ይቀጥላል ብለን እስካሁን ዝም ያልንው በደረሰብን ችግር ነዉ አሁን ከዛው እቀጥላለን ሼር ማድረጉን አይርሱ።
ሀብ ሲቲ ላይቭ ማነው?
ሀብ ሲቲ ላይቭ ይህ ፕሮጀክት ሲነሳ ተደጋግሞ የሚነሳ ስም
ነው፤ በአሜሪካ አገር የሚገኝ ድርጅትና የፕሮጀክቱ ሃሳብ
አፍላቂም ተደርጎ ይነገራል። ሀብ ሲቲ ላይቭ ማነው?
በእኛ በኩል ስለ ድርጅቱ ለማወቅ ጥረት ብናደርግም ጥቂት
ሰዎች ከወደዱት የፌስቡክ ገፅና በቅርቡ አገልግሎት
እንደሚሰጥ ከሚገልፅ ድረ -ገፅ
(www.hubcitylive.com) በስተቀር በቂና የተደራጀ
መረጃ ማግኘት አልቻልንም።
ይህንኑ አስመልክተን የጠየቅናቸው ሚኒስትር ዲዔታው
የቴክኖሎጂ ከተማ የመገንባቱን ሃሳብ በምክክር መድረኩ
ወቅት ያቀረበው ሚካኤል ካሚል የተባለ ጥቁር አሜሪካዊ
እንደሆነና በመስሪያ ቤቱም በተደጋጋሚ ሲመላለስ ያዩት
እርሱን እንደሆነ ገልጸውልናል።
ድርጅቱ ከኢትዮጵያ አሊያም ከመስሪያ ቤቱ ጋር የቀደመ የስራ
ግንኙነት ስለመኖር አለመኖሩም ዕውቅናው እንደሌላቸው
ተናግረዋል።
"ያገኙትን አፍሰው ቢበሉት፣
ያስቸግር የለም ወይ ሲውጡት" እንዳለችው ድምጻዊቷ
ይህ ባልሆነበት ሁኔታ እንዴት ስምምነት ላይ መድረስ ተቻለ
ያልናቸው ሚንስትር ዲዔታው፤
የአንድን ፕሮጀክት ተግባራዊነት ደረጃ የማወቂያ ጥናት
(Feasibility study) ሃሳባዊ፣ ቅድመ ትግበራና ትግበራ
በሚባሉ ሶስት ደረጃዎች ማለፍ እንደሚገባው ያብራራሉ።
በመሆኑም "ፕሮጀክቱ በሃሳባዊ ደረጃ ያለ በመሆኑ፤ ግንዛቤ
የመፍጠርና ፕሮጀክቱን የማስተዋወቅ ስራ ነው የሚሰራው፤
እኛም እሱ ላይ ነን" ሲሉ ይናገራሉ።
በዚህም መሰረት ጥቅምና ጉዳቱን፣ ማህበራዊ፣
ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊ ተግዳሮቶችና ሌሎች ጥናቶች
ይደረጋል፤ የጥናቱ ውጤት ታይቶ ፕሮጀክቱ ሊቀር ይችላል፤
በከፊል ሊስተካከል ይችላል፤ አሊያም እንዳለ ሊቀጥል
ይችላል።
ይህ ፕሮጀክትም ከሶስቱ የአንዱ እጣፈንታ ሊገጥመው
ይችላል ይላሉ።
ቴክኖ ቱሪዝምን፣ ፈጠራንና ኢንዱስትሪን ያስፋፋል ብለው
በማመናቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፕሮጀክቱን በሃሳብ
ደረጃ እንደተቀበለው ደጋግመው ያስረዳሉ።
የገንዘብ ምንጩ
20 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚፈጅ የተገመተለት ይህ
ፕሮጀክት ምንጩ ምንድን ነው?
አቅም ያላቸውና በዓለም ላይ የሚኖሩ ጥቁር ህዝቦች
ተባብረው ይገነቡታል፤ ዋናኛው የገንዘብ ምንጭም በተለያየ
ሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ጥቁር አሜሪካውያን ባለሃብቶች
እንደሚሆኑም ይታመናል።
ሃሳቡን የሚደግፉ ሁሉ ከተማዋን እንዲገነቡ ይደረጋል፤
በተለይ በአገር ውስጥ ያሉ ባለሃብቶች ድርሻ ከፍ እንዲል
ጥረት እንደሚደረግ ኮሚሽነር አቶ ጌታሁን መኮንን ይገልፃሉ።
"ድርጅቱ ሃሳቡን ይዞ የመጣው፤ ገንዘብ ማሰባሰብ
እንደሚቻል አምኖ ነው" የሚሉት ደግሞ ዶ/ር ሹመቴ ናቸው።
ከዚህ ቀደም ከድርጅቱ ጋር በነበራቸው ውይይትም
እውነተኛውን የቴክኖሎጂ ከተማ ለማየት ፍላጎት ያላቸው
በርካታ ግለሰቦች እንዳሉ ተገልጾላቸዋል።
በመሆኑም የሚጠቅም ሆኖ እስከተገኘ ድረስ እጃቸውን
አጣጥፈው የሚቀመጡበት ምክንያት እንደሌለና እንደ
መስሪያ ቤት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ
ያረጋግጣሉ።
"ይህ የሚሆነው ግን ጥናቱ ተጠናቆ መተማመኛ ሲገኝ ነው"
ይላሉ።
ይቀጥላል
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch
ሀብ ሲቲ ላይቭ ማነው?
ሀብ ሲቲ ላይቭ ይህ ፕሮጀክት ሲነሳ ተደጋግሞ የሚነሳ ስም
ነው፤ በአሜሪካ አገር የሚገኝ ድርጅትና የፕሮጀክቱ ሃሳብ
አፍላቂም ተደርጎ ይነገራል። ሀብ ሲቲ ላይቭ ማነው?
በእኛ በኩል ስለ ድርጅቱ ለማወቅ ጥረት ብናደርግም ጥቂት
ሰዎች ከወደዱት የፌስቡክ ገፅና በቅርቡ አገልግሎት
እንደሚሰጥ ከሚገልፅ ድረ -ገፅ
(www.hubcitylive.com) በስተቀር በቂና የተደራጀ
መረጃ ማግኘት አልቻልንም።
ይህንኑ አስመልክተን የጠየቅናቸው ሚኒስትር ዲዔታው
የቴክኖሎጂ ከተማ የመገንባቱን ሃሳብ በምክክር መድረኩ
ወቅት ያቀረበው ሚካኤል ካሚል የተባለ ጥቁር አሜሪካዊ
እንደሆነና በመስሪያ ቤቱም በተደጋጋሚ ሲመላለስ ያዩት
እርሱን እንደሆነ ገልጸውልናል።
ድርጅቱ ከኢትዮጵያ አሊያም ከመስሪያ ቤቱ ጋር የቀደመ የስራ
ግንኙነት ስለመኖር አለመኖሩም ዕውቅናው እንደሌላቸው
ተናግረዋል።
"ያገኙትን አፍሰው ቢበሉት፣
ያስቸግር የለም ወይ ሲውጡት" እንዳለችው ድምጻዊቷ
ይህ ባልሆነበት ሁኔታ እንዴት ስምምነት ላይ መድረስ ተቻለ
ያልናቸው ሚንስትር ዲዔታው፤
የአንድን ፕሮጀክት ተግባራዊነት ደረጃ የማወቂያ ጥናት
(Feasibility study) ሃሳባዊ፣ ቅድመ ትግበራና ትግበራ
በሚባሉ ሶስት ደረጃዎች ማለፍ እንደሚገባው ያብራራሉ።
በመሆኑም "ፕሮጀክቱ በሃሳባዊ ደረጃ ያለ በመሆኑ፤ ግንዛቤ
የመፍጠርና ፕሮጀክቱን የማስተዋወቅ ስራ ነው የሚሰራው፤
እኛም እሱ ላይ ነን" ሲሉ ይናገራሉ።
በዚህም መሰረት ጥቅምና ጉዳቱን፣ ማህበራዊ፣
ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊ ተግዳሮቶችና ሌሎች ጥናቶች
ይደረጋል፤ የጥናቱ ውጤት ታይቶ ፕሮጀክቱ ሊቀር ይችላል፤
በከፊል ሊስተካከል ይችላል፤ አሊያም እንዳለ ሊቀጥል
ይችላል።
ይህ ፕሮጀክትም ከሶስቱ የአንዱ እጣፈንታ ሊገጥመው
ይችላል ይላሉ።
ቴክኖ ቱሪዝምን፣ ፈጠራንና ኢንዱስትሪን ያስፋፋል ብለው
በማመናቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፕሮጀክቱን በሃሳብ
ደረጃ እንደተቀበለው ደጋግመው ያስረዳሉ።
የገንዘብ ምንጩ
20 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚፈጅ የተገመተለት ይህ
ፕሮጀክት ምንጩ ምንድን ነው?
አቅም ያላቸውና በዓለም ላይ የሚኖሩ ጥቁር ህዝቦች
ተባብረው ይገነቡታል፤ ዋናኛው የገንዘብ ምንጭም በተለያየ
ሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ጥቁር አሜሪካውያን ባለሃብቶች
እንደሚሆኑም ይታመናል።
ሃሳቡን የሚደግፉ ሁሉ ከተማዋን እንዲገነቡ ይደረጋል፤
በተለይ በአገር ውስጥ ያሉ ባለሃብቶች ድርሻ ከፍ እንዲል
ጥረት እንደሚደረግ ኮሚሽነር አቶ ጌታሁን መኮንን ይገልፃሉ።
"ድርጅቱ ሃሳቡን ይዞ የመጣው፤ ገንዘብ ማሰባሰብ
እንደሚቻል አምኖ ነው" የሚሉት ደግሞ ዶ/ር ሹመቴ ናቸው።
ከዚህ ቀደም ከድርጅቱ ጋር በነበራቸው ውይይትም
እውነተኛውን የቴክኖሎጂ ከተማ ለማየት ፍላጎት ያላቸው
በርካታ ግለሰቦች እንዳሉ ተገልጾላቸዋል።
በመሆኑም የሚጠቅም ሆኖ እስከተገኘ ድረስ እጃቸውን
አጣጥፈው የሚቀመጡበት ምክንያት እንደሌለና እንደ
መስሪያ ቤት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ
ያረጋግጣሉ።
"ይህ የሚሆነው ግን ጥናቱ ተጠናቆ መተማመኛ ሲገኝ ነው"
ይላሉ።
ይቀጥላል
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch