ ሳላስበው ባይኔ ተከተልኩት... ቆሞ ሁኔታዬን ሲመለከት የነበረው ባሌ ....
"ዛሬ ደስ ያለሽ ትመስያለሽ "....አለኝ የባሌ ድምፅ ነበር ከሀሳቤ ያነቃኝ ... ... ም ..ምምን ተገኝቶ ያው እንደበፊቱ ነኝ.... ል....ልግባና ልረፍ ትንሽ እራሴን አሞኛል አልኩት እየተርበተበትኩ ... ...
መድሀኒት ውሰጅ ምን አልባት ፀጉርሽን ስለተሰራሽ ይሆናል አለኝ ይሆናል ልግባና ልረፍበት ብዬው ወደክፍሌ ሄድኩ.....
አልጋዬ ላይ ጋደም እንዳልኩ ነኝ .... የማላውቀው የተዘበራረቀ ስሜት ይሰማኛል ደጋግሜ ማክቤልን አስብና ፈገግ እላለሁ.....
꧁༺༒༻꧂
✎ ክፍል ሶስት ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share
✨#ህይወቴ✨
🥀 @hiwote_love_story 🥀
🥀 @hiwote_love_story 🥀
┄┄┉┉✽»🌺✿🌺»✽┉┉┄┄