የአብይ አገዛዝ በፍርሃት ቆፈን ውስጥ - እኛ ግን እንመጣለን!
የአብይ አህመድ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ የሀገሪቱን ሙሉ ድሮኖች አዝምቶ ሕዝባዊ ትግሉን ለመግታት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ይሁንና ሕዝባዊ ተቃውሞው ጫና ይነሳብኛል በሚል የተረበሸው አገዛዙ፣ አዲስ አበባ ላይ ድሮኖችን እንደሚያሰማራ በመግለጽ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ መግባቱን በራሱ አረጋግጧል። ይህ እርምጃ፣ አገዛዙ በሕዝባዊ ኃይል ምን ያህል እንደተሸበረና ሥልጣኑን ለማቆየት ምን ያህል እንደተጨነቀ የሚያሳይ ነው::
አገዛዙ የአማራን ሕዝብ ትግል እጅግ በብዙ ሃይል በአጭሩ ለማስቀረት ያደረገው ሙከራ ከከሸፈና ትግሉ ተቀጣጥሎ ከቀጠለ በኋላ፣ አሁን ደግሞ አዲስ አበባን ለማሸበር እየተዘጋጀ ነው። ይህ የሚያሳየው አገዛዙ ፍርሃት እንደተጫነውና ከሕዝባዊ ተቃውሞ የሚመጣውን ለውጥ መቋቋም እንደማይችል ነው። ነገር ግን ይህ ፍርሃትና ዛቻ የትግላችንን እሳት ሊያጠፋው እንደማይችል የአዲስ አበባ ህዝብ ሊገነዘብ ይገባል።
የአዲስ አበባ ሕዝብ ይህን አፈናዊ ድርጊት በጽናት እንዲቋቋም ጥሪ እናቀርባለን:: አዲስ አበባ የለውጥ ማዕከል እንደሆነች እናውቃለን። የአዲስ አበባ ሕዝብ ለአመታት የጭቆናና የድህነት ኑሮ ሲገፋ ቆይቷል። አሁን ደግሞ አገዛዙ ይህን ሕዝባዊ ቁጣ በድሮን ለማፈን መነሳቱ አሳፋሪ ነው። ነገር ግን አዲስ አበቤዎች ለዚህ ጫና ተሸንፈው ወደ ኋላ እንደማይመለሱ እናውቃለን።
ያም ሆነ ይህ፣ የአብይ አገዛዝ ለጊዜው በድሮን ይጠበቅ፣ ይሸሸግ፣ እኛ ግን እንመጣለን! የአዲስ አበባ ሕዝብም ለነጻነቱ ይነሳል!
ታጋይ አምሓራ
03/5/2017 ዓ.ም

ነፃነት በትግል እንጂ በልመና አይገኝም!
03/5/2017 ዓ.ም