መተውን የመሰለ ነገር የለም!
(አሌክስ አብርሃም)
ይታያችሁ ሴቶች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በቀን ብዙ ጊዜ የሚነካኩት የሰውነታቸው ክፍል ምናቸውን ይመስላችኋል? (ወንዶች አትባልጉ በቃ ከሱ ሌላ ሀሳብ የላችሁም?) ፀጉራቸው ነው። በትንሹ በቀን ከ96- 140 ጊዜ ይነካኩታል ይላል አንድ ጥናት። ምን ይሄ ብቻ አንዲት መደበኛ ሴት ፀጉሯን እንደነገሩ ለመንከባከብ (መታጠብ ፣ ማድረቅ መፈሸን ወዘተ) በሳምንት በትንሹ 9 ሰዓታትን ስትወስድ ለውበት ከፍ ያለ ቦታ የምትሰጥ ሴት ደግሞ እስከ 16 ሰዓት ታጠፋለች። በወር ካሰላነው 64 ሰዓት በዓመት 768 ሰዓት ማለት ነው። እንደኛ ባለው አገር የፀጉር ቤት ወረፋ ሲደመርበት የትየለሌ ነው። ይሄ የጊዜ ጉዳይ ነው ወደገንዘብ ከመጣን ለሻምፖ ኮንዲሽነር፣ የተለያየ ትሪትመንት፣ ለቀለም፣ ለቅባት፣ ለፍሸና አንዲት ሴት የምታወጣው ወጭ ጆሮ ጭው ያደርጋል። ይሄ ሁሉ ሆኖ አሳዛኙ ነገር የሴቶች ፀጉር ካለፉት አምስት አስርተ ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ጥንካሬው ብዛቱ እና ርዝመቱ በግማሽ ቀንሷል። ይህም ከመዋቢያ ኬሚካሎች፣ ከአየር ፀባይ ፣ ከአመጋገብ፣ ከውሃ ከአኗኗር ስታይልና እና ረፍት ከማጣት ጋር ይያያዛል። እና ምን ተሻለ ....ተማር ያለው ከዙሪያው ይማራል፤ የአውሮፓን ዴርማቶሎጅስቶች ዝብዘባ ተውትና ወዲህ ተመልከቱ!
ሰሞኑን "የኦነግ ሸኔ አባላት የነበሩ እጅ ሰጥተው ወደሰላም ተመለሱ" የተባሉ ሰወችን አይተናል፣ እነዚህ ሰወች በዱር በገደል ከረሙ የተባሉ ፣በጦርነት ያለፉ ወዘተ ናቸው እንደተነገረን። በሚገርም ሁኔታ ግን ከተማ ሴቶቻችን በፆም በፆሎት፣ በዘመነ ትሪትመንት ኢንች ማስረዘም የተሳናቸው ፀጉር እነዚህ ጫካ የከረሙ ተዋጊወች ላይ ተዘናፍሎና ትከሻቸው ላይ እየተርመሰመሰ የህንድን ዊግ አስንቆ መገኘቱ አስገራሚ አይደለም? ምን ቢያደርጉት ነው? ምንም! በቃ ስለተውት ነው! ቢበዛ ቅቤ ይቀቡት ይሆናል።
የእነዚህ ተዋጊወች እጅ መስጠት ለህብረተሰቡ ያስገኛል ከተባለው "ሰላም" ይልቅ ለሴት እህቶቻችን የፀጉር እንክብካቤ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው። እህቶቸ! ፀጉራችሁን የትም በሚመረት ኬሚካል ፍዳውን ከምታበሉት ጊዜና ገንዘባችሁን ከምታቃጥሉ መፍትሄው ቀላል ነው ተውት! መተውን የመሰለ ነገር የለም፤ ተፈጥሮ እድል ሲሰጣት ራሷን ማከም ትችላለች። (ደግሞ ፀጉር ለማሳደግ ብላችሁ ጫካ እንዳትገቡ...እናተና ውበትኮ...) እዳሪ መሬት ስለሚባል ነገር ሰምታችኋል? የተጎዳ እርሻን ለተወሰነ ጊዜ ሳያርሱ ሳይዘሩ ክፍቱን መተው ማለት ነው፤ ተፈጥሮ ታክመዋለች! በቀጣይ ሲዘራበት እንደጉድ ያመርታል። ያደከማችሁን ነገር እስኪ ተውት...ለሁሉም ነገር መተውን የመሰለ ነገር የለም። ለተፈጥሮ የማሪያም መንገድ ስጧት!
@wegoch
@wegoch
@paappii