✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


✅:አላማው ˙ እንዴት የኢስላማዊ አስተምህሮት ግንዛቤን መጨመር እንችላለን።
ᘛ በሌላም በኩል࿐
▮ሀዲስ📚
▮በድምፅ ትምህርቶች🎤
▮የቁርአን ቲላዋ📖
▮አጫጭር ትምህርቶች📝
▮ከታሪክ ማህደር📜
▮ጠቃሚ አፖች📲
▮ሌላም. . .📧
ᘛ ወደ ግሩፓችን ይቀላቀሉ ✓
@Muslim_group2
─────⊱◈🌟◈⊰─────
📬:አስተያየት ༻
@Muslim_comment_bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


🌿ኢብኑ ተይሚያ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላል :-

⬅️አላህን ፈሪ ለመሆን ወንጀል አለመስራት መስፈርት አደለም። ከወንጀል ጥቡቅ መሆንም የግድ አደለም። ነገሩ እንደዛ ቢሆን ኖሮ በኡማው አንድም አላህን ፈሪ አይኖርም ነበር። ነገር ግን ከወንጀሉ የቶበተ አላህን ፈሪ ይሆናል። ወንጀሉን ሚያስምር ሌላ መልካም ስራ የሰራም ሰው አላህን ፈሪ ሚለው ውስጥ ይገባል።➡️

📙:|[ሚንሀጁ ሱና (٧ / ٨٢) ]
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀ 📙
┊  ✿
🔗
Muslimchannel2.t.me


ቫይታሚን ص 💡
· · • • • ✤ • • • · ·

:ስለቫይታሚን ሷድ(ص) ሰምታችሁ ታውቁ ይሆን

➣ቫይታሚን ሷድ(ص) ማለትማ፦

🔺ፃም(صوم)፣ሶላት(صلاة)፣ሶደቃ(صدقة)፣ትእግስት(صبر)፣ዝምድናን መቀጠል(صلة رحم)፤እውነተኛነት(صدق) እና ደጋጎችን መጎዳኘት ጓደኛ አድርጎ መያዝ(صحبة صالحة)

➡️ይህ ቫይታሚን 《ص》የሚባለው የምግብ ክፍል ሩሀችንን በመገንባት የሚታወቅ እንደሆነ ሁሉ ፍቱን  ፈዋሽነቱ የተረጋገጠ የመዳኒትንም አይነት አዘል አለው ። ይህም መድሀኒት የሚከተለው ነው ➘

➡️:የመድሀኒቱ ስም ፦"ካሁን በኃላ አትረበሽ"፣"ካሁን በኋላ አትጨነቅ" ፣ "ካሁን በኋላ አትጠበብ"።

🧬የተሰራበት ንጥረ ነገር ፦

🔸:لا إله إلا أنت سبحنك إني كنت من الظالمين

🔹:《ካንተ ውጭ በሀቅ የሚመለክ አምላክ የለም ጥራት ይገባህ እኔ ከበዳዮች ነኝ /ብየ እመሰክራለሁ/ 》ከሚለው የአላህ ቃል ነው።

🔖:የመድሀነቱ አጠቃቀም ፦ በስጁድ ውስጥ ብትጠቀመው በጣም ውጤታማ ያደርገሀል።

📇ውጤቱ፦《 فاستجبنا له ونجيناه من الغم وكذالك ننجي المؤمنين》

«ዱአውን ተቀበልነው ከጭንቀቱም ገላገልነው እንደዚሁ ሙእሚኖችን ከጭንቀት እንገላግላቸዋለን» በሚለው የአላህ ቃል የተረጋገጠ ነው።

🟣:መለያው ፦ ይህ መድሀኒት ነፍስ ውስጥ እርካታን ፣ እረፍትን በማስገኘትና ፍርሀትን ፣ ትካዜን ፣ መረበሽን ፣ የነርቭ ውጥረትን እንዲሁም የወንጀል ነቀርሳን በማስወገድ ከሌላው ይለያል።

📌:ከህክምናው ጋር መጥፎ ስነ ምግባር አብሮ ስለማይሄድ ታካሚው #ሊታቀብ ይገባል ። ይህንን መድሀኒት ግፍ ፣ መረገጥ ፣ የሀሳብ መጨናነቅና በህይወት ውጣ ውረድ የልብ ጥበት በተሰማህ ሁሉ ወቅት መውሰድ ትችላለህ ።

🗓:የህክምናው ጊዜ ፦ እድሜ ልክ ።

^~لا إله إلا أنت سبحنك إني كنت من الظالمين~^
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀ 📚
┊  ✿ 🔗
❀ ✨                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP• @Muslim_group2      
┣━━━━╗ ❤️ ╔━━━━⎙
┣CHL• @Muslimchannel2
╠════•❁🎐❁•═════╣
🌐 #SHARE_The_خير🔺


አስኳላቸው 🏵

💡:ኢስላም ዐቂዳ ነው ፤ #አስኳሉ ተውሒድ ነው።

💡:ዒባዳ ነው ፤ #አስኳሉ ኢኽላስ ነው።

💡:መኗኗር ነው ፤ #አስኳሉ እውነተኝነት ነው።

💡:ስነ - ምግባር ነው ፤ #አስኳሉ እዝነት ነው።

💡:ህግ ነው ፤ #አስኳሉ ፍትህ ነው።

💡:ሥራ ነው ፤ #አስኳሉ ጥራት ነው።

💡:አደብ ነው ፤ #አስኳሉ ትህትና ነው።

💡:መስተጋብር ነው ፤ #አስኳሉ ወንድማማችነት ነው።

💡:ሥልጣኔ ነው ፤ #አስኳሉ ሚዛናዊነት ነው።
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀ 📗
┊  ✿
🔗
Muslimchannel2.t.me


ማስታወሻ 🖥

➡️በዒባዳ ላይ የቱንም ያክል ብትሳነፍ በስነምግባርህ ግን እንዳትዘቅጥ። ምናልባትም የጀነትን ከፍ ያለችዋን ደረጃ የምትጎናጸፈው በመልካም ስነምግባርህ ሊሆን ይችላል::

🌿 ኢብኑል ቀይም

:ስነ ምግባር በእስልምና ከፍተኛ ስፍራ ተሰጥቶታል፡፡ የአሏህ መልእክተኛ ( ﷺ ) የተላኩበትን ዓይነተኛ ዓላማ ፣ የዳዕዋቸውን ጉልህ ሚና እንዲህ ሲሉ ገልጸዋል፡-

‹‹እኔ የተላክኩት መልካም ስነ ምግባራትን ለመሙላት ነው፡፡››

🔰:አሏህ ( ﷻ ) እርሳቸውን ሲያሞግስ እንዲህ ብሏል፡-

🔸:ﻭَﺇِﻧَّﻚَ ﻟَﻌَﻠَﻰٰ ﺧُﻠُﻖٍ ﻋَﻈِﻴﻢٍ

🔹:‹‹አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ፡፡›› (አል-ቀለም፥ 4)

🔎:የአሏህ መልእክተኛ ( ﷺ ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በእለተ ቂያማ ከሙእሚን ሚዛን ላይ ከመልካም ስነ ምግባር የሚከብድ ነገር የለም፡፡ አሏህ ባለጌን አይወድም፡፡ የመልካም ስነ ምግባር ባለቤት ጿሚዎችና ሰጋጆች ከሚደርሱበት ደረጃ ይደርሳል፡፡››

🏴‍☠️አህመድ

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤🌗ᢀ
@Muslimchannel2 💌


#ጥቂቶች ⭐️

:ብዙዎች ይናገራሉ፤ ጥቂቶች ይደመጣሉ።

:ብዙዎች ያነባሉ፤ ጥቂቶች ይረዳሉ።

:ብዙዎች ያገኛሉ፤ ጥቂቶች ይደሠታሉ።

:ብዙዎች ይሮጣሉ፤ ጥቂቶች ይደርሳሉ።

:ብዙዎች ይደክማሉ፤ ጥቂቶች ያሣካሉ።

:ብዙዎች ይፀልያሉ፤ ጥቂቶች ይሠማሉ፡፡

:ብዙዎች ይለፋሉ፤ ፕቂቶች ጀነትን ያገኛሉ።

:ብዙዎች አይተው ያልፋሉ ፤ ጥቂቶች ለሌሎች #ሼር ያረጋሉ።
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀ 📗
┊  ✿
🔗
Muslimchannel2.t.me


😎:በቁርዕን ላይ ረጅሙ ቃል የትኛው ምዕራፍ ላይ ይገኛል ❔
Опрос
  •   አል - ሂጅር
  •   አል - ፈለቅ
  •   አል - ዋቂዕህ
540 голосов


ዓላማ አለን ⁉️

:ዓላማ ከሌለን በሕይወት ጉዞ ላይ በቀላሉ እንደናቀፋለን። በቀላሉ የምንዋልልና የምንባክን እንሆናለን። እንዲሁም የስራችን ውጤትም ያነስ ይሆናል።

🎯:#ዓላማ ካለን ግን፤ በሕይወታችን ውስጥ ወጥ የሆነ ነገር ይሆናል። በ ‹‹ዓላማ ላይ›› መሆን ማለት መስራት የምንወደውን መስራት፣ ጎበዝ የሆንበትን መስራት እና አስፈላጊ የሆነውን ውጤት ማግኘት ማለት ነው።

:በእርግጠኛነት ዓላማችን ላይ ከሆንን፤ ሰዎች ፣ የምንፈልገውን ነገሮች እና እድሎች ሁሉ ወደ እኛ ይሳባሉ። ከእውነተኛ የሕይወት ዓላማ ጋር በመስማማት ስንሰራ ፤ ስራችን ሌሎችንም የሚያገለግል ስለሚሆን ዓለምም🌍 በኛ ይጠቀማል።

🪴:
#ዓላማ ይኑረን ~
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀ 📚
┊  ✿
🔗
❀ ✨                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP•
@Muslim_group2      
┣━━━━╗
❤️ ╔━━━━⎙
┣CH
L@Muslimchannel2
╠════•❁🎐❁
•═════╣
🌐 #SHARE_The_خ
ير🔺


#ካ ዕ ባ 🕋

:በኢስላም #ሶስት(3) ቅዱስ ስፍራዎች ሲኖሩ፤ ሙስሊሞች ሊጎቡኛቸው እንደሚችሉ ታዘዋል ።እነዚህም

1️⃣:የመካው የተቀደሰ መስጂድ ৲
2️⃣:የመዲናው የነቢዩﷺ መስጂድ እና ৲
3️⃣:እየሩሳሌም የሚገኘው የአቅሳ መስጂድ ናቸው፡፡

🔎:ይህን በተመለከተ ነቢዩﷺ እንዲህ ብለዋል➘

"ኒያ አድርጋችሁ ወደ ሶስቱ መስጂዶች
ለጉዞ ውጡ፡-ይህ የእኔ መስጂድ(መዲና የሚገኘው) የመካ ቅዱስ መስጂድ እና
የአቅሳ መሲጂድ በኢየሩሳሌም፡፡"

🔹ቡኻሪና ሙስሊም 📚

📋:በመካ የሚሰገድ ሶላት ከሌላው ስፍራ በ100,000 ደረጃ ሲበልጥ፤በእኔ መስጊድ (መዲና)የሚሰገድው 1000 ደረጃ ሲበልጥ፤ በአቅሳ መስጊድ የሚሰገደው ሶላት በ500 ደረጃ ይበልጣል፡፡

🔹ቡኻሪ እንደዘገቡት📗

🔸:إن أول بيت وضع للناس للذي ببكة مباركا وهدى للعالمين

🔹:ለሰዎች (መጸለያ) መጀመሪያ የተኖረው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲኾን ያ በበካህ (በመካ) ያለው ነው፡፡(3:96)


🕋:ካዕባ የሙስሊሞች ፀሎት(ሶላት) አቅጣጫ🧭 ሲሆን ካዕባም ይሁን ሃጅረል አስወድ የሚመለኩ ሳይሆን ይልቁንም ሙስሊሞችን አንድ የሚያደርጉ የኢባዳ (አምልኮ) አቅጣጫ መገልገያ ናቸው፡፡

✅:ነቢዩﷺ ስለ ካዕባ ሲናገ
ሩ ৲

▮አንተ #ቅዱስ ነህ ግን በአላህ ዘንድ
#የሙስሊም ደም የበለጠ ካንተ የተቀደሰ ነው፡፡▮

📕:رواه ابن ماجة وصححه العلامة الألباني في صحيح الترغيب 2/
630
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀ 📚
┊  🔗
❀ ✨                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP• @Muslim_group2      
┣━━━━╗ ❤️ ╔━━━━⎙
┣CHL• @Muslimchanne
l2
╠════•❁🎐❁•═════╣
🌐
#SHARE_The_خير🔺


#ትዝብት 💠

🖱በመስጅድ ግቢ ዉስጥ ያሉ ሽንት ቤቶችን ስትመለከቱ "ንጽህና የኢማን ግማሽ ነው" የሚለዉን ሀዲስ የሰማ ሰው የለም ትላላችሁ። አብዛኛው መስጅድ ግቢ በጣም የሚያሸማቅቅ መጸዳጃ ቤት ነው ያለው።

🖱ለሱብሂ ሶላት ሰዎች የሚለብሷቸውን ልብሶች ስትመለከቱ ለእያንዳንዱ ሶላት መዋቢያዎቻችሁን ያዙ የሚለዉን የቁርአን አንቀጽ ያስተማረ ዐሊም የለም ልትሉ ትችላላችሁ።

🖱አንዳንዴ በትራንስፖርት ላይ ከጎን የተከናነቡ እህቶች ጋር ሆናችሁ ከተጓዛችሁ ደግሞ ከላይ ከተጠቀሱት በተጋነነ መልኩ እፍረት ሊሰማችሁ ይችላል።

;

➡️የመስጅዶቻችን ሽንት ቤቶች ከግል ሽንትቤቶቻችን ለምን ያነሰ ጽዳት ይኖራቸዋል?

➡️ባለስልጣን ለመገናኘት ምርጥ ለብስን እያወጣን አላህ ጋር በምንገናኝበት ሶላት ለምን ቡቲቶና የሌሊት ልብስን እንመርጣለን ?

➡️በንጽህናችን ሌሎችን መማረክ ስንችል ለምን ሰዎችን በመጥፎ ጠረን እናስቸግራለን?
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀ 📚
┊  ✿
🔗
❀ ✨                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP•
@Muslim_group2      
┣━━━━╗
❤️ ╔━━━━⎙
┣CH
L@Muslimchannel2
╠════•❁🎐❁
•═════╣
🌐 #SHARE_The_خ
ير🔺


ተሰቅሎ የሚያድነው (ግልኮስ) ብቻ ነው
እሱ ከ Allah ☝️ ይፈልጋል ለማዳን..

╰┈➤🌗ᢀ
@Muslimchannel2 💌


🔍:ዛሬ ላይ የሰዎችን ማንነትና ሥነምግባር መስጂድ አካባቢ አትፈልጉ። እዉጭ በልብስና በአካላቸው ላይ በሚያንፀባርቁት ሁኔታቸው ላይም አትፈልጉ። ሶላትና ፆማቸው ዉስጥም አትፈልጉ።
ባይሆን በንግድ ቦታዎች አካባቢ እምነት ያላቸው ስለመሆኑ፣ አደራ ሲሰጧቸው ታማኝ ስለመሆናቸው፣ በብድርና ዕዳ በጊዜ የሚመልሱ መሆናቸዉን፣ በዝምድና የሚቀጥሉ መሆናቸዉን፣ ዉርስ በሚከፋፈልበት ጊዜ ፍትሃዊ መሆናቸዉን ..በነኚህ ቦታዎች ላይ ይመልከቱ። በርግጥም እዚህ አካባቢ ተፈትነው ካለፉ ኢማን ያላቸው ጥሩ ሰዎች ናቸው።

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤🌗ᢀ
@Muslimchannel2 💌


ዱንያ አጠፋፋችን አይደል አህባቢ 😶‍🌫️
ምንም ይ
ሁን ምንም ለዱንያ እጅ አንሰጥም . . .

:ዱንያ ላይ ያለነው ለመኖር ነው፡፡ እስከኖርንም እጅ አንሠጥም #እንታገላታለን፡፡ እጃችንን ሰብስበን ዱንያን በብርቱ እንፋለማታለን፡፡ እና አላህ የሚታገሉትን #ይረዳልና በቻላችሁ መጠን ሁሉ ታገሉ፡፡ ⚡️

➡️የሆነች ነገር ሞክሩና 'ጌታዬ ሆይ በዚህች ላይ ትንሽ ጨምርልኝ' በሉ፡፡ የአላህ ትንሽ ነገር ብዙ ናት፡፡ የሱ ጠብታ እዝነት ተራራ ናት፡፡

. . .

:የቻላችሁትን ያህል በአላህ ትዕዛዝ ሥር ተገኙ፡፡

:አቅማችሁ በፈቀደው መጠን መልካም ሥሩ፡፡

:አላስተዋላችሁም እንጂ ብዙ ነገር ተሠጥታችኋል፡፡

:አላህ ከሠጣችሁ መልካም ቃላት ይሁን ገንዘብ ወይም ከሌላ ነገር አትሰስቱ፡፡

:በቀን ይሁን በማታ ለችግረኞች እጃችሁን ዘርጉ፣

:የተጨነቁትን አብሽሩ በሉ፣

:የየቲሞችን እንባ አብሱ፣

:ተስፋ የቆረጡትን አጽናኑ፣

:ሐዘን ለገባቸው ፈገግ አሳዩ፣

:ግራ ለተጋቡት ያልፋል በሉ፣

ሀሳብ ካዳከማቸው አጠገብ ሁኑ፣

:የተሰበሩትን ጠግኑ፣

:የተጎዱትን አክሙ፣

:ሸክም ለከበዳቸው መከታ ሁኑ፡፡



🫀:እንዲያ ስንሆን የዱንያን ፈተናዎች አብረን እንሻገራለን ። እንዲህ ጥሩ ስንሆን አላህ ይወደናል፤ ይቀበለናል፡፡ እሱ ከተቀበለን ሌላው ሁሉ ቢጥለንም ምንም አይደል፡፡  
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀ 📚
┊  ✿
🔗
❀ ✨                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP•
@Muslim_group2      
┣━━━━╗
❤️ ╔━━━━⎙
┣CH
L@Muslimchannel2
╠════•❁🎐❁
•═════╣
🌐 #SHARE_The_خ
ير🔺


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
#አቦሸማኔ🐆በጣም ፈጣን ነኝ አለ

#ዝሆን🐘ግዙፍ ነኝ አለ

#ነብር🐅እኔ በጣም ጠንካራ ነኝ አለ

#ተኩላ🐺 ገዳይ ነኝ አለ

#ዳይኖሰር🦖ጥንታዊ ነኝ አለ

ማን ቀረ ?!

#አንበሳ🦁 "ምንም ይሁን ምንም እኔ ንጉስ ነኝ አለ"

✔️አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-

🏳️قُلِ اللَّهُمَّ مَالِكَ الْمُلْكِ تُؤْتِي الْمُلْكَ مَن تَشَاءُ وَتَنزِعُ الْمُلْكَ مِمَّن تَشَاءُ

🏳️(ሙሐመድ ሆይ!) በል፡- «የንግስና ባለቤት የኾንክ አላህ ሆይ! #ለምትሻው ሰው ንግሥናን ትሰጣለህ፡፡ ከምትሻውም ሰው ንግሥናን ትገፍፋለህ፡፡
▮ዒምራን:26▮

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤🌗ᢀ
@Muslimchannel2 💌


Репост из: ✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🥹💛


📌 | የስድስቱ የሸዋል ቀናት | 📆
📏📏📏📏⭐️📏📏📏📏

🔸:قـَالَ العَلّامَة صَالِح الفَوْزَان -حَفِظَهُ الله

«ﻭﻣﻦ ﻋﻼﻣﺎﺕِ ﺍﻟﻘﺒﻮﻝِ ﻓﻲ ﺭﻣﻀﺎﻥَ ﻭﻓﻲ ﻏﻴﺮﻩ ﺍﺗﺒﺎﻉُ ﺍﻟﺤﺴﻨﺔِ ﺑﺎﻟﺤﺴﻨﺔ ﻓﺈﺫﺍ ﻛﺎﻧﺖ ﺣﺎﻟﺔُ ﺍﻟﻤﺴﻠﻢِ ﺑﻌﺪَ ﺭﻣﻀﺎﻥَ ﺣﺎﻟﺔً ﻃﻴﺒﺔً، ﻳﻜﺜﺮُ ﻣﻦ ﺍﻟﺤﺴﻨﺎتِ وﺍﻷﻋﻤﺎﻝِ ﺍﻟﺼﺎﻟﺤﺔ ﻓﻬﺬﺍ ﺩﻟﻴﻞٌ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻘﺒﻮﻝ،

🔹:የረመዷን ተቀባይነቱ ምልክቱ ፣ በሌላ ጊዜ መልካምን ነገር በመልካም ማስከተሉ ነው። የሙስሊም ሁኔታው ከረመዷን በሇላ ጥሩ የሆነች ጊዜና ጥሩ ነገሮች ፣  ከመልካም ስራዎች የሚያበዛ ከሆነ ይህ ለተቀባይነቱ አመላካች ነው።

🔸:ﺃﻣَّﺎ ﺇﻥ ﻛﺎﻥ ﺍﻟﻌﻜﺲ، ﻳﺘﺒﻊ ﺍﻟﺤﺴﻨﺎﺕِ ﺍﻟﺴﻴﺌﺎﺕِ، ﻓﺈﺫﺍ ﺧﺮﺝَ ﺭﻣﻀﺎﻥ ﺃﺗﺒﻌﻪ ﺑﺎﻟﺴﻴﺌﺎﺕِ ﻭﺍﻟﻐﻔﻼﺕِ ﻭﺍﻹﻋﺮﺍﺽ ﻋﻦ ﻃﺎﻋﺔِ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﻬﺬﺍ ﺩﻟﻴﻞٌ ﻋﻠﻰ ﻋﺪﻡ ﺍﻟﻘﺒﻮﻝ

🔹:በተቃራኒው ከሆነማ ረመዷን ወጣ ጊዜ ጥሩን ነገር መጥፎን የሚያስከትልበት ፣ በዝንጋቴዎች ፣ አላህን ከመታዘዝ በመሸሽ (የሚያስከትለው ከሆነ) ይህ ተቀባይነቱን ማጣቱን አመላካች ነው።»

📘 [ﻣﺠﺎﻟﺲ ﺷﻬﺮ ﺭﻣﻀﺎﻥ ❪١١٩❫ ]

🔸:قال الشيخ صالح الفوزان حفظه الله أيضا: -
« لئن انتهى شهر رمضان فإن حق الله لا ينتهي إلا بالموت»

🔹:«የረመዳን ወር ቢያልቅ የአሏህ ሐቅ አያልቅም በሞት እንጂ።»

🔘 قال الله تعالى: {وَاعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّىٰ يَأْتِيَكَ الْيَقِينُ} [الحجر : 99]

🔸:عن أبي أيُّوب الأنصاري رضي الله عنه أن رسول الله ﷺ قال: ((مَن صام رمضان ثم أتبَعَه ستًّا من شوَّال، كان كصيام الدهر)) رواه مسلم

🔹:“ረመዳንን ፆሞ ከሸዋል ስድስት ቀን ያስከተለ ልክ አመት እንደፆመ ነው፡፡”

🔸:أن الحسنة تضاعف بعشر أمثالها

🔹:አንድ ሐሰና በአስር ይባዛል

🔸:قال تعالى፡ ﴿من جاء بالحسنة فله عشر أمثالها﴾

🔹:"በመልካም ስራ የመጣ ሰው ለእርሱ አስር ብጤዎቿ አሉት፡፡"

✅:ስለዚህ 30 የረመዳን ቀናት + 6 የሸዋል ቀናት = 36 ቀናት

36 x 10 = 360 ቀናት 360 ቀናት ማለት ደግሞ 1 አመት ሙሉ ማለት ነው።
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀ 📚
┊  ✿
🔗
❀ ✨                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP•
@Muslim_group2      
┣━━━━╗
❤️ ╔━━━━⎙
┣CH
L@Muslimchannel2
╠════•❁🎐❁
•═════╣
🌐 #SHARE_The_خ
ير🔺


🔠🔠🔠 🔠🔠🔠🔠🔠🔠🔠
💡💡💡💡💡💡💡💡🌟♥️

💥 تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال 💥

كل عام وانتم بخير 🌙✨

✨🐲🐲🐲🐲🦋🐲🐲🐲🐲✨

⭐️እንኳን ለ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣ኛው ኢድ-አል ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ⭐️

✅በዓሉ የሰላም የፍቅር የእዝነትና የመተሳሰብ ይሁንልን::

መልካም በዓ❤️

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤🌗ᢀ
@Muslimchannel2 💌


#መልዕክት ✉️

💌ስለነገው ዒድ አንዳንድ ነገሮችን እናውጋችሁ እስኪ:: የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ወደ ቡሀላ አካባቢ የምናስተላልፍ ይሆናል::#ግሩፑም(@Muslim_Group2)የሚከፈት መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን (የግሩፑ ህግ እንደተጠበቀ ሁኖ)::

📏📏📏📏🌟📏📏📏📏

:ወደ ዋና ጉዳያችን ስንመለስ ዒድ እንደማንኛውም ቀን አይደለም። ቀኑ ዉብ ነው። ደስታውም ብዙና ረጅም ነው። ከዋዜማው ጀምሮ በደስታና በናፍቆት የተሞላ ቀን ነው። ከተለመደው ቀን የተለየ በሚመስል መልኩ ጸሀይዋ ብሩህ ናት ፣ አየሩ ምቹ ነው ፣ ሌሊቱም የተለየ ሰላም ያለው ሌሊት ነው። የነገው ቀን ልዩ የደስታ ቀን እንደሆነ ልባችን በጽኑ ያምናል። ያ እምነታችን ነው ቀኑን ዉብ የሚያደረገው።

➡️#በዒድ ቀን ሀሳቦቻችንንና ፈተናዎቻችን ራቅ እናደርጋለን።

➡️#በዒድ ቀን ሀዘናችንን እና የውስጥ ህመማችንን ዋጥ አድርገን ፈገግታችንን እና ሳቃችንን ብቻ ለሰዎች እናጋራለን።

➡️ለዚያም ነው ዒዱ የደስታ ቀን የሚሆነልን

🌤 ወዳጆቼ ሆይ ৲

ሁሌም ደስ ይበላችሁ ፣ ሁሌም እንደ ዒድ ይሁን ኑሯችሁ

🌿ስለ ዒድ አል ፊጥር በዓል የተወሰኑ ሱናዎችን በመረጃ እንይ

1️⃣.ለዒድ ቀን ማማርና መዋብ

🔸:عن ابن عباس رضي الله عنهما قال:
((كان رسول الله ﷺ يلبسُ يومَ العيدِ بردةً حمراءَ)) السلسلة الصحيحة - رقم: (1279)  الألباني : إسناده جيد

2️⃣.ለዒድ ሰላት ከመውጣታችን በፊት ገላን መታጠብ

🔸: عنْ نَافِعٍ :
(( أَنَّ عَبْدَ اللَّهِ بْنَ عُمَرَ رضي الله عنه كَانَ يَغْتَسِلُ يَوْمَ الْفِطْرِ قَبْلَ أَنْ يَغْدُوَ إِلَى الْمُصَلَّى)) موطأ مالك - رقم : (384) صححه الألباني في الإرواء

3️⃣.ለዒድ ሰላት ከመውጣታችን በፊት በቴምር ማፍጠር

🔸: عنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رضي الله عنه ، قَالَ:
((كَانَ رَسُولُ اللَّهِ ﷺ َلا يَغْدُو يَوْمَ الْفِطْرِ حَتَّى يَأْكُلَ تَمَرَاتٍ. ويأكلهن وِترا))ً صحيح البخاري - رقم: (953)

4️⃣.ወደ መስገጃ ቦታ በእግር መሄድ እና በእግር መመለስ

🔸: عنِ ابْنِ عُمَرَ، رضي الله عنهما، قَالَ:
(( كَانَ رَسُولُ اللَّهِ ﷺ يَخْرُجُ إِلَى الْعِيدِ مَاشِيًا، وَيَرْجِعُ مَاشِيًا)) حسنه الألباني في صحيح ابن ماجه - رقم : (1078)

5️⃣.ሶላቱል ዒድ የሚሰገደው ከመስጂድ ውጪ በሰፊ ሜዳ ላይ ወይም የዒድ መስገጃ ላይ መስገድ

🔸: عنْ ابْنِ عُمَرَ رَضِي اللَّهُ عَنْهُمَا، قَالَ
(( أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ كَانَ يَغْدُو إِلَى الْمُصَلَّى فِي يَوْمِ الْعِيدِ، وَالْعَنَزَةُ تُحْمَلُ بَيْنَ يَدَيْهِ، فَإِذَا بَلَغَ الْمُصَلَّى نُصِبَتْ بَيْنَ يَدَيْهِ، فَيُصَلِّي إِلَيْهَا، وَذَلِكَ أَنَّ الْمُصَلَّى كَانَ فَضَاءً لَيْسَ فِيهِ شَيْءٌ يُسْتَتَرُ بِه))ِ صححه الألباني في صحيح ابن ماجه - رقم: (1084)

6️⃣.ሲሄዱ በአንድ መንገድ ፤ ሲመለሱ ደግሞ በሌላ መንገድ መመለስ

📌:ዑለማዎች ሰለዚህ ተግባር ሚስጥር ሲናገሩ ሁለቱም መንገዶች መስካሪ እንዲሆኑና እንዲሁም የኢስላም መገለጫዎችን ይበልጥ ይፋ ለማድረግ ነው ይላሉ፡፡

🔸:عنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، رَضِي اللَّهُ عَنْهُمَا، قَالَ :
(( كَانَ النَّبِيُّ ﷺ إِذَا كَانَ يَوْمُ عِيدٍ خَالَفَ الطَّرِيق ))َ صحيح البخاري - رقم : (986)

7️⃣.ከዒድ ሌሊት ጀምሮ እስከሚሰገድ ድረስ ተክቢራ ማድረግ

🔸:عن الزهري :
(( أَنَّ رَسُولَ اللهِ ﷺ كَانَ يُخْرِجُ يَوْمَ الفِطَرِ فَيَكْبُرُ حَتَّى يَأْتِي المُصَلَّى، وَحَتَّى يَقْضِي الصَّلَاةَ، فَإِذَا قَضَى الصَّلَاةَ قَطْعُ التَّكْبِيرِ ) السلسلة الصحيحة - رقم: (171)  قال الألباني إسناده صحيح مرسل له شاهد موصول يتقوى به .

8️⃣.የዒድን ኹጥባ ማዳመጥ

🔸:عن عبد الله ابن السائب رضي الله عنه قال :
(( حَضٓرَتْ العِيدَ مَعَ ر
َسُولِ اللهِ ﷺ فَصَلَّى بِنَا العِيدُ ثُمَّ قَالَ قَدْ قَضَيْنَا الصَّلَاةَ فَمِنْ أُحِبُّ أَنْ يَجْلِسَ لِلخُطْبَةِ فَلِيَجْلِسْ وَمِنْ أُحِبُّ أَنْ يَذْهَبَ فَلِيَذْهَبْ)) صححه الألباني في صحيح الجامع - رقم : (4376)

9
️⃣.የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቶች

🔸:عن جبير بن نفير رضي الله عنه قال
(( كَانَ أَصْحَابُ النَّبِيِّ ﷺ  إِذَا اِلْتَقَوْا يَوْمَ العِيدِ يَقُولَ بَعْضُهُمْ لِبَعْضِ: تُقُبِّلَ اللهُ مِنَّا وَمِنْكَ )) صحح إسناده الألباني في تمام المنة - رقم: (354)

1️⃣0️⃣.ከዒድ ሶላት መልስ ሁለት ረከዓ መሰገድ

🔸: عن أبي سعيد الخدري رضي الله عن
ه قال :
(( كَانَ رَسُولُ اللهِ ﷺ لَا يُصَلِّي قَبْلَ العِيدِ شَيْئًا فَإِذَا رَجَعَ إِلَى مَنْزِلِهِ صَلَّى رَكْعَتَيْنِ )) حسنه الألباني في صحيح ابن ماجه -
رقم: (1076)

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤🌗ᢀ @Muslimchannel2 💌


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
Allah doesn't need YOU!

:ወላሂ ከልቤ ነው የምነግራችሁ እንደዚህ ህይወቴን የለወጠው ዳዕዋ የለም አልሰማሁም አላዳመጥኩም:: ይህ #ዳዕዋ እኔጋ ከደረሰ የዛሬ 2-3 አመት አካባቢ ሁኖታል:: እስካሁን ድረስ ደግሜ ደጋግሜ አየዋለሁ , ከአላህ ራህመት ተስፋ እንዳልቆርጥ እጅግ በጣም የረዳኝ ዳዕዋ ነው:: እስኪ ልባችሁን ሰጥታችሁ አድምጡልኝማ ! ሰምታችሁ እንደምትጠቀሙበት ምንም ጥርጥር የለኝም !

#EnglishVersion

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤🌗ᢀ
@Muslimchannel2 💌


የዛሬዋ 27ተኛ ሌሊት . . .🟥

በብዙ ኢስላማዊ ሊቃውንቶች ዘንድ የዛሬዋ 27ተኛ ሌሊት ለይለቱል ቀድር የሚገኝባት ሌሊት ነች ተብሎ ይገመታል::



“97:1” እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው፡፡

“97:2” መወሰኛይቱም ሌሊተ ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ

“97:3” መወሰኛይቱ ሌሊት
#ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡

“97:4” በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ

“97:5” እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡

🌇🌇🌇🌇🌇🌇🌇🌇

🔺በዝህች ሌሊት የሚከናወኑ ዒባዳዎች መልካም ስራዎች በሙሉ በ1000ሺ ወራት (83 አመት) ከሚሰሩ መልካም ስራዎች ይበልጣሉ:: ይህ አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ የሰጠን ትልቅ ስጦታ ነው:: ስጦታውን በአግባቡ መጠቀም ያለ መጠቀም የኛ ፋንታ ነው:: በዝህች ሌሊት 1 ገፅ የሚቀራ ቁርዓን ከላይ እንዳየነው ምንዳው እጅግ በጣም ትልቅ ነው:: የዝህችን ሌሊት እያንዳንን ሰከንድ በአግባቡ በዚክር , ቁርዓን በመቅራት , የተለያዩ መልካም ስራዎችን በመስራት ልናሳልፋት ይገባል::

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤🌗ᢀ
@Muslimchannel2 💌


➡️ጀነትን የምትገባው በአላህ እዝነት እንጅ በሰራኽው መልካም ስራ አይደለም :: ጀነት ውስጥ ከገባህ ቡሀላ ደረጃህን ከፍ ዝቅ የሚያደርግው መልካም ስራህ ነው::

🟧ስለዚህ መልካም ስራህ ጀነት ለመግባት ዋስትና አይሆንህም:: የአላህ #እዝነት ቢሆን እንጅ::

عَنْ عَائِشَةَ زَوْجِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قالت قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ سَدِّدُوا وَقَارِبُوا وَأَبْشِرُوا فَإِنَّهُ لَنْ يُدْخِلَ الْجَنَّةَ أَحَدًا عَمَلُهُ قَالُوا وَلَا أَنْتَ يَا رَسُولَ اللَّهِ قَالَ وَلَا أَنَا إِلَّا أَنْ يَتَغَمَّدَنِيَ اللَّهُ مِنْهُ بِرَحْمَةٍ وَاعْلَمُوا أَنَّ أَحَبَّ الْعَمَلِ إِلَى اللَّهِ أَدْوَمُهُ وَإِنْ قَلَّ
صحيح البخاري

╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤🪴 [
@Muslimchannel2]🎐

Показано 20 последних публикаций.