የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት መሐመድ ዓሊ ዩሱፍ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ።
ከአውሮፓውያን 2005 ጀምሮ ጅቡቲን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት ዩሱፍ፣ በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ በተካሔደውና ብርቱ ፉክክር በታየበት፣ እስከ ሰባተኛ ዙር ድረስ በዘለቀ ምርጫ ሁለት ሦስተኛ ድምጽ በማግኘት ማሸነፍ ችለዋል።
የ60 አመቱ ዩሱፍ፣ የኬንያውን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ እና የማዳጋስካር የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶን በማሸነፍ ኮሚሽኑን ለአራት ዓመታት እንዲመሩ ተመርጠዋል።
መሐመድ ዓሊ ዩሱፍ በአፍሪካ አህጉር ለረጅም ዓመታት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ብቸኛ ሰው ናቸው። #au #radiotamazuj
@ThiqahEth