በድሮን ጥቃት ሚስታቸውን ጨምሮ 8 ቤተሰባቸውን አጥተዋል 🥲
…..*…..
የብልጽግናው መንግስት የጦር ወንጀል በንጹሀን ህዝብ ላይ ቀጥሏል ‼️
…..*…..
አቶ ንጉሥ በለጠ በድሮን ጥቃት በአንድ ጀምበር ሕይወታቸው ከተመሳቀለባቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ ናቸው።
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ባለቤታቸውን ጨምሮ ስምንት ቤተሰቦቻቸው እንደተገደሉባቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የካቲት 11/2016 ዓ.ም. ሞጃ እና ወደራ ወረዳ ‘አይሱዙ’ በተባለ ተሽከርካሪ ላይ በተፈጸመው የድሮን ጥቃት ከሳሲት ወደ ጋውና ሲጓዙ የነበሩ ከ20 በላይ የአንድ ቤተሰብ አባላት እና ቤተ ዘመድ ሕይወት አልፏል።
“ድሮን ጣለ” ሲባል ሰምተው ስፍራው ላይ በአፋጣኝ የደረሱት አቶ ንጉሥ “[ስደርስ] ባለቤቴን ወድቃ አገኘኋት። ከዚያ በኋላ ራሴን አላውቅም፤ [ራሴን] ስቻለሁ። እንዴት ልሁን፣ ምን ልሁን በወቅቱ አላስታውስም። ወደ ጻድቃኔ ጸበል ገብቼ ነው ከ40 ቀን በኋላ ትንሽ መረጋጋት የጀመርኩት” ይላሉ።
በዚህ የድሮን ጥቃት ባለ ክርስትናው ህጻን በአያቱ እቅፍ ሆኖ የተረፈ ሲሆን፤ አብረው ተቀምጠው የነበሩ እናቱን ጨምሮ በርካታ የቤተሰብ አባላት ግን ተገድለዋል።
Source : BBC Amharic