ልብ አንጠልጣዩ ተከታታይ ትረካ
ምዕራፍ 2 #ክፍል 1
...........እየቀረበኝ እንደሆነ ኮቴው ይነግረኛል ውስጤ ግን ቅንጣት ፍራቻ አልነበረበትምዝግጁ ነበር እኔ ያለሁበት ጠረጴዛ እጅግ ተቃርቧል ልቤ ባይፈራም የልብ ምቴ ግን አብዝቶ ጨምሯል በእልህ ከንፈሬን ነክሼ ሁኔታውን መጠባበቅ ጀምሬያለሁ ለሚመጣው ነገር ምላሽ ለመስጠት ሙሉ በሙሉ ነኝ መዳፌ ጠንከር ብሎ ቢላውን ጨብጧል በቀል ውስጤ እንደ ዘይት ይፈላል ቁጭት አንጀቴን ይበላኛል ምሬት ውስጤ ይርመሰመሳል ነገር ግን ሳላስበው እያላበኝ ነበር ከጥቂት እርምጃዎች በሗላ ካለሁበት እና ከተደበኩበት ሰፍራ ደርሷል እኔ ጋር ሲደርስም ቀጥ ብሎ ቆመ ጊዜ ሳያባክን ወዲያውኑ አጎንብሶ ላሲቲኩን ሲገልጠው...................
...በዛው ቅፅበት ወደሌላኛው ጠረጴዛ ስር ቦታ በመቀየሬ አላገኘኝም ነበር...አቋቋሙ ጀርባውን ለኔ ሰቶኝ መቆሙን በተረከዙ ተረዳሁ ከተደበኩበትም ጠረጴዛ ስር ቀስ ብዬ ወደሗላ ለመውጣት ሞከርኩ ከሗላዬ ያለው ነገር ቢኖር ግድግዳ እና ወደ ውጪ የሚያስወጣው መንገድ ብቻ ነው እዚ ቦታ ላይ ቆሜ ሰውዬው በሰከንድ ሽርፍራፊ ቢዞር እና ቢያየኝ የምሸሸግበት አንዳች ነገር የለም...እንቅስቃሴየሰን ለማድመጥ በሚመስል መልኩ በፀጥታ ቆሟል እኔም ካለሁበት ቦታ ፀጥ ብዬ ማሰብ ጀመርኩኝ ከዛም ቀስ አልኩና ገልጦ አይቷቻው ወዳለፈቻው ጠረጴዛዎች ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ ቦታ ቀየርኩ ተደብቄ የነበረበት ጠረጴዛ የመጨረሻው ነበርና የመያዝ እድሌ ሰፊ ነበር ቦታ ከመቀየሬ ቅፅበት የመጨረሻውን ጠረጴዛ በእግሩ መትቶ ገለበጠው ወዲያውኑ የያዘውን መጥረቢያ ባለ አቅሙ ወለሉ ላይ አላተመው ይመስለኛል እኔን እንዳገኘኝ እርግጠኛ ሆና ለኔ የሰነዘረው ነው...ነገር የያዘኝ አምላክ ሊተወኝ አይደለምና ተርፌያለሁ...በጣም የተበሳጨ ይመስላል የያዘውን መጥረቢያ በድጋሜ ወርውሮ ከግድዳው ጋር አላተመው...ሰውዬው ከሚፈጥረው ሁካታ በቀር ክፍሉ ጸጥ እንዳለ ነው በጣም በፈጠነ እርምጃ ወደነበረበት ከክፍሉ ሌላኛው ቦታ ሄደ በዚህ ጊዜ ከተሸሸኩበት ስፍራ ወጥቼ ራሴን ሸሽጌ ዙሪያ ገባዬን እየቃኘሁ የያዝኩትን ስለት አሰናድቼ እሱን መከተል ጀመርኩ...አሁንም ቢሆን በላስቲክ የተንጠለጠሉትን መለየት ለኔ ከባድ ነው ድንገት የሰማሁት ድምፅ እርምጃዬን ትቼ እንድቆም አደረገኝ ያ አረመኔ ሰውዬ ያንን የዋይታና የሰቆቃ ጩኸት ድምፅ ከፍቷል ይህን ድምፅ ስሰማ አብዝቼ እረበሻለሁ ጣቶቼ እርስ በእርስ መጨባበጥ አቅቷቸው ይብረከረካሉ ይሄ ድምፅ ድምፅ ብቻ አይደለም አንዳች የድግምት ሃይል አለበት ዋይታው በድንገት ፀጥ አለ ወዲያውኑ የተብረከረኩ ጣቶቼ ፀኑ አብዝተውም ጨበጡ ይህ ዋይታ ተሰምቶ ፀጥ ሲል ድምፅ ሲሰማ የሰውዬውን ፍጥነት አውቀዋለሁ ስለዚም ያለ አንዳች እንቅስቃሴ ባለሁበት ቆምኩኝ ዋይታው ጀመረ ወዲያውኑ አፍንጫዬን በሸፈንኩበት ከፊሉ ጨርቅ ወደ ጆሮዬ የሚመጣውን የዋይታ ድምፅ ላለመስማት ጆሮዬ ውስጥ ጠቀጠኩኝ ከዛም ቀጥ ብዬ ወደሰውዬው አመራሁ ምን እንደሆኑ ያላስተዋልኳቸው የላስቲክ እስሮች ብዛታቸው ወደ ሰላሳ ይጠጋል ወለሉ በእግሬ በርከክ ብዬ አንዱን የፊቴን ክፍል ከወለሉ ጋር አዋድጄ ሰውዬው የቆመበትን ቦታ አየሁት ጀርባውን ሰቶኝ ነው የቆመው በመሃላችን ያለው ልዩነት በጣም ጠቧል ልቤ ከመፍራት ይልቅ የያዝኩትን ቢላ እንድሰነቅርበት ይገፋኛል አንድ ነፍሴ በጥፋም አይገደኝ እያለች ታበረታኛለች ክንዴ ከጎልያድ ክንድ ይልቅ ጉልበታም ነኝ ይለኛል ብቻ አንዳች ሀይል ወደሰውዬው ገፋኝ ያንን አረመኔ ለማጥፋት እግሬ ተንደረደረ ጥርስ እና ጥርሴ በእልህ ተጋጩ የማላውቀው የማልቆጣጠረው ድፍረት ወደፊት ነዳኝ ብዙ ሰው ነፃ እንደሚያወጣ ለሀገሩ ሟች ንጉስ እንደሆንኩም ተሰማኝ አሁን ተጠንቅቄ ተጉዤ ከጀርባው ቆሚያለሁ ቢላውን ጎኔ ላይ ሻጥ አድርጌ አጠገቤ የነበረውን የብረት መዶሻ አንስቼ መሰንዘር ነበር የቀረኝ አደረኩት ጭንቅላቱ ላይ ባለ በሌለ ሃይሌ አሳረፍኩበት ነገር ግን አልወደቀም ነበር ይልቁኑ ዞሮ ሊያየኝ ዳዳው በዚህ ጊዜ ከጎኔ የሻጥኩትን ቢላ አውጥቼ ከማጅራቱ ትንሽ ዝቅ ብሎ ሰነቀርኩበት ከፊቱ የነበረው ጠረጴዛ ላይ በደረቱ ወደቀ ቢላውን ነቅዬ ደጋግሜ ወጋሁት ወጋጋሁት ጨከጨኩት የማቃሰት ድምፅ ያወጣል እንጂ አይጮህም ነበር ነገር ግን ቢላው አላረካኝም የስንቱን ህይወት የቀጠፈበት ያ ነፍሰ በላ መጥረቢያ ብልጭ አለብኝ ቀጥ ብዬም ተወርውሮ ወደ ወደቀበት ስፍራ አመራሁ አነሳሁት እሱ ያረገው እንደነበር መሬት ለመሬት እየጎተትኩ ያንን ሰቅጣጭ ድምፅ እያሰማሁ አንገቱን ቆርጬ ስጋውን ለአሞራ ልመግብ ተዘጋጅቻለሁ መጥረቢያውን ከፍ አድርጌ ትከሻዬ ላይ አስቀምጬ ነፍሱን ከስጋው ልለያት ጠረጴዛው ጋ ስደርስ የማየውን ማመን አቃተኝ ጠረጴዛና ወለሉ በደም ከመጨማለቅ ውጪ ሌላ አንዳች ነገር የለም ሰውዬው በቦታው ላይ አልነበረም በጣም ደነገጥኩኝ አንገቴን ሳላንቀሳቅስ አይኔ እስከቻለው አካባቢዬን ተመለከትኩ እሱ ተኝቶ ከነበረበት ጠረጴዛ አካባቢ የደም ነጥብጣብ አለ የነጠብጣቡ አቅጣጫ ርቆ እንዳልሄዴ ያሳያል ጠረጴዛው ላይ ቢላውም የለም "በቀሉ ይቅርብኝ ራሴን ላድን' ብዬ ከዛ ክፉና አረመኔያዊ ተግባር ከሚፈፀምበት መንደር ተስፋ ቆርጬ ነፍሴን ለማትረፍ እና ለመሸሽ ወስኜ መጥረቢያውን ጥዬ ስዞር...
ምዕራፍ 2 .P2...ይቀጥላል........
ከተመቻቹ ÷
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱