#የቀጠለ...
እውነት ነው ሪያል ውጤቶችን በመቀልበስ ተገዳዳሪ የሌለው የሰርፕራይዞች ክለብ ነው፤ ነገር ግን ውጤቱን ስንመለከት 3-0 በቀላሉ የመጣም ለመቀልበስ የሚቀልም ውጤት አይደለም። ከዚህ ቀደም በሶስት እና ከዚያ በላይ በሆነ ልዩነት ተሸንፈን መቀልበስ የቻልንበትን አጋጣሚ ለመመልከት የግድ ወደ ኋላ ብዙ ተጉዘን ወደ 1985/86 መሄድ ይኖርብናል...
1.
ይህም ውጤት በሞንቼግላድቫህ 5-1 የተሸነፍንበት እና በመልሱ ጨዋታ 4-0 አሸንፈን ያለፍንበት ነው።
2. እንዲሁም ከዚያ ውጤት አንድ አመት ቀደም ብሎ 1984/85 ያደረግነው ካምባክ ነበር እሱም በደርቢ ካውንቲ 4-1 የተሸነፍንበትን ውጤት 5-1 አሸንፈን በመገልበጥ ያለፍንበት ሲሆን...
3. ሌላኛው አጋጣሚ ደግሞ በ1975/76 የውድድር ዘመን በአንደርሌክት 3-0 ተሸንፈን የነበረውን ውጤት ወደ 6-1 ውጤት ቅልበሳ የቀየርንበት ነበር።
እነዚህ ውጤቶች በጊዜው የተከናወኑ ድንቅ የ3 ጎል ውጤት ቅልበሳ ቢሆኑም አሁን ላይ ካለንበት እውነታ ጋር ግን ማገናኘት አይቻልም፤ ምክንያቱም አርሰናል 3 ጎል ለመጨረሻ ጊዜ የተቆጠረበትን ጊዜ ለማስታወስ ግዴታ 83 ጨዋታ ወደ ኋላ ተጉዘን ታህሳስ 2023 መሄድ ይኖርብናል። በተጨማሪም ስለማስቆጠር አቅማችን ብዙ ኮንፊደንስ ቢኖረን እና ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እንደሚሄዱልን ብናስብ ከዚህ ቀደም ክሊንሺት ከትልቅ ጨዋታ የጠበቅንበትን ጊዜ ማሰብ ተገቢ ይሆናል።
በተጨማሪም አርሰናል በዚህ የውድድር ዘመን በቻምፒዮንስ ሊጉ ከ10 ጨዋታዎች በኋላ የተቆጠሩበት ግቦች 6 ብቻ ናቸው፤ በመከላከሉ ካለው ጥንካሬ ባሻገር ቡድኑ በሜዳው ያደረገው ጥሩ የሚባል አፈፃፀም ለቤርናቡ የመልስ ጨዋታ ጥሩ ኮንፊደንስ እንደሚሰጣቸው የሚታመን ነው።
@ETHIO_REAL_MADRID_15@ETHIO_REAL_MADRID_15