Tom information


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


"Stay informed with our social media platform , bringing you the latest news and information from around the world!"

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций




#ጥቆማ

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም በአማራጭ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም (Alternative Teachers' Training Program) ለዘጠኝ ወራት ሰልጥነውና ውል ፈርመው በተለያዩ ክልሎች በመምህርነት ለማገልገል የሚፈልጉ አመልካቾችን ተቀብሎ በመደበኛ ፕሮግራም #ወጪያቸውን_ሸፍኖ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

የስልጠና ዘርፎች
➻ Biology
➻ Chemistry
➻ Mathematics
➻ Physics
➻ History
➻ Geography
➻ Citizenship
➻ Economics
➻ Agriculture
➻ Performing & Visual Arts
➻ English Language
➻ Information Communication Technology

የማመልከቻ መስፈርቶች፦
● አመልካቾች ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የመጀመርያ ዲግሪ ያላቸው እና የመውጫ ፈተና ያለፉ
● ከተማሩበት ዩኒቨርሲቲ የኦፊሺያል ትራንሰከሪፕት ማስላክ የሚችሉ
● በመምህርነት ለማገልገል ፍላጎት ያላቸው
● ከግል ትምህርት ተቋማት የተመረቁ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃቸው ትክክለኝነት ከትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው 👇
መስከረም 25/2019 ዓ.ም

ያመልክቱ 👇
https://forms.gle/PhDzQiRbRjkrRcRp8

ከላይ በተገለፀው ሊንክ ላይ በመግባት አስፈላጊ መረጃዎችን በመሙላትና የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን በማያያዝ ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።

ለሴት አመልካቾች እንዲሁም የመኝታ እና የምግብ አገልግሎት ለማይፈልጉ ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡


የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ያደረገውን ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታ 10 ለ 0 አሸነፈ

AMN-መስከረም 23/2019 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ያደረገውን የወዳጅነት ጨዋታ 10ለ0 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዳግማዊት ሰለሞን ሦስት ግቦችን በማስመዝገብ ሃትሪክ ሰርታለች።

እሙሽ ዳንኤል (2) ፣ ቤተልሄም በቀለ ፣ ቤተልሄም መንተሎ ፣ ቱሪስት ለማ ፣ ረድኤት አስረሳኸኝ እና አሻንቲ ማሪ (በራሷ ላይ) ሌሎች ግቦችን አስቆጥረዋል።

ሉሲዎቹ ከቀናት በፊት በተመሳሳይ ሲሸልስን ገጥመው 16ለ0 አሸንፈው ነበር።

ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣይ ለ2028ቱ ኦሊምፒክ ለማለፍ ከሩዋንዳ ጋር የ2ኛ ዙር ማጣሪያ ጨዋታውን ያደርጋል።


በ5 ክልል የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊደርስ እንደሚችል ቅድመ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በ2019 ዓ.ም የበጋ ወቅት (ከጥቅምት እስከ ጥር) በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሊከሰት የሚችለውን የመሬት መንሸራተትና ናዳ አደጋ ለመከላከል የሚያስችል ብሔራዊ ቅድመ ማስጠንቀቂያ አውጥቷል።

በዚህም ፦

1ኛ). ማዕከላዊ ኢትዮጵያ

2ተኛ).ደቡብ ኢትዮጵያ

3ተኛ). ደበብ ምዕራብ ኢትዮጵያ

4ተኛ).ሲዳማ

5ተኛ). ኦሮሚያ

ይህ ማለት በተጠቀሱት ወረዳዎች ውስጥ ባሉ ሁሉም ቀበሌዎች የመሬት መንሸራተት ይከሰታል ማለት እንዳልሆነ ይታወቅ:: በተጠቀሱት ወረዳዎች ውስጥ ተጋለጭቀበሌዎችን የአካባቢው አስተዳደር ይሄንን መረጃ በመጠቀም በተጨማሪነት የመለየት፣ የማረጋገጥና፣ የአካባቢ ክትትል በንቃት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል

የኮሚሽኑ የሠንጠረዦች መረጃና ዝርዝር የመዋቅሮች ሥም ከታች ተያይዟል

ዶች ኤችዲ


የጂማ ዩኒቨርሲቲ የየተመደቡ አዲስ ገቢ (Freshman) ተማሪዎች ምዝገባ

ጂማ ዩኒቨርሲቲ
​ወደ ጂማ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ፦ የ2019 (2026/27) ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚካሄደው፦
​📅 ጥቅምት 4 እና 5 ቀን 2019 ዓ.ም. (October 14–15, 2026) ይሆናል።


አዲስ አበባ በሚገቡ ዋና ዋና መንገዶች ላይ ከዛሬ መስከረም 22 አስከ 24 ቀን ድረስ የጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የጉዞ ገደብ ተጣለ።

በሆራ ፊንፊኔ እና ሆራ አረሰዲ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል ምክንያት በማድረግ ታዳሚዎች በዓሉን ያለ ምንም የፀጥታ ስጋትና የትራፊክ አደጋ ነፃ ሁነው በሰላም እንዲያከብሩ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ዝግጅት ማጠናቀቁን ለብስራት ሬድዮ የላከው መረጃ ያሳያል፡፡

በዓሉ በሚከበርበት ወቅት የትራፊክ መጨናነቅንና አደጋን ለመከላከል ሲባልም ከመስከረም 22ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ መስከረም 24ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ በማንኛውም የጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የጉዞ ገደቦች መደረጋቸዉንም ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡ኮሚሽኑም በጊዚያውነት ተሸከርካሪዎቹ የሚቆሙበትን መስመሮች ይፋ አድርጋል፡፡በዚህም መሰረት

1. በሱሉልታ በኩል ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ በጫንጮ እና ፍቼ ከተሞች እንዲቆሙ

2. በገላን ገበያ በኩል ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ሽኖ እና ሰንዳፋ ከተማ፣

3. በቡራዩ በኩል ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ሆለታ ከተማ እንዲቆሙ፣

4. በሰበታ በኩል ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ደግሞ ወሊሶ ከተማ እንዲቆሙ ተወስኗል።

5. በተጨማሪም በአዳማ በኩል ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ እና ከአዲስ አበባ የሚወጡ ተሽከርካሪዎች በፍጥነት መንገድ ብቻ መጠቀም የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።

በሌላ በኩልም በቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ ያሉ የጉዞ አውቶብሶች፣ የታክሲዎች፣ የህዝብ ትራንስፖርት፣ የቤት ተሽከርካሪዎች እና ሌሎችም ከመስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በተዘጋጁላቸው በቂ የፓርኪንግ ቦታዎች ብቻ እንዲቆሙ ጥሪ አድርጋል፡፡

ከማቆሚያ ቦታዎች ውጭ፣ መንገድ ላይ እና በሆቴሎች ስር ማቆም በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ ተመልክቷል። ኮሚሽኑ በዓሉ ያለ ምንም የትራፊክ አደጋ እንዲከናወን ሁሉም አሽከርካሪዎች እና የንብረት ባለቤቶች አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።




ግብፅ የኢትዮጵያን ዲፕሎማት በ48 ሰዓታት ውስጥ ከካይሮ እንድወጡ አዘዘች‼

ኢትዮጵያ በነበራት ውሳኔ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የግብፅ ዲፕሎማት አህመድ ሞሀረም አህመድ ሱሊማንን «ፐርሶና ነን ግራታ» በማለት በ48 ሰዓታት ውስጥ ከሀገር እንዲወጡ ማዘዟን ተከትሎ፣ ካይሮ በአጸፋው በግብፅ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አማካሪ የሆኑትን ዲፕሎማት በተመሳሳይ የ48 ሰዓታት ጊዜ ውስጥ ሀገር ለቀው እንዲወጡ አዘዘች።

ግብፅ እርምጃውን ዓለም አቀፉን «የአጸፋ መርህ» ተከትላ የወሰደችው መሆኑን በመግለፅ፣ የኢትዮጵያን ውሳኔ «የሚያሳዝን» ስትል ተችታለች።

ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተከሰተው የዲፕሎማቶች መባረር እሰጣ ገባ እንዲሁም ቀደም ሲል ከኤርትራ ጋር የተቋረጠው ግንኙነት፣ የአፍሪካ ቀንድን የፖለቲካ እና የጸጥታ ውጥረት ወደ አደገኛ ምዕራፍ አሸጋግሮታል።


ሰበር ዜና ‼️ ኢትዮጵያ አንድ የግብፅ ዲፕሎማት በ48 ሰዓት ውስጥ ከሀገር እንዲወጣ አሳወቀች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ የግብፅ ኤምባሲ የዲፕሎማቲክ ሰራተኛ የሆኑትን አህመድ ሞሃራም አህመድ ሶሊማን “Persona Non Grata” በማለት ተቀባይነት የሌላቸው ዲፕሎማት መሆናቸውን በሰነዱ አሳውቋል።

በሰነዱ መሠረት፣ ውሳኔው በቪየና የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ስምምነት መሠረት የተላለፈ ሲሆን፣ ዲፕሎማቱ ማሳወቂያው ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ በ48 ሰዓታት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ተጠይቋል


📢 ማስታወቂያ

📌 በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ ለነበራችሁና አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ።

ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል አሁን ባለው ሁኔታ በክልሉ በሚገኙ 4ቱም የፌደራል ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነባሩ ነባር ተማሪዎችና አዲስ የተመደቡ ተማሪዎችን በጊዜያዊነት ከክልሉ ውጪ ወዳሉ ዩኒቨርሲቲዎች የመመደብ ሥራ እየሰራ እንዳለ ይታወቃል።

በመሆኑ በምደባው ሂደት የቀረቡ ቅሬታዎች የማጥራት ሥራ እየተሰራ ስለሆነ በጊዜያዊነት ወደ ተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች የምትገቡበትን ቀን እስክናሳውቅ ድረስ ባላችሁበት ሆናችሁ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳስባለን።

የትምህርት ሚኒስቴር


ሰበር

10 የኤርትራ ዲፕሎማቶችን  በ48 ሰዓት ከኢትዮጵያ ውጡ ተባሉ‼

​የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርትራ እያደረገች ያለችውን ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ የጥላቻ እንቅስቃሴዎች በመቃወም በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲውን ለመዝጋት መወሰኑን አስታወቀ።

በተጨማሪም በብሔራዊ ደህንነት ላይ ስጋት ደቅነዋል ያላቸውን 10 በኢትዮጵያ የሚገኙ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን «ላስፈላጊ» (persona non grata) በማለት በ48 ሰዓታት ውስጥ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዟል።

​ሚኒስቴሩ ኤርትራ ከተከታተለችው እርምጃ እንድትቆጠብ እያሳሰበ፣ ኢትዮጵያ አሁንም ለሰላማዊ አብሮ መኖር እና ለአካባቢያዊ መረጋጋት ዝግጁ መሆኗን ገልጿል። 


ነጻ የትምህርት ዕድል!

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ ትምህርት ዕድልን ለተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ ያለመ የነጻ ትምህርት ዕድል (Scholarship Opportunity) መስጠት መጀመሩን አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ለ2019 የትምህርት ዘመን በሁለተኛ ዲግሪ እና በመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ መርሐግብሮች በተለያዩ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ ሠራተኞችን አወዳድሮ በመቀበል በነጻ የትምህርት ዕድል ማስተማር ይፈልጋል፡፡

በምስሉ ላይ የተዘረዘሩ የ2ኛ ዲግሪ (Masters) እና የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት መስኮች ለመማር የተገለፁ የቅበላ መስፈርቶችን የምታሟሉ አመልካቾች እስከ ሰኞ መስከረም 25/2019 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

መስፈርቶችን የምታሟሉ አመልካቾች የስኮላርሺፕ ዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ከምትሰሩበት ተቋም የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የይጠበቅባችኋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት

ለማመልከት ስትሔዱ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒውን መያዝ አይዘንጉ፡፡

የ2ኛ ዲግሪ አመልካቾች ጊዜው ያላለፈበት ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም መግቢያ ፈተና (NGAT) ሰርትፍኬት ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡


ቀን፡ 21/01/2019 ዓ.ም
የተራዘመ ማስታዎቂያ
በ 2018 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁና በ 2019 ዓ.ም አዲስ ከትምህርት ሚኒስቴር የተመደባችሁ የ1ኛ ዓመትና የአቅም ማሻሻያ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 26 እና 27/2019 ዓ.ም ይከናወናል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ስም ዝርዝራችሁ ስላልደረሰን የምዝገባ ቀኑ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- የሌሎች ነባር መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ከዚህ ቀደም በተገለፀው መሰረት መስከረም 26 እና 27/2019 ዓ.ም ነው፡፡

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት


ትምህርት ሚንስቴር በመምህርነት መሰልጠን ለሚፈልጉ የመቁረጫ ውጤት ይፋ አድርጓል።
ሙሉ መረጃውን ከላይ ይመልከቱ።
አዩዘሀበሻ


በሰሜን ኬንያ የወደብ ከተማ ላሙ ለሚገነባው የነዳጅ ማጣሪያ ዛሬ ረቡዕ መሠረተ ድንጋይ የማኖር ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል።
የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለ ሃብት የሆኑት ናይጄርያዊው ቢልየነበር አሊኮ ዳንጎቴ የሚያስገነቡት የነዳጅ ማጣሪያ 16 ቢሊዮን ዶላር ያወጣል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ መሠረተ ድንጋይ በማኖር ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።
የፋብሪካው ግንባታ ሲጠናቀቅ በቀን 700,000 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ማጣራት ይችላል። በዚህም የፋብሪካው የኢንዱስትሪ አቅም በምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚው ይሆናል።
የመሠረት ድንጋይ ከመጣሉ በፊት የተወሰኑ የአካባቢው ነዋሪዎች አደባባይ ወጥተው ፋብሪካው ለሚገነባበት መሬት ተጨማሪ ካሳ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
ዳንጎቴ ግን ተቃውሞውን አጣጥለው የፋብሪካው ግንባታ በተያዘው ዕቅድ መሠረት እንደሚከናወን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የፋብሪካው ግንባታ በአውሮፓውያኑ 2030 እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተጨማሪ የኡጋንዳ፣ ቶጎ እና ቤኒን መሪዎች ተገኝተዋል።
ዳንጎቴ ለቀጣናው መንግሥታት በአጠቃላይ በፋብሪካው የ30% ድርሻን ይፋ ማድረጋቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
የፋብሪካው ግንባታ ሲጀመር ዳንጎቴ ባደረጉት ንግግር “አፍሪካውያን አፍሪካን ለመገንባት ተሰባስበዋል። ዛሬ እየጀመርን ያለነው ነዳጅ ማጣሪያ ብቻ አይደለም፤ አፍሪካ ብሩህ ተስፋ እንዲኖራት የኢንዱስትሪ ግንባታ አዲስ ምዕራፍ እየከፈትን ነው” ብለዋል።
በናይጄርያ ያላቸውን የነዳጅ ማጣሪያ ‘ሌኪ’ እንደ ምሳሌ በመጥቀስ “በላሙም እንደሚደገም” ገልጸዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማለዳውን ኬንያ ገቡ❗️

🇪🇹ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ጣቢያ የመሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓትን ለመካፈል ዛሬ ጠዋት ኬንያ ገብተዋል።


ሹመት‼️
የደሴ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ፤  ጃንጥራር አባይን በመተካት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ።
በተያያዘ ዜና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የተለያዩ ሹመቶችን ለከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አቅርበዋል።

በዚህ መሰረት ፡-

🔗 አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ እና ክህሎት ኃላፊ

🔗 አቶ ጥላሁን ከበደ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ በአዲስ አበባ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ፣

🔗 አቶ ሀፍታይ ገብረእግዚአብሄር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ፣

🔗 አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ በመሆን በከንቲባዋ የቀረቡ ናቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የቀረቡትን ሹመቶች አጽድቋል።



Показано 18 последних публикаций.