YeneTube


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


በትግራይ “ከመንግስት እውቅና ውጪ” የሚደረግ የሰራዊት እንቅስቃሴ “በአስቸኳይ” እንዲቆም አቶ ጌታቸው ረዳ አሳሰቡ!

በትግራይ ክልል “ከመንግስት እውቅና ውጪ” የሚደረግ የሰራዊት እንቅስቃሴ “በአስቸኳይ እንዲቆም” የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ትዕዛዝ ሰጡ። ይህን ትዕዛዝ ቸል በሚሉ አካላት ላይ “አስቸኳይ” “የእርምት እርምጃ” እንዲወሰድም አሳስበዋል።

አቶ ጌታቸው ይህን ማሳሰቢያ የሰጡት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት እና የሰላም እና ጸጥታ ካቤኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ ለሆኑት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ በጻፉት ደብዳቤ ነው።

ከሁለት ቀናት በፊት የተጻፈው ይህ ደብዳቤ፤ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ስር በሚተዳደረው “ድምጺ ወያነ” ቴሌቪዥን ጣቢያ በኩል ይፋ የተደረገው በዛሬው ዕለት ነው።

“ህገወጥ እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ ስለማሳሰብ” በሚል ርዕስ ስር የተጻፈው ይህ ደብዳቤ፤ “ህገ ወጥ ጉባኤ ያደረገው” በሚል የሚጠራውን ቡድን “ስልጣን ለማግኘት እንቅስቃሴ” እያደረገ እንደሆነ ይወነጅላል።

አቶ ጌታቸው የቡድኑን ማንነት በደብዳቤያቸው በግልጽ ባያስቀምጡም፤ ከዚህ ቀደም ባወጧቸው መግለጫዎች በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራ ስብስብ የህወሓትን “ህገ ወጥ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጓል” በማለት ሲተቹ ቆይተዋል።

ይህ ቡድን “የሰራዊት አመራሮች ውሳኔ” በሚል ጀምሮታል ያሉትን “ህገ ወጥ እንቅስቃሴ እንዲያቆም” የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መወሰኑን አቶ ጌታቸው በደብዳቤያቸው አስታውሰዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa


ጄነራሉ ተገደሉ

ደቡብ ሱዳን ውስጥ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሄሊኮፕተር ላይ በተፈጸመ ጥቃት የሱዳን ጦር ጄኔራልን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ድርጅቱ አስታወቀ።

ሄሊኮፕተሯ በቅርቡ ግጭት በተፋፈመበት የላይኛው ናይል ተፋሰስ ግዛት የአገሪቱን ጦር አባላት ልታስወጣ በምትሞክርበት ወቅት እንደተኮሰባት ተገልጿል።

በጥቃቱም አንድ የሄሊኮፕተሯ ሠራተኛ፣ ቆስለው የነበሩ ጄኔራል እና በርካታ የደቡብ ሱዳን ወታደሮች መገደላቸውን በደቡብ ሱዳን የመንግሥታቱ ድርጅት ተልዕኮ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ወታደሮቹን ውጊያ ከተፋፋመበት የላይኛው ናይል ተፋሰስ ግዛት ለማስወጣት በሚሞከርበት ወቅት የተፈጸመው ጥቃት በጦር ወንጀልነት ሊፈረጅ እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ገልጿል።

@Yenetube @Fikerassefa


🎺🎺🎺 ቅናሻችን አምልጧችሁ የነበረ  ደንበኞቻችን በዲያስፖራ ቁጥር 2 ሳይታችን ልንክሳችሁ መጥተናል


65,000 ካሬ ላይ ያረፈ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር

📣60% የባንክ ብድር የተመቻቸለት

⚡️Aluminium form work Technology 24 ሰዓት እየተሰራ ያለ

👉ቅድመ ክፍያ ከ 8% ጀምሮ

💥2 ከርሰ ምድር ውሀ
💥standby generator
💥ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረግያ
💥4 የ ሰው ሊፍት እና 1 የ እቃ መጓጓዣ
💥በቂ የመኪና ማቆሚያ ከ 3 እስከ 6 ቤዝመንት
💥5 መዋኛ ገንዳ የ ልጆች እና የ አዋቂ
💥የባስኬትቦል መጫወቻ
💥ቤተ መፃህፍት (library)
💥ጂም እና ስፓ
💥የልጆች መጫወቻ ስፍራ
💥አረንጓዴ ስፍራ
💥ለ ማህበራዊ ጉዳይ የሚውል ሰፊ አዳራሽ
💥ዘመናዊ ለ እርድ የሚሆን ቦታ

ከ ስቱዲዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉   ከተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል ከነ መታጠቢያው ,ላውንደሪና  ስቶር ጋር

የተለያየ የካሬ አማራጭ:-

📌 ስቱዲዮ(studio)
        56.60 ካሬ
📌 ባለ አንድ መኝታ
         77.70ካሬ , 69 ካሬ ,85ካሬ, 98ካሬ
📌  ባለ ሁለት መኝታ
        99ካሬ,123ካሬ,128ካሬ እና 148.20 ካሬ
📌 ባለ ሶስት መኝታ
      118ካሬ,104ካሬ,123ካሬ, 139ካሬ, 146ካሬ,151ካሬ, 157ካሬ
📌 ባለ አራት መኝታ
       170ካሬ እና 186ካሬ



👉 እንዲሁም የንግድ ሱቆች 

✉️ ከኢትዮጵያ ውጪ ለምትኖሩ ደንበኞቻችን በDHL የቤት ባለቤት መሆን ትችላላችሁ

ለበለጠ መረጃ እንዲሁም ለሳይት ጉብኝት በ ☎️ +251929928392 ይደውሉልን
Telegram  @BetelZewelde


ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዩናይትድ ስቴትስ ለደቡብ አፍሪካ የምታደርገውን የገንዘብ ድጋፍ አስቆሙ

ደቡብ አፍሪካ በነጭ ገበሬዎች ላይ በደል ታደርሳለች እንዲሁም መሬታቸውን እየነጠቀች ነው ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ወንጅለዋል። ትራምፕ የደቡብ አፍሪካ ነጭ ገበሬዎች የአሜሪካ ዜግነት እንዲያገኙ የሚያስችል ፕሮግራም እንደሚጀምሩም ተናግረዋል።

የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ትራምፕ በአፍሪካዊቷ ሀገር ዙርያ ያላቸው አመለካከት "በተሳሳተ መረጃ" ላይ የተመሠረተ ነው ሲል ከዚህ በፊት ምላሽ መስጠቱ ይታወሳል።

@Yenetube @Fikerassefa


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🏢ሂል ቦተም / HILL BOTTOM PROPERTY

👉 የባለፀጎች መኖሪያ በሆነችው አያት ላይ
ልምድ በአላቸው አርክቴክቶች በጥንቃቄ ዲዛይን ተደርጎ ከነሙሉ ዘመናዊ ፊኒሺንግ የሚገነቡ ቅንጡ አፓርትመንቶች!

      ለአዋቂም ሆነ ለልጆች የሚሆን በጥራት የተመስከረለት በአገልግሎት ላይ ያለ የተሟላ የመዝናኛ ማዕከል በቅጥር ግቢው ውስጥ መኖሩ ልዩ ያደርገናል!

   አገልግሎቶች...
👉ጂም
👉ስፓ                               
👉ሬስቶራንት እና ኮፊ ሐውስ
👉የሜዳ ቴኒስ
👉የመዋኛ ገንዳ
👉የልጆች መጫወቻን በቅጥር ግቢ ውስጥ ያገኛሉ።

👉 BLOCK A ላይ ግንባታቸው 100% ተጠናቀዉ   ለደንበኞች ካስረክብናቸው ውስጥ ውስን ቤቶች እርስዎን ይጠብቃሉ!
  
ከፈልጉ በ50%  ክፍለው ቀሪውን በባንክ 50/50 መክፈል ይቻላል!

በተጨማሪም...
     Block B ላይ
👉በ16  ወር ውስጥ የምናስረክባቸው
80% የግንባታ ደረጃ  ላይ የደረሱ ቤቶች እየሽጥን ነው::

     ባለ 2 መኝታ ቤቶች ከ 120-167 ካሬ
     ባለ 3 መኝታ 167 -227 ካሬ
      ዱፕሌክስ አፓርትመንት

      ከ15% ቅድመ ክፍያ

      ☎️+251937671561


አብዘሃኛዎቹ ተሳፋሪዎች ኢትዮጵያውያን መሆናቸው የተገለጸ አራት ጀልባዎች ተገልብጠው 186ቱ የገቡበት አለመታወቁ ተገለጸ!

በየመን እና ጅቡቱ የባህር ክልል ላይ አራት ጀልባዎች ተገልብጠው 186 ሰዎች የገበቡበት አለመታወቁን አለም አቀፉ የፍለሰተኞች ድርጅት (አይኦኤም) አስታወቀ፤ አብዘሃኛዎቹ ተሳፋሪዎች ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ገልጿል።

የሁለት ተሳፋሪዎች አስከሬን መገኘቱን የጠቆመው አይኦኤም ሁለት የጀልባዎቹ ሰራተኞችን ማትረፍ መቻሉን አስታውቋል፤ 181 ተሳፋሪዎች እና 5 የመናውያን የጀልባዎቺ ሰራተኞች የገቡበት አለመታወቁን ጠቁሟል።

የገበቡበተ አልታወቀም ከተባሉት 181 የጀልባዎቹ ተሳፋሪዎች መካከል አብዘሃኛዎቹ ኢትዮጰያውያነ ናቸው ሲሉ የአይኦኤም የየመን ተልእኮ ዋና ሃላፊ አብዱሳቶር ኢሶኤቭ መናገራቸውን አሶሼትድ ፕሬስ በዘገባው አስታውቋል።

“በሂዎት የተረፉ ካሉ በሚል የነፍስ ማዳን ስራዎች ከአከባቢው ባለስልጣናት ጋር እየሰራን ነው፣ የሚያሳዝነው ነገር በህይዎት የተረፈ ላናገኝ እንችላለን” ማለታቸውን ዘገባው አካቷል።

አደጋው የደረሰው ሀሙስ የካቲት 27 ቀነ 2017 ዓ.ም መሆኑን አመላክቷል፤ በእርስ በርስ ግጭት እየታመሰች በምትገኘው የመን በኩል አድርገው ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚደረገው ህገወጥ የሰወች ዝውውር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል ሲል አይኦኤም መግለጹን ዘገባው አስታውቋል።

በ2023 ብቻ ከ97 ሺ በላይ ሰዎች በህገወጥ መንገድ የመን መግባታቸውን በአብነት አስቀምጧል፤ አምና በ2024 ወደ የመን በህገወጥ መንገድ የገቡ ስደተኞች ቁጥር ቀንሶ እንደነበር የጠቆመው አይኦኤም 61 ሺ ሰዎች ብቻ የመን መድረሳቸውን አመላክቷል።በ2024 ብቻ 558 ሰዎች በጉዞ ላይ እያሉ ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa


ጀርመንኛ ቋንቋ ስልጠና በመራህያን

A1, A2, B1 and B2 and C1 Level

•አዲስ ቋንቋ መማር ለምትፈልጉ
•የጋብቻ ፕሮስስ ጀርመን ኤምባሲ መጀመር ላሰባችሁ
•የስራ ፕሮስስ ለመጀመር ያሰባችሁ

    •Online or Inperson

To register:
       ☎️
0989747878
0799331774

አድራሻ፦ 22 ከ ጎላጉል አጠገብ

ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ : @merahyan


#የሚዘጉ መንገዶች ስለማሳወቅ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከቢሊግርሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ጋር በመተባበር የካቲት 29 እና 30 ቀን 2017 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ የሚያደረገው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መርሀ ግብር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

በዚህም መሠረት በሁለቱም ቀናት ከቀኑ 5:00 ሠዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስኪጠናቀቅ ድረስ፦

. ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)

. ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ ላይ)

. ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ (ለገሃር መብራት)

. ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድየም (ቴሌ ማቋረጫ ላይ)

. ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ (ሀራምቤ መብራት ላይ )

. ከብሔራዊ ቤተ መንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ (ብሔራዊ ቤተመንግሥት ላይ)

. ከቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ወደ መስቀል (ባምቢስ መቅረዝ ሆስፒታል መታጠፊያ) ላይ የሚዘጋ ሲሆን አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።

@Yenetube @Fikerassefa

10.4k 0 31 13 159

'GTNA' ለሚድያ መገንቢያ የተሰጠውን 5 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ በ1 ቢልዮን ብር ሊሸጥ እያስማማ መሆኑ ታወቀ

- ቦታው ለጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ማስፋፊያ ተብሎ የተያዘ ነበር

ግሎባል ቴሌቭዥን ኔትዎርክ ኦፍ አፍሪካ (GTNA) በሚል ስያሜ የተቋቋመው እና በአፍሪካ ግዙፉ የሚድያ ተቋም ይሆናል የተባለለት ድርጅት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሊዝ የተረከበውን 5ሺ ካሬ ሜትር ቦታ በደላሎች አማካኝነት ሊሸጥ መሆኑ ታውቋል።

GTNA መሬቱን ከተረከበ ሶስት አመት እንዳለፈው የጠቆሙት ምንጮቻችን አሁን ላይ ጋንዲ ሆስፒታል አካባቢ የሚገኘው ቦታው ታጥሮ ለመኪና ፓርኪንግ አገልግሎት ብቻ እየዋለ መሆኑን ከምስሎች እና ቪድዮዎች ጋር አያይዘው ለመሠረት ሚድያ ልከዋል።

"በመጀመርያ በደላሎች አማካኝነት ለሽያጭ የቀረበው በ1.4 ቢልዮን ብር ነበር፣ ገዢ ስላልተገኘ አሁን ላይ እስከ 1 ቢልዮን ብር እየተጠራበት ነው" የሚሉት ምንጮች አፍሪካን ማዕከል አድርጎ የአፍሪካን እውነት ለአለም ያሳውቃል የተባለለት ተቋም መሬቱን ለምን እንደሚሸጥ እንደማያውቁ ተናግረዋል።

አንድ የከተማ አስተዳደሩ ባልደረባ ግን መሬቱ ለሽያጭ መቅረቡን እንደሚያውቁ ለሚድያችን ገልፀው "በዲዛይኑ ላይ የተቀመጠውን ግዙፍ መንትያ ህንፃዎች ለመገንባት አበዳሪ ባንክ አልተገኘም፣ ምናልባት ሀብት ለማሰባሰብ ይሆናል" ብለዋል።

ግሩም ጫላ በተባለ ግለሰብ አማካኝነት በአፍሪካ ትልቅ ሚዲያ  ሊገነባ እንደሆነ በርካታ ሚድያዎች ከሶስት አመት በፊት መዘገባቸው ይታወሳል። ለሚድያው ዋና መስሪያ ቤት የሚውለው ቁልፍ ቦታ ከጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ይዞታ ጭምር ተወስዶ እንደተሰጠ ምንጮቻችን ጠቁመዋል።

"መንግሥት ለጋንዲ መታሠቢያ ሆስፒታል የማስፋፊያ ህንፃዎች ግንባታ የሚሆን ሰፊ ቦታ አዘጋጅቶ ነበር፣ ይሁንና ከሆስፒታሉ ይዞታ ላይ 5,000 ካሬ ሜትር የሚሆን ቦታ በቂርቆስ ወረዳ 07 የግንባታ ፈቃድ ከሚሰጡ ሰዎች ጋር በተደረገ ውል በሆስፒታሉ ካርታ ላይ ሌላ አዲስ ካርታ ተሰርቷል" የሚሉት እኚህ የከተማ አስተዳደሩ ሰራተኛ በአንድ አጋጣሚ ለምን ብለው በጠየቁ የሆስፒታሉ ሰራተኞች ላይ ማስፈራራት ደርሶባቸው ነበርም ብለዋል።

ከጋንዲ ሆስፒታል ያገኘነው ተጨማሪ መረጃ እንደሚጠቁመው ሆስፒታሉ ለወላድ እናቶች አገልግሎት የሚውል የከርሰ ምድር ውሃ አስቆፍሮ የነበረ ሲሆን እሱም በGTNA ይዞታ ስር ሊሆን ይገባል የሚል አምባጓሮ ተነስቶ በመጨረሻም በ GTNA ይዞታ ስር እንደተጠቃለለ ታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa


ኢትዮ ቴሌኮም የኢንተርኔት አገልግሎት ፍጥነት መቀነስና መቆራረጥ ችግርን ለመፍታት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም ያጋጠመውን የኢንተርኔት አገልግሎት ፍጥነት መቀነስና መቆራረጥ ችግርን ለመፍታት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷በቀይ ባሕር ውስጥ በሚያልፍ ከፍተኛ ባንድዊድዝ ተሸካሚ ዓለም አቀፍ ባህር ጠለቅ የኢንተርኔት መገናኛ መስመር ላይ ባጋጠመ መቋረጥ ምክንያት የኢንተርኔት አገልግሎቱ በሌሎች አማራጭ መስመሮች ብቻ እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎም ሰሞኑን የኢንተርኔት አገልግሎት ፍጥነት መቀነስ እና መቆራረጥ እያጋጠመ እንደሚገኝ ነው ያመላከተው፡፡

አገልግሎቱን በፍጥነት ለማስቀጠል ከአገልግሎት አቅራቢዎቹ ጋር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ የጠየቀው ኢትዮ ቴሌኮም ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa


የኢትዮጵያ አየር ኃይል አልሸባብ ላይ ጥቃት ማድረሱን የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ!

የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሶማሊያ በማዕከላዊ ሸበሌ ክልል በሚንቀሳቀሰው የአልሸባብ ቁልፍ ይዞታዎች ላይ የአየር ጥቃት ማድረሱን የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር አብዱልቃድር ሞሐመድ ኑር አስታውቀዋል፡፡

የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር አብዱልቃዲር መሀመድ ኑር እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ኃይል በአልሸባብ ምሽግ ላይ የሚሳኤል ጥቃት የተፈጸመው ከሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ጋር በመተባበር ነው።"ያለ መንግስት እውቅና በሶማሊያ ምንም አይነት የአየር ጥቃት ሊፈፀም አይችልም" ብለዋል።

ይሁን እንጂ በኦፕሬሽኑ ስለደረሰው ሞት ወይም ጉዳት ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።ሚኒስትሩ የአንካራው ስምምነት በአል-ሸባብ ላይ ለሚወሰዱ የጋራ ጥረቶች ማዕቀፍ መሆኑን በመጥቀስ የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ የፀጥታ ትብብር እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።የኢትዮጵያ አየር ሃይል ሰሞኑን የአልሸባብ ወታደራዊ ይዞታዎችን መደብደቡን ሶማሊያ ጋሪዳያን መዘገቡ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa


ሙሉ አዞ እስከ 300 ዶላር ድረስ የሚሸጥበት የአዞ ሥጋ ሬስቶራንት በኢትዮጵያ ሊከፈት ነው!

በአርባ ምንጭ ከተማ የአዞ ሥጋ ሬስቶራንት በቀጣይ ዓመት ወደ ሥራ እንደሚገባና በርካታ የውጭ ጎብኚዎችን ወደ ሀገር ውስጥ በመሳብ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እየተሠራ መሆኑን በከተማዋ የሚገኘው የአዞ እርባታ ተቋም ለአሐዱ አስታውቋል።

በ1976 ዓ.ም የተቋቋመው ይህ የአዞ እርባታ ጣቢያ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የማስፋፍያና የማሻሻያ ሥራዎች ተደርገውለት ከ10,000 በላይ አዞዎችን እያሳደገ መሆኑን የገለጹት የአርባ ምንጭ አዞ እርባታ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ዳኜ፤ በውጭ ሀገር ጎብኚዎች ፍላጎት መሠረት ሬስቶራንቱን ለመገንባት መታሰቡን ተናግረዋል።

አክለውም የውጪ ሀገር ቱሪስቶች የአዞ ስጋ ለመመገብ የሚጠይቁ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ ጥናቱ ተጠናቆ በቀጣይ ዓመት ሆቴሉ ወደ ሥራ እንደሚገባም ጠቁመዋል።በጥናቱ መሠረት የአንዱ ሙሉ የአዞ ዋጋ ለውጪ ዜጎች እስከ 300 ዶላር እንዲሁም ለሀገር ውስጥ ተጠቃሚዎች ከ35 ሺሕ ብር ጀምሮ ለእርድ እንደሚቀርብ ነግረውናል።

የጎብኚውን ፍላጎት ለሟሟላት በተቋሙ ከአዞ ውጭ፣ የከርከሮ፣ የአሳማ እርባታን በማስፋፋት ለገበያ እንደሚቀርቡም አክለዋል።

እድሜያቸው ከ3 ዓመት በላይ የሆኑ ለእርድ አዞዎች የሚቀርቡ መሆናቸውንም ሥራ አስኪያጁ ለአሐዱ ተናግረዋል።ሆቴሉም ከአዞ ማራቢያ ራንች ከከተማዋ በ7 ኪ.ሜ ርቀት ከአውሮፕላን ማረፊያው በስተቀኝ በአባያ ሀይቅ ዳርቻ አካባቢ እንደሚገነባም አብራርተዋል።

ሆቴሉ ወደ ሥራ ሲገባ ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳው በተጨማሪ የሥራ ዕድል እንደሚፈጠርም አብራርተዋል።ተቋሙ በጫሞ ሀይቅ ላይ የሚገኘውን ግዙፍ የናይል አዞ በማርባት በአዞ ቆዳ አቅርቦት ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ሥራ አስኪያጁ አያይዘውም፤ ከሆቴሉ ግንባታ በፊት የውጭ ጎብኚዎች በተለይም ላንቲ አሜሪካዊያን፣ ስፔኖች ግዢ በመፈጸም በየግላቸው እርድ እንደሚያካሄዱ አስታውሰዋል። ይህንን የዘፈቀደ እርድ በማስቀረትም ግንባታው መጀመሩን አብራርተዋል።

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa


የረመዳን ፆም የመጀመርያው የጁምዓ ፀሎት ምክንያት በማድረግ በአል-አቅሳ መስጊድ ገደብ ተጣለ

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስተር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ፅህፈት ቤት ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት መንግስታቸው ከዌስት ባንክ ወደ አል-አቅሳ መስጊድ መግባት የሚችሉ አማኞች የቁጥር ገደብ መጣሉን ይፋ አድርጓል።

በአዲሱ ገደብ መሰረትም ከ55 ዓመት በላይ የሆናቸው ወንዶችና ከ50 ዓመት በላይ የሆናቸው ሴቶች እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ብቻ በአል-አቅሳ መስጊድ የሚደረገውን የረመዳን ፆም የመጀመርያው ዓርብ የፀሎት መርሀግብር ላይ ለመሳተፍ ይችላሉ።

እንዲም ሆኖ ግን በአዲሱ መመርያ መሰረት ወደ መስጊዱ እንዲገቡ የተፈቀደላቸው ሰዎች ጥብቅ የሚባሉ የደህንነትና የፍተሻ ስርዓቶችን ማለፍ ግድ እንደሚላቸው ተነግሯል።

ውሳኔው በተከበረው የረመዳን ወር ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያን ሰፋሪዎች ወደ አል-አቅሳ መስጊድ ግቢ ከሚያደርጉት ዕለታዊ ወረራ እና ወደ ዌስት ባንክ በሚጓዙ ፍልስጤማውያን ላይ የሚጣሉ ገደቦችን እየጨመሩ ባሉበት ወቅት የተላለፈ ነው።

የአል-አቅሳ መስጊድ ለእስልምና እምነት ተከታዮች ሶስተኛው ቅዱስ ስፍራ ሲሆን አይሁዶች በበኩላቸው ቴምፕል ማውንት ሲሉ የሚጠሩት የመጀመርያውና ሁለተኛው የአይሁድ ቤተ መቅደሶች የነበሩበት ቦታ ነው ብለው ያምናሉ። መስጊዱ በጥንቷ እየሩሳሌም ከተማ የሚገኝ ሲሆን የዓለም ቅርስ ተብሎም በዩኔስኮ የተመዘገበ ነው።

@Yenetube @Fikerassefa


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🏢ሂል ቦተም / HILL BOTTOM PROPERTY

👉 የባለፀጎች መኖሪያ በሆነችው አያት ላይ
ልምድ በአላቸው አርክቴክቶች በጥንቃቄ ዲዛይን ተደርጎ ከነሙሉ ዘመናዊ ፊኒሺንግ የሚገነቡ ቅንጡ አፓርትመንቶች!

      ለአዋቂም ሆነ ለልጆች የሚሆን በጥራት የተመስከረለት በአገልግሎት ላይ ያለ የተሟላ የመዝናኛ ማዕከል በቅጥር ግቢው ውስጥ መኖሩ ልዩ ያደርገናል!

   አገልግሎቶች...
👉ጂም
👉ስፓ                               
👉ሬስቶራንት እና ኮፊ ሐውስ
👉የሜዳ ቴኒስ
👉የመዋኛ ገንዳ
👉የልጆች መጫወቻን በቅጥር ግቢ ውስጥ ያገኛሉ።

👉 BLOCK A ላይ ግንባታቸው 100% ተጠናቀዉ   ለደንበኞች ካስረክብናቸው ውስጥ ውስን ቤቶች እርስዎን ይጠብቃሉ!
  
ከፈልጉ በ50%  ክፍለው ቀሪውን በባንክ 50/50 መክፈል ይቻላል!

በተጨማሪም...
     Block B ላይ
👉በ16  ወር ውስጥ የምናስረክባቸው
80% የግንባታ ደረጃ  ላይ የደረሱ ቤቶች እየሽጥን ነው::

     ባለ 2 መኝታ ቤቶች ከ 120-167 ካሬ
     ባለ 3 መኝታ 167 -227 ካሬ
      ዱፕሌክስ አፓርትመንት

      ከ15% ቅድመ ክፍያ

      ☎️+251937671561


በሸገር ከተማ አስተዳደር በርካታ መምህራን የሥራ ማቆም አድማ ላይ ናቸው!

በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ በርካታ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን፣ ከትላንት ረቡዕ፣ የካቲት 26 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በሥራ ማቆም አድማ ላይ እንደሚገኙ፣ አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ መምህራንና የተማሪ ወላጆች ተናግረዋል፡፡መምህራኑ፣ ለሥራ ማቆም አድማው መነሻ የኾነው፣ “ጥያቄዎቻችን ምላሽ አለማግኘታቸውና ጥቅማችንን የሚጎዳ አሠራር መጀመሩ ነው፤” ብለዋል፡፡

ለደኅንነታቸው እንደሚሰጉ በመግለጽ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁን አስተያየት ሰጪዎቹ፣ አድማው ከአንደኛ እስከ ኹለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ድረስ ባሉ በርካታ ትምህርት ቤቶች ውስጥ፣ የመማር ማስተማር ሒደቱ እንዲቋረጥና እንዲስተጓጎል ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ከሸገር ከተማ አስተዳደር 12 ክፍላተ ከተማ ውስጥ፦ ኮዬ ፈጬ፣ ገላን፣ ፉሪ፣ ሰበታ እና ለገጣፎ ለገዳዲ በርካታ መምህራን የሥራ ማቆም አድማ ያደረጉባቸው ክፍላተ ከተማ ሲኾኑ፣ አድማው በከፊል የሚካሔድባቸው ክፍላተ ከተማም መኖራቸውን ከተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የሥራ ማቆም አድማው ለሦስት ቀናት እንደሚቆይ የገለጹት አስተያየታቸውን የሰጡን መምህራን፣ በእነዚኽ ቀናት ውስጥ ምላሽ ካላገኙ፣ አቤቱታቸውን በጋራ ለክልሉ ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት ለማቅረብ ወደዚያው እንደሚያመሩ ጠቁመዋል፡፡በሥራ ማቆም አድማው ምክንያት፣ በኦሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ በርካታ ትምህርት ቤቶች፣ ከትላንት ረቡዕ ጀምሮ የመማር ማስተማር ሒደቱ መስተጓጎሉን፣ መምህራንና የተማሪ ወላጆች ተናግረዋል።በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው የከተማ አስተዳደሩ መምህራን ማኅበር ፕሬዝደንት አቶ ግርማ፣ “የሥራ ማቆም አድማ መኖሩን እናውቃለን፤ ነገር ግን ማኅበሩ ተወያይቶ ያሳለፈው ውሳኔ አይደለም፤” ከማለት ያለፈ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልኾኑም።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa


ከ750 በላይ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሠራተኞች በተቋሙ ከስራ 'እንደሚሰናበቱ መገለጹና 5 ሠራተኞች መታሰራቸው' ቅሬታ አስነሳ!

በማህበራት ተደራጅተው ከአስራ አምስት ዓመት በላይ ለሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ያገለገሉ ከ750 በላይ ሠራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ “በመጠየቃቸው ብቻ ዩኒቨርስቲው ከስራ ገበታቸው እንደሚያሰናብታቸው” መግለጹንና ከጥያቄው ጋር ተያይዞ ከ5 በላይ ሠራተኞች መታሰራቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

ለደህንነታቸው በመስጋት ስሜ ባይጠቀስ ያሉ ሠራተኛ፤ "እኔ ጽዳት ነው የምሰራው። 17 ዓመታት አገልግያለሁ።በወር 1100 ብር ነው ሚከፈለኝ።ጭማሪ ስንጠይቅ የምንከፍለው ጭማሪ የለም እናሰናብታቹኋላን አሉን።ከፈለጋችሁ መክሰስ ትችላላችሁ የሚል ምላሽ ተሰጠን" ብለዋል።

ተጨማሪ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=7145

@YeneTube @Fikerassefa


3ተኛ ዙር
የ 5 in 1 Digital Marketing Package ስልጠና

ለ6 ወር የሚቆይ ስልጠና !
-Basic to advanced digital marketing
- Graphic design
-Video editing
-Content Creation
- Wordpress Development

💡ኢንተርናሽናል የኢንተርንሺፕ ፕሮግራም እናመቻቻለን
በምዝገባ ላይ ነን :
☎️
0989747878
0799331774

በመራህያን የወደፊት ብሩህ ተስፋዎን የሚዘሩ ክህሎቶችን ይማሩ !!

አድራሻ፡ ሃያ ሁለት ፣ ከጐላጐል ወደ ቦሌ ሚወስደው 4ተኛ ፎቅ ከ Hanan K Plaza አጠገብ ቢጫ ፎቅ ግራውንድ ፍሎር 10B

ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ : @merahyan


🎺🎺🎺 ቅናሻችን አምልጧችሁ የነበረ  ደንበኞቻችን በዲያስፖራ ቁጥር 2 ሳይታችን ልንክሳችሁ መጥተናል


65,000 ካሬ ላይ ያረፈ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር

📣60% የባንክ ብድር የተመቻቸለት

⚡️Aluminium form work Technology 24 ሰዓት እየተሰራ ያለ

👉ቅድመ ክፍያ ከ 8% ጀምሮ

💥2 ከርሰ ምድር ውሀ
💥standby generator
💥ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረግያ
💥4 የ ሰው ሊፍት እና 1 የ እቃ መጓጓዣ
💥በቂ የመኪና ማቆሚያ ከ 3 እስከ 6 ቤዝመንት
💥5 መዋኛ ገንዳ የ ልጆች እና የ አዋቂ
💥የባስኬትቦል መጫወቻ
💥ቤተ መፃህፍት (library)
💥ጂም እና ስፓ
💥የልጆች መጫወቻ ስፍራ
💥አረንጓዴ ስፍራ
💥ለ ማህበራዊ ጉዳይ የሚውል ሰፊ አዳራሽ
💥ዘመናዊ ለ እርድ የሚሆን ቦታ

ከ ስቱዲዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉   ከተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል ከነ መታጠቢያው ,ላውንደሪና  ስቶር ጋር

የተለያየ የካሬ አማራጭ:-

📌 ስቱዲዮ(studio)
        56.60 ካሬ
📌 ባለ አንድ መኝታ
         77.70ካሬ , 69 ካሬ ,85ካሬ, 98ካሬ
📌  ባለ ሁለት መኝታ
        99ካሬ,123ካሬ,128ካሬ እና 148.20 ካሬ
📌 ባለ ሶስት መኝታ
      118ካሬ,104ካሬ,123ካሬ, 139ካሬ, 146ካሬ,151ካሬ, 157ካሬ
📌 ባለ አራት መኝታ
       170ካሬ እና 186ካሬ



👉 እንዲሁም የንግድ ሱቆች 

ለበለጠ መረጃ እንዲሁም ለሳይት ጉብኝት በ ☎️ +251929928392 ይደውሉልን


በ2018 የትምህርት ዘመን ማንኛውም የአዲስ አበባ ተማሪ የፋይዳ መታወቂያ ከሌለው ምዝግገባ ማድረግ አይችልም ተባለ

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከወሳኝ ኩነት ጋር በመሆን ከ5 አመት በላይ የሆኑ ተማሪዎችን መመዝገብ ተጀምራል።

በአዲስ አበባ ከተማ 1 ነጥብ 1 ሚሊየን የሚሆኑ ተማሪዎች መኖራቸውን ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጸህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ ተማሪዎችን መመዝገብ እንደተጀመረም አስታውቀዋል።

በዚህም በአንድ ወር ውስጥ ከ450ሺ በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል። ይህ የተማሪዎች ምዝገባ በግልም ሆነ በመንግስት እንዲሁም የትኛውም የኮሚኒቲ እና ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች የፋይዳ መታወቂያ መመዝገብ አለባቸው።

የአዲስ አበባ ተማሪዎችን በኢ ስኩል ሲስተም ለመመዝገብ ከአሁን በፊት መጀመሩ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ መግለፁ የሚታወስ ሲሆን ይህንን አሰራር ለማገዝ የፋይዳ መታወቂያ የአንድን ተማሪ ሙሉ መረጃ የሚያሳይ በመሆኑ ቅድሚ ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ኢንጂነር ወንድሙ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል።

አስካሁን ከ5 ሚሊየን በላይ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የፋይዳ መታወቂያ ተጠቃሚ መሆናቸውም ተነግሯል። በቀጣይም ማንኛውም የከተማ አስተዳደር አገልግሎቶች ለማግኘት የፋይዳ መታወቂያ አስገዳጅ ይሆናል።

@Yenetube @Fikerassefa


🇱🇸🇺🇸 ትራምፕ ሌሶቶን "ማንም ሠምቷት የማያውቅ" ሀገር ማለታቸው "አስደንግጦኛል" ሲሉ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ

🗣 "በዓለም ላይ በጣም ታዋቂ እና ልዩ ከሆኑ ሀገሮች አንዷ ሌሶቶ ናት። ፕሬዝዳንቱ እንዲሁም ቀሪው ዓለም ሌሴቶን መጥቶ እንዲጎበኝ በደስታ እጋብዛለሁ" ሲሉ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌጆኔ ምፖትጆአኔ ተናግረዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማክሰኞ ለአሜሪካ ኮንግረስ ባደረጉት ንግግር የውጭ እርዳታ ካቋረጡባቸው ሀገራት ውስጥ "ብዙ ገንዘብ የባከነባት" ያሏትን ሌሶቶ አንስተዋል። እንደ ትራምፕ ገለጻ በሌሶቶ የ LGBTQI+* መብቶችን ለማበረታት 8 ሚሊዮን ዶላር ተመድቦ ነበር።

ድጋፉ በመቋረጡ ምክንያት በተለይም በዩናይትድ ስቴትስ ፈንድ የሚደገፉት የሀገሪቱ የጤና እና ግብርና ዘርፎች ተፅዕኖ እንደደረሳባቸው ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ሀገሪቱ ራሷን በተሻለ መንገድ የምትችልባቸውን መንገዶች እያሳሰች እንደሆነም ነው ሚኒስትሩ ጨምረው የገለፁት።

*የኤልጂቢቲ እንቅስቃሴ ከባሕል ያፈነገጠ ጽንፈኛ ቡድን ተብሎ ሩሲያ ውስጥ ታግዷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦

👉  APK ፋይል ሊንክ 

ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉 @sputnik_ethiopia

Показано 20 последних публикаций.