🌿 #ንነጽር_፵፯
ቀኑ 19/06/2015 ዓ/ም ዕለቱም እሑድ ነው። በመኪና ረጅም ጉዞ በመጓዝ ላይ ነበርኩ። መኪና ውስጥ እንደገባሁ የታየኝ ብዙ ሰው እና አንድ ክፍት ወንበር ነበር። እኔም ወደ ወንበሩ ጠጋ አልኩና ' #ሰው_አለው?' ብዬ ጠየቅኩ። ❝አይ የለውም መቀመጥ ትችላለህ❞ ተብሎ ሲመለስልኝ የገባሁት ለመቀመጥ ነውና ተቀመጥኩ።
...
ልክ እንደተቀመጥኩ ከአጠገቤ የነበሩት ኹለት ሴቶች መዝሙር ከፍተው ከስልካቸው ጋር አብረው እየዘመሩ ሰማኹ። መቼስ መዝሙር ሲሰማ የማይወድ የለ! እኔም በመዝሙሩ ተመስጬ በውስጤ መዘመር ጀመርኩ።
...
ትንሽ እንደቆየኹ መዘመር አቆምኩኝ እነርሱን ማድመጥ ቀጠልኩ። ድምጻቸው ያረሰርስ ነበር። ኹለቱም የድምጽ መንትዮች ይመስላሉ ተመሳሳይ ድምጽ አላቸው። ያው ሰው አይደለን? ደካሞችም አይደለን? ድካም ይዟቸው ነው መሰል ዝም አሉ። ስልኩ ግን አልተዘጋም።
...
ከትንሽ ቆይታ በኋላ ግን የማይታሰብ ነገር ተፈጠረ። መዝሙሩን ዘግተው ዘፈን ከፍተዋል። እጅግ አዘንኩና ከውስጤ ጠይቃቸው... ጠይቃቸው...! የሚል ስሜት ሲያስቸግረኝ ጠየቅኳቸው።
...
#ከትንሽ_ደቂቃ_በፊት_መዝሙር_ከፍታችኹ_ነበር_አኹን_ዘፈን_የመከፈቱ_ትርጕም_ምንድር_ነው? ብዬ ጠየቅኩ።
እነርሱም አሉኝ ❝መዝሙር እሚያምረው/እሚከፈተው ጠዋት ጠዋት ሲሆን ነው።❞ አሉኝ።
ቀጠልኩና ጠየቅኩ...
...
#አኹን_ይህን_ዘፈን_በምታደምጡበት_ሰዓት_እንደበፊቱ_መዝሙሩን_ከፍታችኹ_ብታደምጡ_ችግሩ_ምን_ላይ_ነው? እንዲህ አሉኝ...
❝አይ ችግር እንኳ የለውም፤ትንሽ ነቃ ነቃ ለማለት እንጂ።❞
ጥያቄዬን ቀጠልኩ...
...
#አኹን_ዘፈን_የከፈታችኹት « #ነቃ_ነቃ_ለማለት» #ከሆነ_ቅድም_መዝሙሩን_የከፈታችኹት_ለምን_ነበር?
❝እንዳይደብረን❞
! እንግዲህ ልብ በሉ ዘፈኑን የከፈቱት «ነቃ ነቃ ለማለት» ነበር። መዝሙሩን ደግሞ «ድብርትን ለማላቀቅ»
...
ነቃ ነቃ በማለትና ድብርትን በማላቀቅ መሃል ያለውን ልዩነት አስተውሉልኝማ!
...
ምንም እንኳ መዝሙር የመክፈት ዋነኛ ዓላማ እነርሱ እንዳሉት ባይሆንም፤ ግን ከድብርት አያላቅቅም እንዴ እእእ?
...
እኛ ሰዎች ስንባል እንዲህ ነን ምክንያት ለማያስፈልገው ነገር የማይሆን ምክንያት የምንደረድር፣
ለስሜታችን ተገዝተን ሌላውን የምናሰናክል፣
ደጉንም ክፉውንም የእኛ የሚመስለን በኹሉ የም
ንዳክር። ኧረ ይቅር ይበለን!
ሰላም ለምድራችን🙏
@MekuriyaM
@menefesawitereka
ፍቅር ለሕዝባችን🙏
...
❝ #እወ_እግዚኦ_አምላክነ_አኃዜ_ኵሉ_ዘይነግሥ_ለኵሉ_ዓለም_አቡሁ_ለእግዚእነ_ወመድኃኒነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ። #ንስእለከ_ወናስተበቍዐከ_በእንተ_ሰላም_ንጉሠ_ሰላም_ሰላመ_ሀበነ_እስመ_ኵሉ_ወሀብከነ_አጥርየነ_እግዚአብሔር_ወዕሥየነ_እስመ
_ዘእንበሌከ_ባዕድ_አልቦ_ዘነአምር_ስ
መከ_ቅዱሰ_ንሰሚ_ወንጼውዕ
_እንተ_ዘእምሰማያት_ሰላመከ_ፈኑ_ውስተ_አልባቢነ_ለኵልነ። 🙏ተሣሃለነ🙏