በጣም ያማል።በ11 ቀበሌዎች የ770 አርሶ አደሮች ሰብል ወድሟል።
ተጎጅ አርሶ አደሮች
በዋድላ የደረሰው ጉዳት ከጉዳትም በላይ ነው።
በሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ በ11 ቀበሌዎች የሰብል ክምር ላይ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ደርሷል፡፡
በዋድላ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ምክንያቱ ባልታወቀ የእሳት ቃጠሎ የ154 አርሶ አደሮች የሰብል ክምር መቃጠሉ ነው የተገለጸው፡፡
ጥር 1/2017 ዓ.ም በደረሰው ቃጠሎ ጉዳት የደረሰባቸው አርሶ አደር ሲሳይ ፈቃዴ እና ሌሎቹም የቃጠሎው ተጎጅ የኅብረተሰብ ክፍሎች የቃጠሎው መነሻ በውል አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡ ተጎጅዎቹ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አስረድተዋል፡፡
ጉዳት ከደረሰባቸው አርሶ አደሮች መካከል የአንዳንዶቹ ከተቃጠለው ሰብል ውጭ ሌላ ምንም አዝመራ እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡
የዋድላ ወረዳ የአደጋ መከላከል እና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ጽሕፈት ቤት ቡድን መሪ ምትኩ ሞላ በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች የእሳት ቃጠሎ መከሰቱን ገልጸው እስካሁን ባለው መረጃ 770 የሚኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የጉዳቱ ሰለባ መኾናቸውን ተናግረዋል፡፡
የዋድላ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሙሉየ ረታ በወረዳው በ11 ቀበለሌዎች በ152 ክምር ላይ ቃጠሎ እንደደረሰ ነው ያስረዱት፡፡ በቃጠሎው 154 አርሶ አደሮች የጉዳቱ ሰለባ ስለመኾናቸውም ተናግረዋል፡
@zena_ethiopia24