ፀደይ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሸሪአ አማካሪ ቦርድ ሰየመ፡፡
ፀደይ ባንክ ‹‹አርሂቡ›› በሚል ስያሜ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ይህንን ተከትሎም የሸሪአ አማካሪ ቦርድ ሰይሟል፡፡
አምስት አባላት ያሉት አማካሪ ቦርዱ ዛሬ ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ፕሬዚዳንት እና ፀኃፊ መርጧል፡፡
በዚህም መሠረት፣ ኡስታዝ አደም መሐመድን የአማካሪ ቦርዱ ፕሬዚዳንት እንዲሁም ኡስታዝ መሐመድ ማህሙድን ፀኃፊ አድርጎ መርጧል፡፡ ፕሮፌሰር አደም ካሚል፣ ሼህ ዑመር የህያ እና ሼህ መሐመድ ሰኢድ ደግሞ የሸሪአ አማካሪ ቦርዱ አበላት ሆነዋል፡፡
በዚሁ እለት የሸሪአ አማካሪ ቦርዱ ከባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ጋር ትውውቅ አካሂዷል፡፡ ለአማካሪ ቦርዱ አባላት የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ መኮንን የለውምወሰን፣ ‹‹በወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በኩል የተሻለ አገልግሎት ለማቅረብ እንተጋለን›› ብለዋል፡፡ ‹‹በርካታ አገልግሎቶችን ስንሰጥ የቆየን በመሆኑ ይህንን ልምድ በመያዝ የሸሪአውን ሕግ ተከትለን ጎላ ባለ መልኩ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎታችንን እናስቀጥላለን›› ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡
ፀደይ ባንክ አርሂቡ በሚል ስያሜ ከወለድ ነፃ የባንክ አገለግሎት ከመጋቢት 2016 ዓ.ም ጀምሮ መስጠት የጀመረ ሲሆን በሙከራ የትግበራ ጊዜውም ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት ማሰባሰብ ችሏል፡፡
#እንወዳጅ!
Telegram: https://t.me/tsedeybanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/tsedey-bank-s-c/
Facebook: https://www.facebook.com/TsedeyBankSC
የሁሉም ባንክ!
Bank for all!