🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ፀሀፊ ✍️ ማኔ
ክፍል 3️⃣3️⃣
እዛ ቦታ ላይ ማታ ብቻዋን ስትደፈር የስምንት ጎረምሳ ወንዶች ስሜት ማብረጃ ስትሆን ያ ሁላ ወጠጤ እጁን ሲያሳርፍባት ሁሉም የሞቀ ቤቱ ውስጥ ተኝቶ ነበር፡፡ ልክ እሷ ደክማ ለሞት ስትዳረግ ግን ሁሉም ሰው ከንፈሩን እየመጠጠ ተሰብስቦ እሷን ለማየት ይጋፋል።
ህይወት በራሷ ምንም የማትጨበጥ ናት፡፡
ሁሉም ሰው ከቤት ወጣ እዮብም ቢሆን አብሮኝ አልነበረም ያንን አጋጣሚ ተጠቅሜ ከቤት ወጣሁ በድጋሜ ወደ እዮብጋ ላለመመለስ ለራሴ ቃል እየገባሁ ነበር ከዛ ሰፈር የወጣሁት ድጋሜ ላላገኘው ላላየው አጠገቡ ላልደርስ የሰው ነፍስ ሲጠፋ ቆም የሚመለከት ጨካኝ ሰው አድርጌ ነበር የቆጠርኩት።
መሄጃ ባይኖረኝም መሄዱን ስለፈለኩት ዝም ብዬ መጓዝ ጀመርኩ።
መጀመሪያ እናቴ ሄድኩና የተፈጠረውን እንዳለ ነገርኳት እንባዬ መቆም አልቻለም ነበር።
መቃብር ቦታው ላይ ትንሽ ከቆየሁ ቡሀላ ተመልሼ ወደሌላ ቦታ መጓዝ ጀመርኩ ኪሴ ውስጥ አምስት ብር ነው ያለው፡፡
እዮብ ተደጋጋሚ ጊዜ ሲደውልልኝ ሲሙን አውጥቼ ወርውሬ ስልኩን ብቻ ያዝኩት።
ሰአቱ ስምንት ሰአት አካባቢ ሲሆን በጣም እራበኝ እኔ ደሞ ተመላሽ እንኳን እንዴት እንደሚጠየቅ አላውቅም፡፡
ጨጓራዬ ሆዴ ውስጥ ያሉ ሁሉንሜ አካሎቼን ሳይበላቸው በፊት እኔ ምግብ መብላት እንዳለብኝ ሲገባኝ ስልኬን አውጥቼ ለመሸጥ ወደስልክ ቤት ይዣት ሄድኩ።
150 ብር ልግዛህ አለኝ። እሺ አልኩት ብሬን ተቀብዬ ሄድኩና በላሁ።
የቀረችውን ብሬን ኪሴ ከትቼ ስንከራተት ቀኑ መሸ ዝም ብዬ የሆኑ ጎዳና ተዳዳሪዎችን ሳይ ተጠግቼ ካጠገባቸው ቁጭ አልኩ።
ቼክ አላረጉኝም ሁሉም የየራሱን በላ እንቅልፍ እስኪወስዳቸው ዘፈናቸውን ዘፋፈኑና ተደራርበው ለማለት በሚያስችል ሁኔታ ውስጥ ተኙ። እኔ ጥጌን ይዤ ግድግዳውን ተደግፌ ቁጭ አልኩ፡፡
ዝም ብዬ አስፋልቱ ላይ አይኔን ተክዬ እየተመለከትኩ እማ ሳመሽ እንደዛ ምትጨነቀው ግን ምን እንዳልሆን ነበር ዛሬስ እንደዚህ ሌትና ቀኑ እንደተምታታብኝ ብታይ ምን ትል ይሆን እያልኩ እንደለመድኩት ማልቀስ ጀመርኩ ሳለቅስ ቶሎ ይደክመኛል መሰለኝ እዛው በተደገፍኩበት እንቅልፍ ወሰደኝ።
ሌሊት ላይ ብንን ስል ዝም ብዬ መራመድ ጀመርኩ ሰፈሩን ባላቀውም እግሬ ወደመራኝ ስጓዝ አንድ ሰፈር ደረስኩ ሰፈሩ ቀውጢ ነው በዛን ሰአት ተቃቅፎ ወክ ሚያደርግ አለ።
ዘፈኑ ለጉድ ነው በየክለቡ በር ላይ የተቀቀለ እንቁላልና ችብስ የሚሸጡ ብዙ ሰዎች አሉ ግማሹ እራቃኑን ሚያስንቅ አለባበስ ለብሶ ግማሹ ደሞ ገና በለጋ እድሜው ሲጋራ ለኩሶ እያንቦገቦገ ተመለከትኩ ዞር ስል እድሜዋ ከአስራዎቹ የማይዘል ልጅ ቦርጩ ብቻ 9ዐኪሎ ከሚመዝን ሰውዬ መኪና ውስጥ ቁጭ ብላ ጭኗን ሲደባብስ አየሁ።
ቁጭ ብሎ እንቁላል እየሸጠ ወደነበረው ሰውዬ ጠጋ አልኩና ስንት ሰአት ነው ብዬ ጠየኩት 9:3ዐ አለኝ፡ የቀኑ ይሁን የሌሊቱ እንጃ ብቻ ግር ግሩ የሌለ ነው ከዛ እዚህ ከዚህ እዛ ሚራወጡ ሴቶች ብዛታቸውን ሳይ ገረመኝና አይ ፈጣሪ እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥም ቀንና ሌሊቱ ይለያያል ማለት ነው ብኔ ጥጌን ይዤ ዝም ብዬ ሁሉንም መመልከት ጀመርኩ ።
አላስተዋልኩትም እኔ ትልቁ ችግሬ ለካ ብቻዬን መሆን አለመቻሌ ነው ትንሽ ደቂቃ ብቻዬን ስሆን እያበድኩም እየሞትኩም ይመስለኛል።
እንደዚህ ቁጭ ብዬ ደሞ የሰዎችን ግርግር ስመለከት ትንሽ ጭንቅላቴ አረፍ ይላል።
የማይነጋ የለም ነጋ ልክ ቀኑ ወገግ እያለ ሲሄድ ሰፈሩም ጭር እያለ ሄደ እንቅስቃሴ ቆመ ዘፈኖቹ ፀጥ እረጭ አሉ።
ይቀጥላል...
🔻ክፍል3️⃣4️⃣ከ 1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔