🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ፀሀፊ ✍️ ማኔ
ክፍል 2️⃣9️⃣
አይኔ ከጣራው ላይ ሳይነቀል ደቂቃዎች ተቆጠሩ ለመተኛት ሞከርኩ አቃተኝ በግራ በቀኝ በደረቴ በጀርባዬ ተኛሁአልቻልኩም።
ተነስቼ ወደውጭ ወጣሁ ልእልት ግቢ ውስጥ ጉልበቷን አቅፋ አንገቷን ጉልበቷ ውስጥ ቀብራ ስቅስቅ እያለች ታለቅሳለች ሳያት አሳዝናኝ ይሁን እኔጃ ግን አጠገቧ ሄድኩና ለምን ወደቤትሽ አልሄድሽም ምን ያስለቅስሻል አልኳት።ዘልዬ ወጥቼ ዘልዬ ልግባ እንዴ አለችኝ እንባዋን እየጠረገች ምን ችግር አለው ባይሆን አቅፌ ወርወር አድርግሻለሁ አትከብጅኝም አደል አልኳት ወዲያው ፈገግ አለችና እስቲ ሞክረኝ እከብድህ ይሆን እንዴ ብላ እጇን ዘረጋችልኝ አነሳኋት ከፊት ለፊቴ ቆማ ልቀፍህ እንዴ አለችኝ።
ገረመችኝ እኔ ምለሽ ልእልት ስንት አመትሽ ነው ነገረ ስራሽኮ የህፃን ነው ኩርፊያሽ አይለይ ሳቅሽ አይለይ ውስጥሽ ኩርፊያ አያውቅ ምንድነሽ ግን አልኳት፡፡ እኔ የጠየኩህኮ ሌላ ነው አለችኝ።
እሺ እቀፊኝ አልኳት ተጠመጠመችብኝ አንገቴ ስር ገብታ ውሽቅ አለች ትንፋሿ እንደሳት ይሞቃል እጇን ወገቤ ላይ አጣምራ አጥብቃ ያዘችኝ፡፡
እጄን ማን በወገቦቿ ዙሪያ እንዳሳረፈው አላውቅም ግን እኔም አቀፍኳት ለወራቶች ያህል አንዴ እንኳን እናቴን ባቀፍኳት ብዬ የተመኘሁት ምኞች እውነት የሆነ ያህል ጥምጥም አልኳባት በሰአቱ ባትለቀኝ ከእቅፏ ባታወጣኝ ብዬ ተመኘሁ፡፡ተቃቅፈን ለምን ያህል ደቂቃ እንደቆምን አላስታውስም አቅፊያት የእናቴን ትዝታዎች አስቤ መጨረሴን ብቻ ነው ማቀው ፡፡ድንገት ብንን እንዳለ ሰው ሆኜ እህህህ ልጂት እንደዚህ ቆመን እንደር ወይስ እንግባ ወደቤት አልኳት፡፡
አመሰግናለሁ እቅፍህ በራሱ ሰላም አለው ይልመድብህ አለችኝና ወደውስጥ ገባን እጇን በነጠላ ጨርቅ ጠቀለልኩላት ከውስጤ የሆነ ነገር እንደወጣ ያህል ቀለልብሎኛል።
እሷ በዛ ሁኔታ ውስጥ ሆና ተነስታ ልብሶቼን አዘገጃጅታ እዚህ ድረስ ከመጣህ አይቀር ሻወር ውሰድና ልብስ ቀይር መቼስ በሰባራ እጄ አዘገጃጅቼ እንቢ አትለኝማ አለችኝ። እሺ ብዬ ተነስቼ ሻወር ለመውሰድ ገባሁ ሰው እንዴት ያንን ሁሉ ጭቃ በሰውነቱ ተሸክሞ ይሄዳል የሆነ ሰአት እራሴን ታዘብኩት ስታጠብ ቅልል አለኝ ጨራረሼ ልብሴን ቀያይሬ ወጣሁ።
እእእ እንዴት ነው ቀለል አላለህም ባንዴኮ ፊትህ ሁላ ወዝ በወዝ ሆነ አለችኝ።አንቺ የከተማው አፈር እኔ ላይ ነበር እንዴ ሚከማቸው ምንድነው ይሄ ሁሉ ጭቃ ለካ መንገድ ላይ ስሄድ ቀስ እያልኩ ምራመደው ጭቃው ከብዶኝ ወደኋላ እየጎተትኝ ነው አልኳት ከት ብላ ሳቀች መሳቅ ቢሉ መሳቅ እንዳይመስላችሁ ጉንጮቿ ከግራ ከቀኝ ጎድጉደው 32 ጥርሷ እየታየ ካይኖቿ እንባ ጠብ ጠብ እስኪል ሳቀች እግሯን ሁላ እያነሳች ስትስቅ ሳያት በሷ አሳሳቅ እኔም ሳኩኝ ደነገጠች ወይኔ ጉዴ ሳቅህኮ ከምርህ ነው አዬቼሀለሁ አደል ስቀሀል ማርያምን ስቀሀል አለችኝ።
ሳቄን ዋጥ አድርጌ ዝም ብዬ ቁጭ አልኩ ምግብ ሰራች በላን እኔ ሶፋ ላይ ቁጭ እንዳልኩ እንቅልፍ ወሰደኝ ሌሊት 10 ሰአት አካባቢ መልሼ ተነሳሁ ልእልትም በተቀመጠችበት ሶፋ ላይ እንቅልፍ ወስዷታል አይቻት አስተካክዬ እንኳን ሳላስተኛት ቤት ውስጥ መንጎራደድ ጀመርኩ ።
እዛም ግብት ውጥት እዛም ግብት ውጥት ዝም ብሎ ሲያቅበዘብዘኝ ወደውጭ ወጣሁና ሲጋራ ለኮስኩ አጨስኩ ግቢ ውስጥ እጄን ወደኋላ አድርጌ በር እየደረስኩ መመላለስ ጀመርኩ ሁኔታዬ ለራሴም አስፈራኝ የማብድ የማብድ ሁላ መሰለኝ በተለይ ማታ ከልእልትጋ አብሬ ስቄ እንደነበር ትዝ ሲለኝ እናቴ ሞታ ተቀብራ እኔ መሳቄ በራሱ ክህደት መሰለኝ ዝም ብዬ በሩን ከፍቼ ከግቢው ወጣሁ፡፡ወደነ እዮብጋ ሄድኩ እንዴት እንደደረስኩ አላቅም ብቻ ደረስኩ ስገባ እዮብም ሁሉም ተደራርበው ተኝተዋል።እዮብን ሳየው ከልእልትጋ ድራማ እንደሰሩብኝ ገባኝ ቢሆንም ዝም አልኩኝና ከጎኑ ሄጄ ተኛሁ.....
ይቀጥላል...
🔻ክፍል3️⃣0️⃣ከ 1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔