“ደሞዝ ከጠበቃችሁ ህወይታችሁ አይለወጥም..!” ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ
|ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በአርባ ምንጭ ከተማ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ብዙ ሰው አይረዳም ያሉትን ቁልፍ ጉዳይ በማንሳት ሞግተዋል፡፡ እርሱም መንግስታቸው ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በሕዝቡ ኑሮ ላይ ምን ለወጠ የሚለውን ነው፡፡
እንደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ገለፃ መንግስት ለያንዳንዱ ዜጋ ደሞዝ በመክፈል የዚህችን አገር ችግር አይፈታም፡፡ “በተለያየ ሀገራት መሪዎች በሁለት መልኩ የህዝቡን ኑሮ ለውጠዋል” ሲሉ ያጣቀሱት አብይ “በአንድ በኩል ህዝባቸው ከምቾት ቀጠና እንዲወጣ - ያለበት ህይወት እንዳይመቸው እና ተጨማሪ ስራዎችን አንዲሰራ አቅማቸውን አሟጠው በመጠቀም ተለውጠዋል” ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡
ከዚህ ባለፈ ደግሞ - “ሌሎች ሀገራት መጠነ ሰፊ የተፈጥሮ ሀብት አግኝተው - በነዳጅ እና ሌሎች ማእድናት ሀገር እና ህዝብን ያበለፀጉ አሉ ሲሉ” ጠቅሰዋል፡፡ “እናም ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለቱን መንገዶችን መጠቀም አለብን” ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ - “በአንድ በኩል ከፍተኛ የተፈጥሮ ሀብት አለን እርሱን አውጥተን መጠቀም አለብን - በሌላ በኩል ደግሞ ሰፊ ህዝብ አለን - ብዙ የወጣት ክምችት አለን - ይሄንን ሰው በመነቅነቅ - ከተመቸው ከባቢ አስወጥቶ በማነቃነቅ ሀገር መገንባት አለብን” ሲሉ ተናግረዋል፡፡