#አላጣም
፡
፡
፡
ኑረት ማለት ምንድነው ትርጉሙ የያዘው ቅኔ
አንቺን ያጣሁኝ ለታ የጠፋኝ አብሮሽ ከጎኔ።
ምንድነው የቃሉ ፍቺ ለምን ነው ታዲያ መኖሬ
ያ ፅኑ ተራራው ልቤ ተዋክቡዋል እንደዚህ ዛሬ።
:
:
በ'ውነቱ አንቺስ እንዴት ነሽ እንደምን ይዞሻል ኑሮ
አብረን ከኖርነው አንፃር ምን ድባብ ሰፍኗል ዘንድሮ።
ካብሮነት የብቻው ጽዋ ጣፋጭ ነው ወይስ መራራ?
የኔ ቤት ውሉ ጠፍቶታል ያንቺን በይ ልስማው አደራ።
:
:
ይሰማ የሆድሽ ጩኽት ይዳረስ ቃልሽ ከልቤ
ካንቺው ጋር ያቆራኘኝን የኑሮን ድብቅ እሳቤ።
ስትጠፊ የጠፋኝ ፍቺ በቃልሽ ደርሶ እንዲገለጥ
ከህመም የመሻርን ምስ ንገሪኝ ቃልሽ ይደመጥ።
:
:
በይ አውሪኝ በልብሽ ቋንቋ ስሜትሽ በቃል ይዘርዘር
እንኳንስ የሰው ዝምታ መስታወት ወድቆ ሲሰበር
የሚታይ ጉልህ ገፅታ አይከርምም ፊት እንደነበር።
፡
፡
እንግዲያው ሞላም ጎደለ
ካንቺው መምጣት መሄድ ጋር ትርጉሙ ስለዋለለ
ሲገባኝ የተዛመደሽ በርግጥም አንድ እውነት አለ።
፡
፡
ቆላ ደጋ ሳትወርጂ ልክ ድሮ እንደነበረው
የታፈነው ጥልቅ ስሜት ዝምታሽን ከሰበረው
እማሬውን ሀቻ ፍቺ የመኖሬን ያን ድብቅ ጣ'ም
አንቺ ጎኔ ክተሚ እንጂ መቼም ቢሆን እኔ አላጣም።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘
አዘጋጅ፦ ፍቅሬን በግጥM
➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ !! ➢➢
Join us 👉👇 https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA
፡
፡
፡
ኑረት ማለት ምንድነው ትርጉሙ የያዘው ቅኔ
አንቺን ያጣሁኝ ለታ የጠፋኝ አብሮሽ ከጎኔ።
ምንድነው የቃሉ ፍቺ ለምን ነው ታዲያ መኖሬ
ያ ፅኑ ተራራው ልቤ ተዋክቡዋል እንደዚህ ዛሬ።
:
:
በ'ውነቱ አንቺስ እንዴት ነሽ እንደምን ይዞሻል ኑሮ
አብረን ከኖርነው አንፃር ምን ድባብ ሰፍኗል ዘንድሮ።
ካብሮነት የብቻው ጽዋ ጣፋጭ ነው ወይስ መራራ?
የኔ ቤት ውሉ ጠፍቶታል ያንቺን በይ ልስማው አደራ።
:
:
ይሰማ የሆድሽ ጩኽት ይዳረስ ቃልሽ ከልቤ
ካንቺው ጋር ያቆራኘኝን የኑሮን ድብቅ እሳቤ።
ስትጠፊ የጠፋኝ ፍቺ በቃልሽ ደርሶ እንዲገለጥ
ከህመም የመሻርን ምስ ንገሪኝ ቃልሽ ይደመጥ።
:
:
በይ አውሪኝ በልብሽ ቋንቋ ስሜትሽ በቃል ይዘርዘር
እንኳንስ የሰው ዝምታ መስታወት ወድቆ ሲሰበር
የሚታይ ጉልህ ገፅታ አይከርምም ፊት እንደነበር።
፡
፡
እንግዲያው ሞላም ጎደለ
ካንቺው መምጣት መሄድ ጋር ትርጉሙ ስለዋለለ
ሲገባኝ የተዛመደሽ በርግጥም አንድ እውነት አለ።
፡
፡
ቆላ ደጋ ሳትወርጂ ልክ ድሮ እንደነበረው
የታፈነው ጥልቅ ስሜት ዝምታሽን ከሰበረው
እማሬውን ሀቻ ፍቺ የመኖሬን ያን ድብቅ ጣ'ም
አንቺ ጎኔ ክተሚ እንጂ መቼም ቢሆን እኔ አላጣም።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘
አዘጋጅ፦ ፍቅሬን በግጥM
➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ !! ➢➢
Join us 👉👇 https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA