አንደበታችንን_እንጠብቅ!
አፉ ውስጥ ያለችውን ይህችን ትንሽዬ ብልት መቆጣጠር የማይችል ሰው ህይወቱ በመከራ እና በብስጭት የተሞላ መሆኑ የማይቀር ነው። ከአንደበታችን የሚወጡት ቃላቶች ከሰይፍ የላቀ፣ ከፈንጂ የባሰ ጉዳትን የማስከተል አቅም አላቸው።
👉 ይህ መጽሐፍ የአንደበት ኃጢአት ምን ያህል የከፋ እንደሆነ እንዲሁም አቅጣጫውን የሳተን አንደበት እንዴት መግራት እንደሚቻል ያስተምራል።
#ማሳበባችንን_እንተው!
ማንኛውንም ውድቀት ላለመቀበል ሁሉንም ዓይነት ሰበቦች እና ምክንያቶችን እናመጣለን። ይህም ከስህተታችን እንዳንማር ያደርገናል። ለማሳበብ ለማሳበብማ አዳም ሔዋን ላይ አሳቧል፤ ሔዋንም እባብ ላይ አሳባለች… ታዲያ ማን ከእርግማኑ ተረፈ?
👉 በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሰበብን መንገድ መከተላችን ውድቀት ወደተባለው አዳራሽ እንጂ ወደ ስኬት እንደማይመራን እንማራለን።
ፀሎት_አየራችን_ይሁን
ፀሎት ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት ዋነኛው መንገድ ነው… ከፀሎት ጋር ያልተቆራኘ ህይወት አየር በሌለበት ቦታ ላይ እንደመኖር ይቆጠራል! የጭንቀት እና የስጋት ሰንሰለት የትም እንዳንሄድ፣ ምንም ብሩህ ነገር እንዳናስብ ተብትቦ ይይዘናል፤
👉 ፀሎት እንዴት ይህንን የብረት ሰንሰለት ማቅለጥ እንደሚችል እንማርበታለን።
ጭንቀት_በእግዚአብሔር_ላይ_ማመጽ_ነው
አምላካችን እግዚአብሔር ጭንቀታችንን ሁሉ ለእሱ እንድንተው መክሮናል። እኛ ግን ብዙ ጊዜ በጭንቀት ራሳችንን ስናሳምም ነው የምንገኘው። የታዘዝነውን ከማድረግ ይልቅ በተፈጠረብን ችግር አማካይነት ሳናውቀው በተቃውሞ ውስጥ እንገባለን። የጭንቀት መድሃኒቱ የሚያስጨንቀንን ነገር ሁሉ ለአምላካችን መተው ነው።
👉መጽሐፉ እንዴት ጭንቀታችንን በእግዚአብሔር ላይ መጣልና እኛ በእፎይታ ማረፍ እንደምንችል ያስተምረናል።
መድኃኒታችንን_እንዋጥ
ይቅርታ ከብዙ በሽታዎች የሚፈሰው መድኃኒት ነው፡፡ ራሳችንን ከመመረዝ ነጻ ማውጣት የምንችለው በይቅርታ ነው፡፡ ይቅርታ ልክ የተቀደደ ልብስን እንደሚሰፋ የሚያውቅ መርፌ ዓይነት ነው። በየቀኑ የይቅርታን መድኃኒት እየዋጥን መፈወስ ስንችል ለምን ይሆን ራሳችንን የምንመርዘው?
👉 ይህ መጽሐፍ የይቅርታን ኃያልነት እንዲሁም የደደረ ልብ የሚያመጣውን ስቃይ አስገራሚ በሆኑ ታሪኮች እያዋዛ ያቀርባል!
© አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ