🔷የሙመይዐዎች አቅለ ደካማነት እነ እውርነትየኢሊያስ አህመድ ሰላሳዎቹ የእንቅልፍ ኪኒኒዎች ሙሪዶቹን አደንዝዞ የመርከዙን መሪዎች ግልጽ የሚንሓጅ ስህተታቸውን ማግኘት አቅቷቸው ቆይተዋል
በዚህ በታወረ እይታቸውና በደካማ አቅላቸው የሱናውን ደዕዋህ ቢድዐህ እነ ብልሽት የእኽዋኖችን ደዕዋህ መደገፍና ከእነሱ ጋር መንቀሳቀስ ደሩራ እነ መስለሃ አድርጎ በማየትና በመረዳት የሰለፊያንና የሰለፊዮችን እንቅስቃሴ ይዋጋሉ ።
እነዚህ አቅላ ደካማዎች ተመዩዝን ግዜ ያለፈበት ለዚህ ዘመን የማይመጥን አድርጎ በማየት በሰለፊዮች ለይ ያፌዛሉ ።
የድክመታቸው መጨረሻ መሪዎቻቸው ከሱና ከመውጣታቸው በፊት በነበሩት ግዜ የሱና ኡስታዞችና መሻይኾች የወደሷቸውን ሪከርድ እየበተኑ "ማን ነው ከድሮ አቋሙ የተቀየረው እያሉ ለማጭበርበር መሞከራቸው ነው !
👉
የኔ ትክክለኛው አቋም ለይ በነበሩበት ግዜ ሰለፊዮች ለነሱ መከላከላቸው እነ እነሱን ማወደሳቸው የሰለፊዮችን ፍትሐዊነት እነ ምንግዜም ከሀቅ ሰዎች ጎን መቆማቸውን ነበር የሚያሳየው ግን ምን ይደረጋል አቅላቸው ደካማ ነው ።
ምን ይሄ ብቻ በሆነ ቅጽበት እንዃን እንዳይመለከቱ አይናቸው ታውሮዋል ። ከእንቅልፋቸው ተነስተው እንደምንም አይናቸውን ከፍተው የመሪዎቻቸውን ጥሜት ይመለከቱ ዘንድ የሰለፊያ መሻይኾች ኡስታዞች ዱዓቶች ወንድሞች አላህ ይጠብቃቸው የእነ ኢብኑ ሙነወርን የኢሊያስ አህመድን የኸድር ኸሚሴን የሳዳት ከማልን የሌሎችንም ጥሜት በተለያየ መንገድ የአጥፊዎቻቸውን ጥፋት በማብራራት ዋጋ ተከፍሏል እየተከፈለም ታዲያ አይናቸውን አሻሽተው ውሃም ቢሆን አርከፍክፈው በመክፈት የመሪዎቻቸውን ጥሜት ማየት መመልከት ሲኖርባቸው አይ አንፈልግም እንቅልፉ ተመችቶናል በማለት በቅዠታቸው ቀጥለውበታል ።🔹
ኡስታዝ አቡበከር ዩሱፍ ከባህርዳር የኔ ሳዳት ከማል በሱና በነበረበት ሰዐት ከእኽዋኖች በኩል የነበረበትን ትችት በተመለከተ እየተከላከለለት የተናገረውን የድምፅ ፋይል ይዘው ይሄው እናንተ ወይስ የኛ ኡስታዞች ናቸው አቋም የቀየሩት እያሉ በደካማ አቅላቸውና በታወረ እይታቸው በቁማቸው ይቃዣሉ ።👉የኡስታዝ አቡበከርን ድምፅ 👇ለማግኘት
https://t.me/MisbahMohammed_6682/9695🔂
ልብ ያለው ልብ ይበል ተዝኪያ ውዳሴዎች መከላከል ድጋፍ ከለላ የሚሰጡት ለዘላለም አይደለም ።
ዑመር ረዲየአላሁ ዐንሁ ዐብድረህማን ኢብኑ ሙልጂምን አወድሶት ነበር ታዲያ ይህ ውዳሴ ለዐብድረህመን ጠቀመው ? ላ ! አልጠቀመውም መጨረሻ ኸዋሪጅ ሆኖ ሶሃባውን ዐሊን ረዲየአላሁ ዐንሁ ገደለ ።👉ኡስታዝ እንዳለውም እነዚህ ሰዎች ሙመይዐዎች ማለት ነው በሰለፊዮች ሚዛን የሚደፋ ስህተት ቢያገኙ ጩሀታቸው በየሙሃደራውና ማህበራዊ ሚዲያው በናወጡት ነበር ። ! አቅለ ደካማነት እነ እውርነት ሆኖ በቁም መቃዠት ሆነባቸው ።
መስካሪዎቹ የምስክርነት ቃል ስሰጡ " በሆዷ ነው ስትሳደበው ያየነው" እንዳሉት ሆነባቸው ።
👉አንድ ሰው የሚገመገመው በስራው እንጂ በሸሐዳው እነ በተዝኪያው አይደለም !
ኧረ ተው ንቁ ከእንቅልፋችሁ ተመልከቱ የኢሊያስን ችግር ተመልከቱ
የኢሊያስና የባልደረቦቹ ስህተቶች ያኔ በደምብ ባልተዩበት ግዜ እነ ኢብኑ ሙነወር ኸድር ኸሚሴ ሳዳት ከማል ረድ አድርገው ነበር አሁን ጥሜቶቻቸው የበለጠ ግልጽ ሆነው ሐገር አዳርሰዋል አይደል የት አለ የኢብኑ ሙነወር ረድ ?
የት አለ የሳዳት ረድ ?
የት አለ የኸድር ኸሚሴ ረድ ?
እንዃን ረድ ልያደርጉ ውዳሴያቸውን ነው የሚያዘንቡት !
እንዃን ረድ አድራጊ የሱና መሻይኾችን ልደግፉ በስድብና በማላገጥ ነው ከአጥማሚዎቹ ከእነ ኢሊያስ ጎን ነው የቆሙት !
እኛ የምንለው አሁንም አልረፈደም ከእንቅልፋችሁ ተነሱ ሰዎቻችሁን የያዛቸው ነገር ይዞዋቸዋል የጀይላን ጠንካራ ስራ ደርሶ ጠልፏቸዋል አንቅራችሁ ለጀይላን በመተው ኑ በፍትህ በሐቅ ተውሂድንና ሱናን በግልጽ የሚሰበክበት ተመዩዝ በተግባር የሚሰራበት መድረክ የሰለፊያ ሚንሓጅ ይሻላችኋል ።
🤲አላህ ሆይ ሐቅ መስሏቸው ከሙመይዐዎች የተሰለፉ ሱና ወዳዶችን ሱናን አሳውቀሃቸው ከሱና ሰዎች በመሆን ለሚወዱት ሱና የሚሰሩ አድርጋቸው
ለሁላችንም በሰለፊያ ለይ በኢኽላስ ፅናትን ስጠን
✍Abu Nuh ሚስባህ ሙሐመድ
https://t.me/MisbahMohammed_6682