በሶሪያ ቢያንስ 15 ንጹሐን በቦምብ ጥቃት ተገደሉ፡፡
በሰሜናዊ ሶሪያ በምትገኘው የማንቢጅ ከተማ መኪና ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተዘግቧል፡፡
የጥቃቱ ሰለባዎች በግብርና ስራ ተሰማርተው የሚኖሩ ሲሆኑ፤ ከስራ ሲመለሱ ጥቃቱ እንደተፈጸመባቸው የዓይን እማኞች ተናግረዋል።
ከሟቾቹ መካከል 14ቱ ሴቶች ሲሆኑ፣ አንዱ ደግሞ ወንድ ነው ተብሏል፡፡
ምንም እንኳን በከተማዋ በቱርክ የሚደገፉ የሶሪያ ታጣቂዎች እና በአሜሪካ የሚደገፉ የኩርድ ታጣቂዎች ግጭት ውስጥ ቢገኙም ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነት የወሰደ አካል ግን የለም፡፡ #sananewsxgency #apnews
@ThiqahEth