የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የስራ ሀላፊዎች የሐዋሳ ዲስትሪክትና ቅርንጫፍ ደንበኞችን ጎበኙ።
በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ሆልሴልና ሪቴይል ቺፍ ኦፊሰር አቶ ግርማ ፈቀደ የተመራ ልዑክ ከባንኩ ደንበኞች ጋር ተወያይቷል። ሉዑኩ የባንኩ ሐዋሳ ዲስትሪክትና ቅርንጫፍ ባንኮችን እንቅስቃሴም ተመልክቷል።
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የጀመረውን አዲስ ጉዞ ወደላቀ ከፍታ ለማድረስ ሁሉ አቀፍ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል።
ከእነዚህም ዲስትሪክትና ቅርንጫፍ ባንኮቹን በቅርበት በመደገፍ የተሻለ አፈጻጸም እንዲያስመዘግቡ ማድረግ ይገኝበታል።
በዚህም በቺፍ ኦፊሰሩ የተመራው ልዑክ በሐዋሳና ዙሪያው ከባንኩ ጋር አብረው እየሰሩ የሚገኙ ተቋማትን ተዘዋውረው ተመልክቷል። ደንበኞችም በጉብኝቱ ደስተኞች መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን አብሮ ለመስራት ያላቸውንም ፍላጎት አሳውቀዋል።
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!
#Nib #Nibinternationalbank #nibbank #HawassaDistrict
Facebook / Instagram / linkedin / X / Youtube / Tiktok / Website