''ሳዑድ አረቢያ ሶሪያን የመርዳት ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት አላት'' - አህመድ አልሻራ
የሶሪያ ጊዚያዊ የሽግግር ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት አሕመድ አልሻራ የመጀመሪያ የውጭ ሀገር ጉዟቸውን በሳዑዲ አረቢያ አድርገዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በሪያድ ከልዑል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሳልማን ጋር ባደረጉት ውይይት፤ በጦርነት የተጎዳቸውን ሶሪያን መልሶ በመገንባት ዙሪያ ሰፋ ያለ ጊዜ ወስደው ተነጋግረዋል ተብሏል፡፡
''ሳዑድ አረቢያ ሶሪያን የመርዳት ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት አላት'' ሲሉም ተናግረዋል።
ባሳለፍነው ታህሳስ ወር ላይ የበሽር አላሳድን መንግስት በኃይል ገርስሰው ስልጣን የተቆጣጠሩት አልሻራም፤ የሽግግር ፕሬዝዳንት ተደርገው ሲመረጡ የመጀመሪያው የደስታ መግለጫ የተላከላቸው ከሳውድው ንጉስ ሳልማን ነበር፡፡ #brecorder
@ThiqahEth