የትግራይ የሠራተኛ ማሕበራትና የክልሉ መንግስት ዉዝግብ
የትግራይ መንግስት ሰራተኞች ማሕበር፣ የትግራይ ዓቃብያነ ሕግ ማሕበር፣ የክልሉ ጤና ባለሙያዎች እና የግል ትምህርት ቤት አስተማሪዎች ማሕበራት እና ሌሎች በጋራ እንዳሉት የተከማቸ የረዥም ወራት ደሞዝ ካለመክፈል በተጨማሪ ከሕግ፣ ከአሰራር እና የቆዩ ስምምነቶች ውጭ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ክልከላዎች አኑሯል ሲሉ ከሰዋል።
በትግራይ ክልል የሚገኙ የሰራተኛ ማሕበራት የሠራተኞች ዉዝፍ ደሞዝ እንዲከፈላቸዉ ለፍርድ ቤት አቤቱታ እንዳያቀርቡ የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር መከልከሉን ተቃወሙ።የትግራይ የመንግስት ሰራተኞች ማሕበርን ጨምሮ አምስት የሲቪክ ተቋማት ትናንት በሰጡት መግለጫ የጊዚያዊ አስተዳደሩን እገዳ፣ ሕገ-መንግስቱን የጣሰ ነዉ ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ ውዝፍ ደሞዛቸው መንግስት እና ቀጣሪ ተቋማት እንዲከፍሏቸው ጠይቀዋል።
ትላንት በጋራ መግለጫ የሰጡት በትግራይ የሚንቀሳቀሱ አምስት የሙያ እና ሌሎች ማሕበራት እንዳሉት በስራቸው ያሉ የመንግስት እና የግል ተቋማት ሰራተኞች የያለፉ ወራት ውዝፍ ደሞዛቸው ተከልክለው አስቸጋሪ ሕይወት እየመሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል። የትግራይ መንግስት ሰራተኞች ማሕበር፣ የትግራይ ዓቃብያነ ሕግ ማሕበር፣ የክልሉ ጤና ባለሙያዎች እና የግል ትምህርት ቤት አስተማሪዎች ማሕበራት እና ሌሎች በጋራ እንዳሉት የተከማቸ የረዥም ወራት ደሞዝ ካለመክፈል በተጨማሪ ከሕግ፣ ከአሰራር እና የቆዩ ስምምነቶች ውጭ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ክልከላዎች አኑሯል ሲሉ ከሰዋል። ሲቪል ተቋማቱ እንዳሉት ተቀጣሪ ሰራተኞች የደሞዝ ጥያቄአቸው ወደ ፍርድቤት ወስደው መብታቸው እንዳያስከብሩ በግዚያዊ አስተዳደሩ ተከልክለዋል።
የትግራይ አቃብያነ ሕግ ማሕበር አስተባባሪ አቶ ሃፍቶም መለስ "ከጥቅምት 2013 እስከ ሕዳር 30 ቀን 2015 ዓመተምህረት ሊከፈል ይገባ የነበረ የመንግስት ሰራተኞች እና የግል ተቋማት ሰራተኞች ውዝፍ ደሞዝ አስመልክቶ ክስ እንዳይቀርብ ለማገድ ያወጣው ድንጋጌ እና ይህ እገዳ ለማራዘም ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓመተምህረት የተፃፈው ደብዳቤ፥ በትግራይ ሕገመንግስት ይሁን በፌደራል ሕገመንግስት አንቀፅ 37 የተደነገገ ፍትህ የማግኘት መብት የሚጥስ ስለሆነ ኢ-ሕገመንግስታዊ ነው። ማህበራችን ይህ ሕገመንግስታዊ ጥሰት አጥብቆ ያወግዛል" ብለዋል።
በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደርፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ተፈርሞ ከዚህ በፊት ለክልሉ ከፍተኛ ፍርድቤት እና ሌሎች መስርያቤቶች የተሰራጨ ደብዳቤ እንደሚያሳየው፥ የመንግስት እና የግል ተቋማት ሰራተኞች ውዝፍ ደሞዝ ጋር በተገናኘ ወደ ፍርድ ቤቶች የሚቀርብ ጥያቄ እና በሂደት ላይ ያለ ጉዳዮች ታግደው እንዲቆዩ መመርያ የሚሰጥ ሲሆን ይህ መምርያ ባለፈው ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓመተምህረት ለተጨማሪ ስድስት ወራት ተራዝሟል።
ይህ ክልከላ ከፍተኛ ገቢ በሚሰበስቡ የግል ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተቀጣሪ አስተማሪዎች ጭምር እየጎዳ መሆኑ የገለፁት የትግራይ የግል ትምህርት ቤት አስተማሪዎች ሕብረት ፀሓፊ መምህር አታኽልቲ ኪዳነ በበኩላቸው በዚህም ምክንያት አስተማሪዎች ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር ተዳርገው ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።
የግል ትምህርት ቤት አስተማሪዎች ሕብረት ፀሓፊ መምህር አታኽልቲ ኪዳነ "አስተማሪዎች በከፋ ቀውስ ውስጥ ነው ያሉት። ሁሉ ሊያውቀው የሚገባ የግል ትምህርት ቤቶች ከማሕበረሰቡ ምን ያክል ገንዘብ እንደሚሰበስቡ የታወቀ ነው። ትምህርት ቤቶቹ ገቢ እየሰበሰቡ እያለ ጭምር ለአስተማሪዎች የማይከፍሉበት ምክንያት ግን ምንድነው ?" ሲሉ ያላቸው ቅሬታ ገልፀዋል።
ለረዥም ግዜ የቆየው እና በትግራይ የሚገኙ የመንግስትና የግል ተቋማት ሰራተኞች የሚያቀርቡት ውዝፍ ያልተከፈላቸው ደሞዝ በአጭር ግዜ ውስጥ መቋጫ እንዲያገኘም የትግራይ የመንግስት ሰራተኞች ማሕበር ጥሪ አቅርቧል። የትግራይ መንግስት ሰራተኞች ማሕበር አስተባባሪ አቶ አብርሃ ኪዱ "ያልተከፈለ ወርሓዊ ደሞዛችን በጥር ወር ውስጥ ሊከፈለን ይገባል። ለዚህም የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር አንዱ ከውስጥ ገቢው፣ ሌላ ከትእምት አልያም ከአበዳሪዎች በመበደር ሊከፍል ይችላል ብለን እናስባለን። ይህ በሲዳማ ተደርጓል፣ በቤንሻንጉል ተደርጓል፣ በጋምቤላ ተደርጓል" ብለዋል።
@zena_ethiopia24