መረጃ ቲቪ ከአየር ላይ መውረዱ፤ ያሳደረብን ሐዘንና ሊሰመርበት የሚገባው እውነት!
በእውነት አዝነናል! መረጃ ቲቪ ከአየር ላይ መውረዱን ስንሰማ ልባችን በሐዘን ተሰበረ። ይህ ቴሌቪዥን ለአማራ ሕዝብ ድምጽና የመረጃ ምንጭ የነበረ የሕዝባችን ተወዳጅ የትግል አጋር ነበር። በተለይም በአማራ ፋኖ ትግል ውስጥ ያለው አስተዋጽኦ ወደር የሌለው ነው።
መረጃ ቲቪ የብዙዎቻችን የዕለት ተዕለት መረጃ ምንጭ ብቻ አልነበረም። የፋኖ መዋቅሮች መመሪያዎችን ሲያስተላልፉ፣ ወገናችን በየቦታው ሲሰቃይና ሲፈናቀል በተለይ በአስቸጋሪ ወቅት እውነተኛውን መረጃ የምናገኝበት ብቸኛ መድረክ ነበር። ዛሬ ይህ ድምጽ በጊዜያዊነትም ቢሆን ጸጥ ማለቱ በእጅጉ አሳዝኖናል።
በተለይም በዚህ ወቅት ቴሌቪዥኑ ከአየር ላይ መውረዱን ተከትሎ የሚደሰቱና የሚፈነጥዙ መኖራቸው እጅግ ያሳዝናል። እንዲህ ዓይነት የደስታ ስሜት የሚሰማቸው አካላት መረጃ ቲቪ ለአማራ ሕዝብ ምን ማለት እንደሆነ ያልገባቸው መሆኑን ያሳያል። የዚህ ቴሌቪዥን ዋጋ እጅግ የከበረ ነው። ፋኖ በየቦታው ለሚያደርገው ተጋድሎ፣ ሕዝቡን ለማነቃቃትና ለማስተባበር የነበረው ሚና የሚዘነጋ አይደለም።
መረጃ ቲቪ የብዙ ወገኖቻችን ድምጽ የነበረ፣ የነጻነት ትግላችን አካል እንደነበር ልንዘነጋ አይገባም። ዛሬ በጊዜያዊነት ከአየር ላይ መውረዱ ሊያሳዝነን እንጂ ሊያስደስተን አይገባም።
በመጨረሻም መረጃ ቲቪ በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚመለስ ተስፋ እናደርጋለን። እስከዚያው ድረስ ግን ይህንን ቴሌቪዥን ስናስብ የነበረውን እውነትና ያበረከተውን አስተዋጽኦ በልባችን ልናኖር ይገባል።
ታጋይ አምሓራ

ነፃነት በትግል እንጂ በልመና አይገኝም!