እንክርዳድ
አባቴማ ድሮ
ስንዴ እያበጠረ
አንዳንዱን እንክርዳድ
ይለቅም ነበረ።
እኔ ግን ዘንድሮ
ግርድ አነፍሳለሁ
ከእንክርዳዱ መሀል
ስንዴ 'ፈልጋለሁ።
(ይስማዕከ ወርቁ)
አባቴማ ድሮ
ስንዴ እያበጠረ
አንዳንዱን እንክርዳድ
ይለቅም ነበረ።
እኔ ግን ዘንድሮ
ግርድ አነፍሳለሁ
ከእንክርዳዱ መሀል
ስንዴ 'ፈልጋለሁ።
(ይስማዕከ ወርቁ)