〰 በወዝ የሚተት መተት
ብዙዎች ልብሳቸውን፣ጫማቸውን፣ደብተራቸውን፣ብዕራቸውን ወዘተ ጓደኛ ለተባሉ ጉደኛ በማዋስ እድላቸውን በመተት በመቀልበስባዶ አድርገዋቸዋል፡፡ በወዛችን መተት የሚመተተው እና እድላችን የሚወሰደው በሁለት መልኩ ነው፡፡ አንደኛው የራሳችን እና የቅርባችን ለምንላቸው ሰዎች ልብሳችንን፣የምንጠቀምበትን ቁስ በማዋስ ነው፡፡ ከእኛ የተዋሱትን ነገር አጋንንት ጎታች እና መተት መታች ጋር ይዘው በመሄድ በወዛችን ያስደግማሉ፡፡ ከዛማ የእኛ የሆነው ሁሉ በተዘዋዋሪ ሳይሆን በቀጥታ የእነሱ ይሆናል፡፡
ሁለተኛው የእኛ የምንላቸው እኛ በምቀኝነት እና በቅናት የሚያዩን፣በመልካም ነገሮቻችን፣በተሰጦአችን ዓይናቸው ደምየሚለብስ፣በቅናት የሚንከላወስ የቅርብ ሩቅ የሆኑ ሰዎች የእኛን ለምሳሌ ልብሳችንን፣ቁሳችንን በመስረቅ እና በሰው በማሰረቅ ያስመትቱብናል፡፡ እነዚህም ሰዎች ሁለት ገጽታ ነው ያላቸው፡፡ አንደኛው ቀርበውን ወዳጅ ሆነውን ጓዳ ጎድጓዳችን ካወቁ በኃላ በመጎራበት የእኛን ነገር በመስረቅ ወስደው ያስመትቱበታል፡፡ ሁለተኛው እኛን ሳይቀርቡን ለምሳሌ ያሰጣነውን ልብስ፣ያስቀመጥነውን ቁስ ወዘተ ከውጭ ሆነው በማሰረቅ ያስመትቱብናል፡፡
ወዳጆቼ ሆይ አንዳንዴ ከቤት ያስቀመጥነው ልብስ እና ቁሳቁስ እንዲሁም በውጭ ያሰጣነው ልብስ እንደ ዘበት የሚጠፋው ለመተት ተግባር ነው፡፡ እኛ ኢትዮጲያውያን ኑሮአችን፣ማህበራዊ መስተጋብራችን ለመጠላለፍ፣በመተት ለመጉዳዳት ይመቸናል፡፡ ምክንያቱም ጉርብትናችን እንደ ቤተሰብ፣አሰፋፈራችን እንደ ምላስ እና ጥርስ በአንድ ቦታ ስለሆነ ነው፡፡
እዚህ ላይ አጥርቼ ልለፍላችሁ፡፡ መቼም ‹‹እንዴት መተት በወዛችን ይመተትብናል?›› ማለታችን አይቀርም፡፡ ወዳጄ አሁን በረቀቀው ዓለም አንድ ሰው አንድን ሰው በጨለማ እና ሰው በሌለበት ቦታ ቢገድለው ለገዳይ ምስክር ላይኖር ይችላል፡፡ ለሟች ግን እውነተኛ እና ሐቀኛ ምስክር አለ፡፡ ይህም አሻራ የምንለው ነው፡፡ አሻራ ደግሞ በሟች ሰውነት ወይም ሟች በሞተበት መሣሪያ ላይ የሚታተመው በወዝ ነው፡፡ ሟች የሞተበት ማንኛው ነገር ላይ የገዳይ አሻራ በራሱ ወዝ ምስክር
ይሆንበታል፡፡ ይህ ማለት ወዝ ማንነት ነው፡፡ ወዝ የአንድን ሰው ሁለንተና ሊገልጽ ይችላል፡፡ ስለዚህ ወዳጅ ያልናቸው እና በቅናት በጠላትነት የሚነሱብን ሰዎች በልብሳችን እና በቁሳችን ሳይሆን እሱ ላይ ባለው ወዛችን መተት ያስመትቱብናል፡፡ ያኔ ከሕይወታችን የሚፈልጉትን መልካም እድላችንን ይነጥቁናል፡፡ በራሳችን ወዝ በመተት በማፍዘዝ በማደንዘዝ ከቆሙት በታች ከሞቱት በላይ፤ከመቃብር በላይ ከሕያዋን በታች ያደርጉናል፡፡
ያኔ ከእኛ ኃላ ያሉት ሰዎች በእኛ እድል ከእኛው ይቀድሙናል፡፡ ብንሮጥ አንደርስባቸውም፡፡ የእኛ የሆነ ነገር እነሱ ጋር ስላለ ምን ይዘን እንሮጣለን? እኛ ውበት ከቁመናና እና ከመልካም ጠባይ ጋር ይዘን እነሱ ከእኛ በታች ሆነው በእኛው እድል ከእኛ በላይ ይሆናሉ፡፡ እነሱ ያገባሉ እኛ ቆመን እንቀራላን፡፡ እነሱ በእኛ እድል ይወልዳሉ እኛ የወላድ መካን እንሆናለን፡፡ እነሱ በእኛ እድል ሠርተው ሐብታም ይሆናሉ እኛ መሥራት እየቻልን እድላችንን ተነጥቀን በቤታችን ታስረን እንኖራለን፡፡ እኛ ተምረው የት ይደርሳሉ ለሰው እና ለሀገር ይተርፋሉ ተብለን ተስፋ የተጣለብን ተስፋ ቢስ ሆነን እውቀታችንን ተነጥቀን ያለ አንዳች ሥራ እንቀመጣለን እነሱ በእኛ እድል እና እውቀት ተምረው እንጀራችን እየበሉ ይኖራሉ፡፡
ብዙዎቻችን እንደ ቀልድ በለጋነት እድሜያችን ነገሮችን በፍጹም በማናውቃቸው ጊዜያት እድላችንን በወዛችን ተነጥቀናል፡፡ ለምሳሌ በትምህርት ዓለም እያለን አንዱ የትምህርት እድላችን፣እውቀታችን የሚሰለበው በመተት ቢሆንም የሚደገመው በወዛችን ነው፡፡ ይህም ደብተራችን፣ብዕራችን፣ልብሳችንን ተውሰው በወዙ አስደግመውበት ይመልሱልናል፡፡ እኛም በአስደንጋጭ ሁኔታ የትምህርት አቅማችን እየወረደ፣ትምህርት እያስጠላን በሂደት እንፈዛለን እንደነዝዛለን፡፡ እነሱ እያየናቸው እየተገላበጡ እየተለወጡ ይሄዳሉ በእኛ እድል ተምረው ሰው ይሆናሉ፡፡
እኛ ለወዳጅ ባዋስነው እኛ በተሰረቀብን ልብስ፣ቁስ በወዙ መተት ተመትቶበት ዕድላችንን ይወስዳሉ፡፡ በተለይ የትዳር፣የልጅ፣የሥራ ወዘተ ዕድላችን በወዛችን ተደግሞበት ብዙ ነገራችንን እናጣበታለን፡፡ ወዳጆቼ አጋንንት ረቀቅ ያለበት ጊዜ ስለሆነ መተት የሚመትቱትም እንኳን በቁሳችን በእጃችን ወዝ የመስለብ ሥራን ይሠራሉ፡፡ አንድ የማውቀው ማህበርተኛዬ አለ፡፡ ይህ ልጅ አሜሪካ እንደ ነገ ሊሄድ እንደ ዛሬ የሽኝት ፕሮግራም አዘጋጅቶ ጓደኞቹን ይጠራል፡፡ እሱ ይህንን ባዘጋጀ ጊዜ አንድ የሚያውቃቸው ትልቅ አባት ከሽሬ ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ድረስ በመምጣት አግኝተውት ‹‹ልጄ እባክህ እንዲህ ዓይነት ሰው ጠበቅ አድርጎ እጅህን ጨብጦ ሰላም ይልሃል፡፡ ከቻልክ ጸሎተ ማርያምን እየጸለይክ አናግረው ግን ሰላም ባትለው ይሻላል›› ይሉታል፡፡ እሱም እንደ ቀልድ ለይስሙላ እሺ ይላቸዋል፡፡
ማታ ፕሮግራም ይጀመራል ወዳጅ የተባለ ሁሉ ይመጣል፡፡ ይበላል ይጠጣል፡፡ አንድ የሚያውቀው እና በነገሮች ሁሉ የሚቀናበት ስለ እሱ መልካም እድሎች በተደጋጋሚ ‹‹አንተማ ታድለህ፣አንተማ ያሰብከው ይሳካል›› እያለ የሚያሟርትበት ጓደኛ ተብዬው ግጥም አድርጉ ባልተለመደ ምልኩ ጨብጦ ሰላም ይለዋል፡፡ አጅሬም ከሆነ በኃላ የእኛ አባት ቃል ትዝ ይለውና በልቡ ‹‹ምናባቱ ምን ያመጣል›› ብሎ እንደ ዘበት አይቶ ያልፋል፡፡ ይሄ ልጅ አሜሪካ እንደ ገባ ከጥቂት ቀናት በኃላ እጄን ወጋኝ ጠዘጠዘን ማለት ጀመረ፡፡ እዛም በጥሩ ሁኔታ ታከመ ግን እየተሻለው ሳይሆን እየባሰበት ሄደ፡፡ በሚገርም ሁኔታ ቀኝ እጁ እንደ ለምጽ በመንደድ በሂደት እጁ ሰለለ፡፡ ዛሬ ቀኝ እጁ ምንም የማይሠራበት ሆኖ ከመስለሉ በተጨማሪ ሠርቶ አምድ አፋሽ ሆኗል፡፡ ጤናውን አጥቶ በመተት ተጎድቶ ይኖራል፡፡
ወዳጆቼ ከላይ በርዕሱ እንደነገርኳችሁ የመተት አንዱ ጦሱ ጤናችንን ማቃወሱ ነው፡፡ ስንቶች አሉ በልብሳቸው፣በቁሳቸው ወዝ መተት ተመትቶባቸው እድላቸውን ብቻ ሳይሆን ጤናቸውንም አጥተው የአልጋ ቁራኛ የደዌ ዳኛ ሆነው በየ ቤታቸው፣በየ ጸበሉ በየ ሐኪም ቤቱ ያሉ፡፡
እህት ወንድሞቼ ከቤታችሁ ያስቀመጣችሁት፣በውጭ ያሰጣችሁት የውስጥ ልብሶቻችሁ ለምሳሌ ፓንት፣ታይት፣ካልሲ፣የጡት ማስያዣ፣ጃፖኒ/ፓክ አውት/ በቀጥታ ከሰውነታች ጋር ስለሚገናኙ በወዝ ለሚመት መተት አንድ ግብአት ስለሆኑ ጠንቀቅ ብትሉባቸው አይከፋም፡፡ ‹‹ኢዲያ
ውሸት ነው እኔ ላይ አይሠራም›› ካላችሁ እዳው ገብስ ነውና ታገኙታላችሁ መልሳችሁ የማታገኙትን እድላችሁንም ታጣላችሁ፡፡
ወዳጆቼ ሆይ በልብሳችን ወዝ የሚመተተው መተት እድላችንን ከማኮላሸት በተጨማሪ መልካችንን ያበላሻል፡፡ አንዲት ሴት በወዝዋ ጓደኛዋ መተት ብታስመትትባት መልከኛዋ ለወንዶች መልከ ጥፉ ሆና ትታያለች፡፡ መልከ ቢስዋ ለወንዶች መልከኛ ሆና ትታያለች፡፡ በዚህም አስመታችዋ የመልከኛዋን የመልክ ወዝ ተላብሳ ቆንጆ መስላ ትታያለች፡፡ ለዚህም ነው መልከኞቹ ውበት ይዘው ሳያገዙ ይቀራሉ የእነሱ ጓደኛ መልከ ቢስ መተተኛዋ ቆንጆ ወንድ አግብታ ትኖራለች፡፡ ወዳጆቼ በወዝ የሚመተት መተት የመልክ ደም ግባታችንንም እንዲወሰድ ያደርግብናል፡፡ በብዛት በመልካቸው የወዝ ድግምት ተደግሞባቸው ያሉ ሰዎች ፊታቸው ባላወቁት ምክንያት ውበታችው ይጠፋል፣ፊታቸው በብጉር ይመታል፣ፊታቸው ይቆስላል፣ፊታቸው እየሻከረ እየወየበ ይሄዳል፣የማይጠፋ ጠባሳ መሰል ምልክት ይታይባቸዋል፡፡