🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ጥቁር ልብ❤️
ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ 💟
ክፍል 2️⃣0️⃣
አይኔን በጨው አጥቤ እንደባል አደረገኝ።
አባቴጋ ደርሼ ከተመለስኩ ቡሀላ ልጆቼን ትኩር ብዬ ማስተዋል ጀመርኩ።
ለካ አድገዋል ለካ ወንዱ ልጄ በእግሩ መሄድ ጀምሯል ለካ ሴቷም ለናቷ እቃ ማቀበል ጀምራለች ለካ ትናት አራስ የነበረችው ልጅ ዛሬ ዳዴ እያለች የኔስ ቤተሰቦች አንዴ ወልደው ጥለውኛል እኔ አለሁ አደል ለልጆቼ ወይ አለሁ አላልኳቸው ወይ ከነጭራሹ ከህይወታቸው አልወጣሁ ።
የሆነ ቦታ ደርሼ ስመለስ እንደ አባት እሮጠው ጓጉተው መጥተው አያቅፉኝም ከቤት ለመውጣት ሳስብ ማናቸውም ለምን ይወጣል አብረን ካልሄድን ብለው አያልቅሱም የጎረቤት ልጆች አባታቸው ከቤት ሲወጣ አብረን ካልወጣን ለምን አባታችን ከጎናችን ይለያል ብለው እሪሪ ሱሉ ሳይ አቤት ታድለው የኔስ ልጆች ምን አድርጊያቸው ነው እንደነሱ ማይሆኑልኝ ብዬ እራሴን ጠይቃለሁ
ብቻ ከአዲስ አበባ ከተመለስኩ ቡሀላ ወደ ማህበሬም ወደ እቁቤም ተመለስኩ የሀገሬው ሰው በነገር ነካ ያደርገኛል ቤተሰብ አለኝ ብሎ ሄዶ አባረሩት መሰለኝ እያሉ ያፌዙብኝ ጀመር እኔ ጆሮ ዳባ ብዬ ዝም አልኩ ።
የህይወት ዘመን ጥያቄዬ አባቴ ነበር እሱም ተመለሰልኝ በቃ ከዚህ ቡሀላ ምን ቀረኝ አርፌ እርሻዬን እያረስኩ ልጆቼን ላሳድግ የሰው ጥግ አልደርስም ድጋሜ እናትም አባትም አለኝ ብዬ ፊቴን አላዞርም ብዬ ለራሴ ቃል ገባሁ ድጋሜ ባለቤቴንና ልጆቼን ትቼ የትም ላለመሄድ ወሰንኩ ልጆቼን ወደኔ ለመሳብ የእውነት አባት ልሆንላቸው አቀጄ ህይወቴን ሀ ብዬ በገጠር መምራት ጀመርኩ።
በቃ አንዴ እድሌ ተሰብሮ የለ ተረጋግቼ ትንሽ እንኳን ሳልቀመጥ ከስንት አመት በፊት ጓደኛዬ ማገጠሽብኝ ብሎ የገደላት ልጅ ቤተሰቦች(እኔን በመጥረቢያ የመታኝ) እኔ ላይ ተነሱብኝ ለልጃችን መገደል ምክንያት አንተ ነህ አሉኝ ከስንት አመት በፊት ለተፈጠረ ጥፋት እንደ አዲስ ወቀሱኝ እኔ ነገሩን አብርጄ ለማሳለፍ ሞከርኩ ለካ ዝምታዬ ለነሱ ልብ እየሰጣቸው ነበር።
አንዴ ህይወትህን እየተቅበዘበዝክ ኑሮ ተብዬ የተረገምኩ ይመስል ።
በየመጠጥ ቤቱ አልያም በሄድኩበት በየትኛውም ቦታ ገዳዩን ትተው እኔ ላይ ይዝቱብኝ ጀመር።
አንድ ቀን አባትዬውን ጠጋ አልኩና ቆይ የልጃችሁ ስጋ እራሱ እስካሁን በስብሶ ይጠፋልኮ ስንት አመት ሙሉ ዝም ብላችሁ አሁን ምን ተገኝ እንደዚህ ምትደነፉት አልኩት።
ጉዳችንን መች አወቅን አሁን እንዲገላት ምክንያት እንደሆንክ ያወቅነው የልጃችን ገዳይ ሁሉንም በሰው ልኮብናል ሰመተነዋል ታሪኩን አሉኝ።
ቁጭ ብዬ ነገሩን ለማሰብ ሞከርኩ እንዴትም ሊሆን አይችልም ስንት አመት ሙሉ ጫካ ዝም ብሎ ተቀምጦ አሁን ምን ተገኝቶ ነው እኔን ሚያጠማምደኝ ወይ ሲያልፍልኝ አላየ ቆይ መኑ ተነክቶ ነው ብዬ ከራሴጋ አወራሁ።
ወይስ እኔ በሰላም ምኖር ከሆነ ሚከፋው ሴጣን አለ አረ ተይ ቅድስት አርሴማ ገላግይኝ ከዚህ ጉድ ብዬ ደጋግም ፀለይኩ።
ለካ የኔ ፀሎትም ፍሬ የለውም ኖሯል እርሻ ሲጀመር የኔንም ያጎቴንም እርሻ እያረስኩ በሰላም ለመኖር እየተደላደልኩ ባለሁበት ሰአት
እቁብ ነበረኝና ለመሄድ ስወጣ ባለቤቴ ዛሬ ጥሩ ህልም አላየሁም አቃዥቶኛል አደራ በጊዜ ተመለስ ብላ ለመነችኝ ::
ጭራሽ እስከ እቁብ ቤቱ ድረስ ትንሿን ልጅ አዝላ ሸኘችኝና አደረ በጊዜ ተመለስ እቁብህን ክፈልና ብላኝ ወደቤቷ ተመለሰች ።
እንግዲህ በገጠር እቁብ ለመከፈል እቁብ የሚደርሰው ሰውዬ ቆሎና ጠላ አዘጋጅቶ ደግሶ እቁብተኛው ሰፊ ጊዜ ወስዶ ተጨዋውቶ የወጣውን እቁብ ለደረሰው ሰው አስረክቦ ነው ሚሄደው።
እኔ ጠላ እየጠጣሁ ጨዋታ ይዤ የባለቤቴን ቃል ዘንግቼው እዛው አመሸሁ።
አምሽቼ ስመለስ የሟች አባት እና ወንድም ቅንጭብ የሚባል ተክል አለ እሱ ስር ተደብቀው ጠበቁኝ እኔ ሞቅታውም እንዳለ ሆኖ በደመነፍስ እየተራመድኩ ከኋላዬ መጥቶ ጅንፎ በሚባል ዱላ ሲመታኝ መቆም አቅቶኝ ለመውደቅ ስንገዳገድ ከፊት ልጅየው ደገመኝ የዛኔ አቅሜን ስቼ ወደኩኝ በተኛሁበት ደጋግመው አሳረፉብኝ ከምቶቹ ሁሉ ግን ጭንቅላቴ ላይ ያሳረፉት ዱላ በጣም ጎድቶኝ ነበር የሚደርስልኝ ሰው እንደሌለ ስረዳ ህመሜን ዋጥ አድርጌ እንደሞተ ሰው ሆንኩባቸው የሞትኩ ሲመስላቸው ወደቅንጭቡ ውስጥ አስገቡኝና ጥለውኝ ሄዱ።
እራቅ ማለታቸውን ሳረጋግጥ ተነስቼ በለበስኩት ፎጣ አናቴን ጠቅልዬ ደሜ እየተንጠባጠበ እየተጎተትኩ እንደምንም በድግድግ ጨለማ ቤቴ ገባሁ።
ባለቤቴ በር ላይ ጭብጥ ብላ እየጠበቀችኝ ነበር ስታይኝ ወይኔ ጉዴ የፈራሁት ደረሰ ብላ ጮኸች ጎረቤት ተሰበሰበ ደሜ ተጠራረገ ጭንቅላቴ ተፈንክቶ ስለነበር በማሰሻ ጨርቅ እሳት እያስነካች ቁስሌን ተኮሰችልኝ ።
ሌሊቱን እንደምንም አደርኩና በነጋታው ያጎቴ ሚስትና ልጆች እንዲሁም የተወሰነ ጎረቤቶች ሆነን ወደ ሀኪም ቤት ሄድን ሀኪም ቤቱ እሩቅ ስለነበር በመከራ ነው የደረስነው ።
ስንደርስ የታሰረው ቁስሌ ተፈቶ ተሰፋልኝ ሰውነቴ ላይ ያሉት ቁስሎችንም አዩልኝ።
ለተወሰነ ቀን ሀኪም ቤት መተኛት እንዳለብኝ ተነገረኝ ።
ባለቤቴ ከጎኔ ሳትለይ ለአምስት ቀን አስታመመችኝና ማንም ሰው ሳያውቅ ሳያየኝ ወደቤቴ ተመለስኩ።
ባለቤቴ አንዱን በሬ ሸጠችና ፍየል ገዝታ አረደችልኝ ከስጋውም ከትኩሱም አድርጋ ከተንከባከበችኝ ቡሀላ አንዱ የጎረቤት ልጅ ወደ አዲስ አበባ እንደነገ ሊሄድ ነበርና የበሬውን ግማሹን ብር አሲያዘችኝና አብረህ ወደ አዲስ አበባ ሂድ እዚህ ካገኙህ ይገሉሀል ብላ ሸኘችኝ።
ከአባቴና ከእህቶቼጋ ባልጣላ ኖሮ ቢያንስ ማርፍበት ይኖረኝ ነበር እያልኩ ባደረኩት ድርጊት ስበሳጭ ነበር ።
ብቻ ከልጁጋ ወደ አዲስ አበባ መጣን ጓደኛው ቀድሞ መጥቶ ቤት ተከራይቶ ነበር የሚኖረው እንጦጦ ማርያም የዛኔ ቤቶቹ ሰፋፊና እርካሽ ነበሩ ።
እኛም እሱጋ አረፍን ልጁ እንደመጣ ከመጥፎ ልጆችጋ ስለገጠመ አጫሽና ቃሚ ሆኗል መኪና ላይ እረዳት ሆኖ ነው ሚሰራው
እኔ ከህመሜ እስካገግምና የያዝኩት ብር እስኪያልቅ ቤት ተኝቼ መዋል ጀመርኩ አብረን የመጣነው የጎረቤቴ ልጅ ግን ከመጣ ቡሀላ እንዳሰበው ሳይሆንለት ቀረና ተመልሶ ወደገጠር ሄደ ።
ይቀጥላል .....
🔻ክፍል2️⃣1️⃣ ከ 1️⃣0️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀