ፍቅር እና ግጥም 🇪🇹


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Криптовалюты


ከሚቀበል:ይልቅ:የሚሰጥ:ብፁዕ:ነው

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Криптовалюты
Статистика
Фильтр публикаций


ሰዉ መስያቹ ነዉ ከ19ሺ በላይ ሰዎች ምትከተሉኝ ?🥺
.

"አሁን ድረስ እኮ
አዉሮፕላን በሰማይ ሲያልፍ ለማየት ሮጬ ወጣለሁ'' 😢

1.3k 0 0 10 108

ሁለት ሕፃናት እየተጫወቱ ነው.. በመሃል አንደኛው ልጅ ጓደኛውን "አትጩህ እናቴ ተኝታለች እንዳትነሳ.." ብሎ ተቆጣው.. ከዛ ጓደኛው ወደ መቃብር ይዞት ሄደና.. "እሺ እዚ በደንብ እየጮህን እንጫወት..?" አለው "ለምን.. " ብሎ ሲጠይቀው "እማዬ ከተኛች ቆየች.. ድንገት ስንጮህ ከተነሳች..😞" አለው..

ካጣነው በላይ ያጡ አሉ.. ችለውት እንጂ የኛ ጉዳት ከነሱ በልጦ አይደለም..

2.5k 0 21 13 206


3.5k 0 15 4 122

ልጅ ፡ አባቴ  ባህሪዬ እንዴት ቢሆን ደስ ይልሃል ?

አባት፡ እንደዚህ ሁን ልጄ

ልጅ ፡ እንዴት ?

አባት ፡ እንደ ውሃ ሁን ባስቸገረ ግዜ እሳትን ቢያጠፋም በተፈለገ  ጊዜ ግን እንዲገኝ  ዛፍ ማሳደጉን አይተውምና ፤ እንደጨውም ሁን ለሁሉም  ምግብ  ቢፈለግም በቀላሉ  ይገዛ ዘንድ ግን-ዋጋው ውድ  አይደለምና ፤

ከሁሉ ከሁሉ-ግን እንደ ወተት ሁን በተውት ግዜ በሌላ-መልክ ተመልሶ  ይመጣል  እንጅ አይበላሽምና-በተገፋም ግዜ ከፍ ከፍ ይላልና።

ልጅ፡ እሽ አባቴ እንዳልሆንስ የምትፈልገው  የለም ?

አባት አለ ልጄ፤ እንደዚህ  አትሁን
ልጅ ፡ እንዴት  ?

አባት፡ልጄ ሆይ እንደ መርፌ አትሁን  የሌሎች ብዙ ቀዳዳ  እየደፈነ የራሱን አንዷን መድፈን አይችልምና፤ እንደ  መቋሚያም አትሁን  ለሌሎች መደገፊያ እየሆነ ለራሱ  ግን መቆም  አይችልምና ፤ ...............

4.3k 0 32 6 133

ምን እያረግሽ ነው?

"ጉንፋን አሞኝ ማር እየጠጣው"

ቱ የመጨረሻው ዘመን ደረሰ ማለት ነው 😭

"ምነው?"

በመጨረሻው ዘመን ማር በማር ላይ ይነሳል😁

4.9k 0 20 2 241

"ከሰው ኳኳታ እንነጠል
ለአንድ አፍታ እንኳ እንገለል
በፎይታ ጥላ እንጠለል
ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል"

.


ተስፋችን ላይ ትዕግስትን ካልጨመርንበት የዛሬ ጭንቀትን የነገን ደሞ መራር ህይወትን ታስጎነጨናለች ትዕግስት ከልባቹ አይጥፋ

.

6.1k 0 14 11 129

🥀°• በህይወትህ ቀናት ፈጽሞ አትጸጸት፡
      መልካም ቀናት ደስታን ይሰጣሉ
      መጥፎ ቀናት ልምድን ይሰጣሉ
 በጣም መጥፎዎቹ ቀናት ትምህርቶችን ይሰጣሉ
    እና ምርጥ ቀናት ደሞ ትዝታን ይሰጣሉ
◈✨

7.5k 0 26 8 171

◦ፍቅር ማንም ሊያየው ፣ ሊረዳው እና ሊያስተውለው ያልቻለውን ማንነት ማወቅ ከሚፈልግ ሰው ጋር መሆን ነው።❤️‍🩹


.

8.1k 0 25 3 134

🙏🙏እናቴን አፍልጉኝ 🙏🙏

ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቱዋቸው እናታችን በቀን 03/06/2017 ዓ.ም እንደወጡ ወደ ቤታቸው አልተመለሱም ለመጨረሻ ጊዜ የታዩት ሳሪስ አቦ ቤተ/ክርስትያን አካባቢ ነው እና መናገር እና ሃሳባቸው መግለጽ ስለማይችሉ ያሉበትን የምታቁ በዚህ ስልክ ቁጥር ጠቁሙን ።
0953429684
0962171562
0943049266

ይሄንንም ቪድዮ share https://youtu.be/uEnCM15nuS4?si=REElDsn19XZfD4Xm


●በፍቅር ላይ ስትሆን እና ስትጎዳ ልክ እንደ መቆረጥ ነው - ይድናል ግን ሁሌም ጠባሳ ሆኖ ይኖራል።🥀

6.9k 0 28 13 146

💝💝 የልቤ ትርታ 💝💝

‍ ​​         
            ◅አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ▻

      
♥️🌺 የመጨረሻው ክፍል 🌺♥️


◆እነመቅደስም መሞቱን አምነው ሀዘን
ሲቀመጡ መቅደስ እራሷን ለማጥፋት ስትሞክር ሀሉም በንባ
ታጥበው ነበር.............
.........ቢያንስ መቅደስ ከሶስቴ በላይ እራሷን ልታጠፋ ስትል
እየደረሱ አድነዋታል በዚህም የተነሳ ብቻዋን ጥለዋት ወተው
አያውቁም ዛሬ ግን አጋጣሚ ሆነባቸውና ቅብጥብጡን ቅዱስን
አደራ ብለውት ከፊቷ እንዳይጠፋ አስጠንቅቀውት ጉዳይ
ስለነበረባቸው ሁሉም ወጡ እንደእብድ ያረጋት መቅደስ አሁንም
የጌዲዮን መሞት ስታስብ መሞት አማራት ከዛ ብዙ ኪኒን
ለመዋጥ ስታስብ ቅዱስ አለ ከዛም ሱቅ ልትልከው አስባ ቅዱሴ
ስትለው ወዬ አላት ሱቅ ሄደህልኝ ና አለችው አረ ላሽ በይ እነ
ማሚ ጥዬሽ እንዳልሄድ አስጠንቅቀውኛል ሲላት ሴት እኮ ነኝ
ታዲያ ልበላሽ አላሳዝንህም ስትለው ምንድነው የምገዛልሽ አላት
እ .እ. እንትን ልክ እንደፈራች ሆና መርበትበት ጀመረች ደሞ
ከዚህ ውጪ ምንም ቢሆን እንደማሄድላት ታውቃለች ከዛም ካፏ
ቀበል አርጎ እየሳቀ ሲስቱ ብዙ አትጨናነቂ ገባኝ የሴቶች
ፓንፐርስ ነዋ ሲላት ሂ ሞዛዛ ብላ በጥፊ አለችው ከዛም
አደራውን እረስቶ ሊያመጣላት ተስማማና ብር ተቀብሏት ሄደ
እንደሄደም ኪኒኑን ሰብስባ ልትውጠው ስትል የቤታቸው ስልክ
ጮኸ ዝም አለችው አሁንም ልትውጥ ስትል ጮኸ አሁንም
ዝም አለችው ከዛም አሁንም ልትውጥ ስትል ሞባይሏ ጮኸ
በንዴት አንስታ ሄሎ ስትል ሀይ መቅዲዬ ብሩክ ነኝ በቤትስልክ
ስደውል የሚያነሳ የለም ደንዝዛ ቀረች በዛ ላይ የብሩክ ድምፅ
ፍፁም ልክ አልነበረም መልስ ልትሰጠውም አንደበቷ አልፈታም
አለ ከዛም በዛ በተዘበራረቀ ድምፁ አሁን ኤርፖርት ነኝ ነገ ማታ
12 ሰአት ስለምንደርስ ኤርፓርት ጠብቁን አላት ጌዲስ ሞተ
አይደል ብላ ልትጠይቀው አስባ ካፏ ሳታወጣው ስልኩ ተቋረጠ
እንባ ካይኖቿ ዱብ ዱብ እያለ ብቻዋን ስታወራ ቅዱስ ተመልሶ
መጣ ሲያይት ደንግጦ ምን ሆንሽ አላት መልስ አልሰጠችውም
ክፍሏ ገብታ ተኛች ማታ ቤተሰቦቿ መጡ..........
ተሰብስበው ሳሎን ቁጭ ባሉበት ያለወትሮዋ መጥታ መሀላቸው
ሶፋው ላይ ቁጭ አለች ሁሉም አይን አይኗን ማየት ጀመሩ
ምክንያቱም አብራቸው መሆን ካቆመች ቆየች መሬት መሬቱን
እያየች ብሩክ ነገ ይመጣል አለቻቸው ምን አሏት አዎ 12ሰአት
ተቀበሉኝ ብሏል ስትላቸው ጌዲዮንስ አሏት እኔንጃ አላቅም ብላ
ተመልሳ ወደክፍሏ ሄደች......
......መድረስ አይቀርምና የመምጫቸው ሰአት ሲደርስ ሁሉም
ተሰብስበው የኤርፖርቱ በር ላይ በሁለት ስሜት ይጠባበቁ ጀመር
ግማሹ ተሳፋሪ ወጣ ቡሀላም ብሩክ ወደነሱ ቀረበ ግን እሱን
ሳይሆን ሁሉም የሚያዩት ባይናቸው የሚፈልጉት ጌዲዮንን ነበረ
ቢሆንም አጡት አባትየው ቀስ ብሎ መቅደስን ደገፋት ሁሉም
ልባቸው ቀጥ ልትል ምንም አልቀራትም ተስፋቸው ተሟጦ
የጌዲዮን ሞት አምነው ለመጮህ እራሳቸውን ሲያዘጋጁ
በስተመጨረሻ ባልጋ እየተገፋ ቻው ብሏቸው የሄደው ጌዲዮ
ድኖ ጋቢ ለብሶ ከቅዱስ ቡሀላ እየተራመደ መጣ...........
............ሁሉም በህልም አለም ያሉ መሰላቸው መቅደስ
በጩኸት ዘለለች ሌሎቹም እየተንበረከኩ በምስጋና ላምላካቸው
መስገድ ጀመሩ መቅደስ እንደጨቅላ ፍየል እንደንቦሳ ጥጃ ከዛ
ከዚህ መሯሯጥ ጀመረች የታመነችለት ፍቅር ታመነላት ጌዲዮንን
አሳልፎ ለሞት አልሰጠባትም ከሩቅ ገና ሲያያት ጌዲዮን
እየተንደረደረ ወደሷ መጣ እሷም እየሮጠች ወደሱ ስትሄድ
መሀል ላይ ተገናኙ ከዛም ሊያቅፋት ሲል ተመልሳ ወደቤተሰቦቿ
ተንደረደረች ጌዲዮ ደነገጠ እሷን እሷን እያየ እንባውን አዘራ
እሷም እያለቀሰች እየዘለለች አባ አባዬ እሱ ነው ጌዲዮን
አልሞተም እኮ እያለች እውን የሆነውን ህልሟን ትተርክ ጀመር
በሁኔታዋ እንኳን ቤተሰቦቿ ያያቸው የተመለከታቸው አለቀሰ
ከዛም ወደጌዲዮ ተመለሰች አሁንም ሳታቅፈው ተመለሰች
ጌዲዮን ደስታዋ መሆኑን ሲያውቅ ከመሬት ተንበርክኮ በንባ ታጠበ
ፈጣሪውን አመሰገነ ለሶስተኛ ጊዜ ስትመጣ አሁንም
እንዳትመለስ ሁልቱን እጆቿን ጭምቅ አርጎ ይዞ ጉንጮቹ ላይ
አረጋቸው የናፈቀው አይኗ የናፈቃት አይኑ ተፋጠጡ ፍቅር
የተራበው ልባቸው በሀሴት ጮቤ እረገጠ ከንፈራቸው
ተንቀጠቀጠ ናፍቆትና ፍቅር የጋረደው አይናቸው በዙሪያቸው
የሚመለከታቸውን ህዝብ አላስትዋሉም ጌዲዮንም ቤተሰቦቿ
መኖራቸውን እረሳው ብቻ ለመጨረሻ ጊዜ ሳማት የተባለ
ይመስል ያኔ የመጀመሪያ ቀን እንደሳማት ግጥም አርጎ ከንፈሯን
ጎረሰው አቤት ሲያምሩ አቤት ሲያስቀኑ መፋቀርስ እንደነሱ
ፀጉሯን እየዳበሰ እሷም አንዴ ጉንጩን አንዴ ወገቡን አጥብቃ
እየያዘችው እያገላበጠ ያለምንም ፍራት ይሳሳሙ ጀመር
ቡሀላም አለመላቀቃቸውን ቀበጡ ቅዱስ ሲያይ ጠጋ ብሎ
እህህ እህህ አረ እኛንም ሰላም በለን ናፍቀኸናል እኮ ሲለው
ጌዲ ደንገጥ አፈር ብሎ መቅደስን ለቀቃትና ከመጣህ
ትመልስልኛለህ ብላ ያጠለቀችለትን ያንገቷን ማህተብ አውልቆ
አጠለቀላት ከዛም ግንባሯን ስሞ ሁሉንም እያቀፈ በንባ ሰላም
አላቸው..............
.............ወደቤትም እንደሄዱ እራት በሉ ቡናም እየጠጡ
እናቱን ጠየቃቸው ከዛም ገዳም እንደሆኑ እሱ ሲሄድ
እንደሚወጡ ነገሩት መቅደስ ከቅፉ አልወጣችም ነበረ በቃ
ከናንተ ጋር ናፍቆቴን ይህን ያክል ካሳለፍኩ ነገ እሄዳለሁ እሜ
እጅግ በጣም ነው የናፈቀችኝ አላቸው ከዛም የመቅደስ እናት
በቃ መቅደስም አብራህ ትሂድ ባይሆን ጓደኞቿ እሁድ
ስለሚመረቁ በዛውን የደስታችንን ድግስ አብሬ እደግሳለሁ
ቅዳሜ እናትህን ይዛችሁ እንድትመጡ ሲሉት እንዴ መቅዲስ
አትመረቅም አላቸው መቅደስ ቶሎ ብላ አይኗን ከመሬት ተከለች
አባቷም አይ ጌዲ እንኳን ከትምርት ከራሷም አለም ወታ ነበር
እኮ ብለው የተፈጠረውን ተራ በተራ አስረዱት ጌዲዮን የመቅደስ
ፍቅር ካቅሙ በላይ ሆኖበት ከውስጡ ሸሸጋት.......
........ከዛም አገር ቤት ሲሄዱ አገር ምድሩ ተቀበላቸው እናቱም
በልልታ ፀሎቷን የሰማት አምላኳን እያመሰገነች ልጇን ከቅፏ
አስገባችው የናቱም ያባቱም ዘመዶች ጎረቤቱም ሳይቀር ከግሩ
ተንበርክከው ይቅርታ ለመኑት እሱም ይቅር ለእግዚብሄር
አላቸውመረገጣቸው መገፋታቸው ለበጎ ሆነ አሸናፊዎቹ ተሸነፉ
ተሸናፊዎቹ አሸነፉ!!!!!...........

        
💝  ተፈፀመ  💝

                
●የታል Like 👍

○○○○○○○♥️♥️♥️♥️♥️♥️●●●●●●●

6.8k 0 17 24 134

📚#ከመጣጥፍ_ዓለም
~~~~
●ራሳችንን የምናይበት አስገራሚ ታሪክ»

አንዲት ወጣት ሴት ለጉዞ ኤርፖርት ውስጥ ተቀምጣለች።
አውሮፕላኑ እንደሚዘገይ ባወቀች ጊዜ ኤርፓርት ውስጥ
ካሉት ሱቆች ኩኪስና መጽሐፍ ገዛች።

ወደ VIP (የተመረጡ ሰዎች ብቻ ወደ የሚስተናገዱበት)
ክፍል ገብታ ለንባብ ምቹ ወደ ሆነው መደገፊያ ወንበር
አመራች። ተደላድላ ተቀምጣ ማንበብ ጀመረች።

አጠገቧ እንድ ሰው መጽሐፍ ያነባል። በሁለት መደገፊያ
ወንበሮች መሐል ኩኪስ ተቀምጧል። በንባቧ መካከል
መተከዢያ
ሆኗታል።

ታዲያ ከኩኪሷ አንድ ስታነሳ ሰውየውም አንድ አነሳ ገረማት።
ሳያስፈቅዳት መውሰዱ አስደነቃት። ግን ዝም አለች። ቀጥላ
እርሷ አንድ ስትወስድ እርሱም ሌላ ወሰደ አሁን ተበሳጨች።
ድፍረቱ አናደዳት። በዚህ አላበቃም እስከ መጨረሻው
ቀጠለ።
ቅጥል አለች! ግን ንቃ ተወችው።

በአካባቢው ያሉ ሰዎችን አትኩሮት መሳብ አልፈለገችም።
ለዚህ ብቻ
አይደለም በኩኪስ ምክንያት ጸብ ረብሻ መፍጠር
አልፈለገችም።
እንዲህ እንዲህ እያለ የመጨረሻ አንድ ኩኪስ ቀረች።

" ይሄ የተረገመ ሰው ምን ያደርግ ይሆን? " ስትል አሰበችና
በቀስታ ማየት ጀመረች። ከዚያም ሰውየው ኩኪሷን ሁለት
ቦታ ከፈላትና ግማሹን ወሰደ። ለድፍረቱ ጥግ አጣችለት።
ከልክ ያለፈ ስርዓት የለሽ እንደሆነ ደመደመች።

ሰዓቱ ደርሶ አውሮፕላን ላይ እንደተሳፈረች መነጽር
ለማውጣት ቦርሳዋን ስትከፍት አይኗን ማመን
አልቻለችም። ያልተከፈተው የታሸገው ኩኪሷ ቦርሳዋ
ውስጥ አለ። በጣም አፈረች ተሸማቀቀች።

ለካስ የራስዋን ኩኪስ ቦርሳዋ ውስጥ ረስታ የሰውየውን ነበር
ስትበላ የቆየችው። ከሁሉም በላይ በጣም ያጸጸታት ሰውየው
እስከ መጨረሻው አንዲት ኩኪስ እስክትቀር ድረስ ያካፍላት
የነበረው ምንም ሳይቆጣና ሳይመረር በደስታ መሆኑ ነበር።

የራሱን ኩኪስ እየበላች በሰውየው ላይ ስትበሳጭበት
በመቆየቷ እጅግ አፈረች። አሁን ይቅርታ ለመጠየቅ እንኳን
ጊዜው አልፏል። እርሱም በሌላ አውሮፕላን ወደ ሐገሩ
አቅንቷል። እርሱን የማግኘት አንድ ተጨማሪ እድል እንኳን
የላትም።

ብዙ ተመኘች ማመስገን፣ ይቅርታ መጠየቅ፣ ጉዳዩን
ማብራራት፣
ግን ሁሉም እሷው ጋ ቀሩ አልፏል። አራት የማይጠገኑ
ነገሮችን
አሰበች፦
1. ድንጋይ ከተወረወረ በኋላ
2. ቃላት ከተናገርናቸው በኋላ
3. ድርጊቶች ካመለጡን በኋላ
4. ጊዜ ካለፈ በኋላ ዋጋ እንደሌለው

እኛም ምንም ነገር ከመናገራችን ከመፈፀማችን በፊት
መጀመሪያ
ራሳችንን እንይ ።


💝💝 የልቤ ትርታ 💝💝

‍ ​​         
            ◅አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ▻

                 
#ክፍል_❷❼

➞የንስሀ አባታቸውም ብዙ አስተማሯቸው ስለይቅርባይነት
ብዙ ነገሯቸው በስተመጨረሻም እግዚያብሄር ሊፈትነኝስ ቢሆን
ብለው አሰቡና ልጄን አትርፍልኝ እንጂ እንኳን ይሄንን ስንቱን
ችያለሁ ብለው ይቅር ለግዚያብሄር አሉ ሰላም ወረደ ገዳምም
ገብተው ፆም ፀሎታቸውን ተያያዙት.................
.........መቅደስ አዘውትራ የምትሄደው ጌዲዮ የሚያጠናበት
ጫካ ነው ነገ ትምርት ጨርሰው ወደየመጡበት ይበተናሉ
ያመጣችው ውጤት ምንም ከሷ የማይጠበቅ ነው ይሄ ወር
ደግሞ ያምስተኛ አመት ተማሪዎች የጌዲዮ ጓደኞች ምርቃት
ነው ህመሟን ጨመረው ስለምርቃቱ ጓጉቶ የነገራት
እያስታወሰች በተለይ ምን ታመጪልኛለሽ ሲላት ያገር አበባ
ያለችው ብቻ ሁሉንም እያስታወሰች በንባ እየታጠበች
ነው........
.....እውነትም አልቀረም የምርቃታቸው ቀን ደረሰ የዛ ቀን
መቅደስ በጠና ታመመች ሀኪም ቤትም እንዳትወሱዱኝ አለች
ከዛም እቤት ድረስ ዶክተር አመጡ ዶክተሩም አክሞ ሲጨርስ
በጣም በናፍቆት ተጎድታለች ምግብም ካለመመገቧ የተነሳ
እራሷን መቆጣጠር ተስኗታል በተቻላችሁ አቅም የናፈቀችውን
ሰው ብታገናኟት ጥሩ ነው ሲላቸው አይ ዶክተር ይሄማ መች
ጠፋን ለማንኛውም እናመሰግናለን አሉት..... በቃ ከዛን ጊዜ
ጀምሮ ጭራሽ ከክፍሏ አልወጣም አለች ያምስተኛ አመት
ትምርቷንም ልክ እንደጌዲዮ አቆመች ቤተሰቦቿ እግሯ ላይ
ቢወድቁም አልማርም አለች ግዜም መሄዱ አይቀርምና ጌዲዮ ሁሉንም ቀዶ ጥገና
በወዳጆቹ ፀሎትና በፈጣሪ ፍቃድ በሰላም አጠናቆ የመጨረሻው
ቀዶ ጥገና ለማድረግ ቀጠሮው ደርሶ ወደ ቀዶ ጥገናው ክፍል
አስገቡት......ብሩክ ከዚህ ቡሀላ ጌዲዮ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ
አልቻለም አንድም መልስ የሚሰጠው ዶክተር አጣ ይሙት ይኑር
ምኑን አውቆት ቤተሰቦቹም አስጨነቁት ግራ ቢገባው ሞቶም
ከሆነ ቁርጤን ንገሩኝ አላቸው የህክምናው ክፍል መግባት
አይቻልም መልስ የሚሰጠው አጣ ለምን የሚል ጥያቄ
ጭንቅላቱ ውስጥ ተፈጥሮበት በከፍተኛ ሀዘን ተዋጠ ለብዙ
ሳምንታትም የተለያየ ምክንያት እየሰጠ ቢሸውዳቸውም በስተ
መጨረሻ ግን አልቻለም ሁሉም አፋጠጡት ስልኩን ሙሉ ለሙሉ
ኦፍ አረገው በቃ ከዚህም ቡሀላ ቤተሰቡ ሀዘን ተቀመጠ
መቅደስ ካንዴም ሁለቴ እራሷን ልታጠፋ ስትል ደርሰው አዳኗት
እንኳን የጌዲዮን የብሩክን ድምፅ ከሰሙ ወራቶች ተቆጠሩ...
.....ጌዲዮና መቅደስ ከትውውቅ ጀምሮ እስካሁን በጣም ብዙ
ፈተናና መከራ አሳልፈዋል ከምንም በላይ ግን ያለፈው ግማሽ
አመትና ይሄ አመት በሳት የተፈተኑበት ወቅት ነው ትምርቷን
አቁማ ከቤት አልወጣም ካለች ይኸው አመት ሊሞላት ነው
ብትወጣ እንኳን አምላኳን ልትለምን ቤተክርስቲያን ብቻ ነው
የጌዲዮ እናትም ገዳም ገብተው ሱባኤ ከጀመሩ ሰንበትበት አሉ
የመቅደስ ቤተሰቦችም የጌዲዮ ጓደኞችም ብቻ የሚያውቁት ሁሉ
በፀሎት አልተለዩትም
ጌዲዮ የመጨረሻውን ቀዶ ጥገና ሊያደርግ ከገባበት ወቅት
አንስቶ አስታማሚው ብሩክ ስለሱ ሁኔታ የሚነግረው አጥቶ
ተስፋ ሲቆርጥ ቤተሰቦቹም እየደወሉ እንዴት ሆነ ሲሉት ስልኩን
ሙሉ ለሙሉ ሲያጠፋ...

🥀አንብበው ሲጨርሱ #LIKE ማድረግ አይርሱ


➜ ክፍል ❷❼ ከ ❶⓪⓪ 👍 በኃላ ይቀጥላል...

5.9k 0 15 14 86

ፍቅር ታጋሽ ነው, ፍቅር ቸር ነው. አይቀናም፣ አይመካም፣ አይታበይም፣ ባለጌ አይደለም፣ የራሱን ጥቅም አይፈልግም፣ አይበሳጭም፣ ቅሬታን አይመዘግብም፣ በፍትሕ መጓደል ደስ አይለውም፣ ግን በእውነት ይደሰታል። ፍቅር ሁሉን ይታገሣል በሁሉ ያምናል ሁሉን ተስፋ ያደርጋል በሁሉ ይጸናል::❤️


❤️‍🩹 ከልብ ያደረጉትን ሰው መሸኘት እንዴት ይከብዳል። ያፈቀሩትን ሰው ሩቅ መስደድ እንዴት ያማል።ከዚህ ሁሉ በኃላ ያሳለፉትን መርሳትስ እንዴት ይቻላል።መቼስ አለማስታወስ፤ትዝ አለማለት፤ከልብ አንቅሎ ማውጣት እየታመሙ ነው እንጂ እየተደሰቱ አይሆን፤እያለቀሱ ነው እንጂ እየተሳሳቁ አይሆን፤ልብ ተሰብሮ ነው እንጂ ተጠግኖ አይሆን።ቢሆን ቢሆንማ፤ቢሳካ ቢሰካማ እንዲሁ እንደዋዛ መርሳቱ ቢኖርማ ሁሉን ረስቶ ነፃ ሆኖ መኖር ይቻል ነበር።


💝💝 የልቤ ትርታ 💝💝

‍ ​​         
            ◅አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ▻

                 
#ክፍል_❷❻

‍ ​

➜ጌዲዮን ለህክምና ውጪ ከሄደበት ቀን አንስቶ መቅደስ
ሀሳቧን መሰብሰብ ተሳናት ቃሉን ለማክበር ስትል ወደ ግቢ
ብትመለስም ከትምርቷ ይልቅ ሀሳቧ ስለጌዲዮ ሁኔታ ወንድሟ
የሚልክላትን መረጃ ለማወቅ ነበር ጉጉቷ ያው ዶክተሩ እንዳለው
ቀዶ ጥገናው ባንድ ጊዜ የሚከናወን ስላልነበረ ቀዶ ጥገና
አለው ባላት ቁጥር በሀሳብና በጭንቀት ቀድማ የምታልቀው እሷ
ነች........
.....አረ ጌዲዮስ ቢሆን የሞት አፋፍ ላይ ቆሞ ሞትን የሚፈራ
የመጀመሪያው ሰው እኔ ነኝ ብሎ እስኪያስብ ድረስ ሞትን ፈራው
ዳግም የናቱንና የመቅደስን አይኖች አለማየቱን ሲያስብ ሞትን
አብዝቶ እረገመው ከበሽታው በላይ ናፍቆት ጎዳው መለየቱ
ህመም ሆነበት የመቅደስ ፈገግታ ጨዋታዋ ሳቂታነቷ ፍቅሯን
መቋቋም አቃተው በተለይ አብራ የታመመችለት ህመሟ
ከማንም አስበልጣ ተማርኮ የማረከው ፍቅሯ እህህህህ እያረገ
ውስጥ ውስጡን ሌላ በሽታ ሆነበት......... በመመረቂያው
ወቅት ሆስፒታል መተኛቱን እረስቶ መቅደስን አግብቶ ለናቱ
የልጅ ልጅ ማሳየት አማረው ሌላ ተስፋ ምን አልባትም እውን
የማይሆን ህልም...አለቀሰ አብዝቶ አነባ..........
.......ብርሀን ሰአዳ ወይንሸትም ብትሆን መቅደስ እንድትረጋጋ
ዘና እንድትል ብዙ ጥረት እያረጉ ነው ቢሆንም እንዳሰቡት
አልሆነላቸውም ምክንያቱም ከነሱ ጋር ከመሆን ይልቅ በፊት
ጌዲዮ የሚሄድበት የሚያዘወትርበት ስፍራ እየተቀመጠች
ብቸኝነቷን መርጣለች....ከሰው ተራ አውጥቶ ያረገኝ ብቸኛ
አውቃለሁ ፍቅርሽ ነው ይሄ መዘዘኛ ብሎ አይደል የዘፈነው
ጥላሁንስ ቢሆን........
.........የጌዲዮ እናት እነመቅደስ ቤት ትንሽ ከተቀመጡ ቡሀላ
ወዳገርቤት መመለስ እንደሚፈልጉ ለቤተሰቡ ሲናገሩ የመቅደስ
አባት ግራ በመጋባት ምን አጠፋን ሲሉ ጠየቋቸው የጌዲዮ
እናትም አረ ምን ቦጣችሁና የናንተን ውለታ እኮ ነብሴንም
ብሰጥ ከፍዬ አልጨርሰውም ግን ይህን መልካምነታችሁን
እግዚያብሄር ነው በሰማይ የሚከፍላችሁ ሰው የለም ባልኩበት
ወቅት ነው እናንተን አግኝቼ እውነትም የሰው መዳኒቱ ሰው ነው
ያልኩት ስትላቸው ታዲያ ምን አርገን ነው ጌዲዮ ሳይመጣ ልሂድ
የሚሉ ... አዪ እንጃ ብቻ አንድ ያለኝን ያይኔን ማረፊያ ዘሬን
መተኪያዬን ልጄን እንዳላጣው ልቤ ፈራ ታዲያ እዚህ ሆኜ
በሰቀቀን ከማልቅ ከቀያችን አንድ ገዳም አለ እዛው ሄጄ በሱባኤ
ፈጣሪ ጨክኖ እንዳይጨክንብኝ ብለምነው ይሻለኛል ብዬ
ነው..... እንደዛስ ከሆነ መልካም ፈጣሪ ጥሎ አይጥልም
ይለመናል እውነት ብላችኋል የተናቀን ያከብራል የተረሳን
ያስታውሳል አበቃለት የተባለን ታሪክ ይቀይራል አዎድ ይለመናል
........
........እንዳሉትም በንጋታው የጌዲይ እናት ወዳገርቤት ተመለሱ
አመሻሽ ላይ ስለነበር የደረሱት ቤታቸውን አዘገጃጅተው ነገውኑ
ወደገዳም ገብቼ ሱባኤዬን እጀምራለሁ ብለው አሰቡና
ኩርትምትም ብለው ጋደም አሉ የልጃቸው ነገር እያስጨነቃቸው
በሀሳብ ተውጠው በዛው እንቅልፍ ወሰዳቸው ለሊትም በራቸው
በሀይል ተንኳኳ እትዬ አስካል እትዬ አስካል የሚል ድምፅም
ሰሙ በራቸው በመንኳኳቱ ቢደነግጡም የሰሙት ድምፅ የንስሀ
አባታቸው መሆኑን ሲያውቁ ተረጋግተው በሩን ከፈቱ ስኪፍቱት
ግን እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ሽማግሌዎች ጎረቤቶቻቸው
እንዲሁም ለብዙ አመታት የራቋቸው የባለቤታቸውና የራሳቸው
ቤተሰቦቻቸው ደጃቸውን ሞልተውት ነበር የጌዲዮ እናት
በድንጋጤ ደርቀው ቀሩ የልጃቸውን መርዶ ነጋሪዎች መሰሏቸው
አንደበታቸው ተርበተበተ ሰውነታቸው ተንቀጠቀጠ ልባቸው ሄድ
መጣ ይል ጀመር በሚቆራረጥ ድምፃቸውም ልጄ ልጄ ምን ሆነ
አባ ሲሉ የንስሀ አባታቸውን ጠየቁ ነገሩ ግን ካሰቡት ውጪ ነበር
ይሄ ሁሉ ሰው የተሰበሰበው ይቅርታ ለመጠየቅ እንደሆነ ሲረዱ
ነብሳቸው አረፈች ግን ለምን ሲሉም ጠየቁ የልጃቸው
መታመምን ሰምተው እንደሆነም ሲነግሯቸው አለቀሱ በንባቸው
መስታወትም ያሳለፉትን የመከራ ሃያ አመታት ወደኋላ መለስ
ብለው አስታወሱ............
........ጌዲዮን ከልጆቻቸው ጋር አንድም ቀን እንዲጮት
ፈቅደውለት አያውቁም ለግዜር ሰላምታም ቢሆን ይፀየፏቸዋል
በዛላይ አሽሙራቸው መጥፎ ንግግራቸው ከሰው መሀል ሆነው
ሰው የተራቡበትን ጊዜያት ከማህበራዊ ኑሮ ተገለው የኖሩበት
አመታት አረ ስንት መከራ ስንት ስቃይ ግን ይህን ሁሉ ጨክነው
ነበር ጌዲዮን እዚህ ደረጃ ያደረሱት የሳቸው ቅስም እየተሰበረ
የልጃቸውን ሞራል እየጠበቁ ታዲያ ምነው ዛሬ ተስፋቸው ሊሞት
መሆኑን ሲሰሙ ለይቅርታ ሽማግሌ ሰበሰቡ የጌዲዮ እናት
አሻፈረኝ አይሆንም ይቅርታችሁን አልቀበልም አሉ...

🥀አንብበው ሲጨርሱ #LIKE ማድረግ አይርሱ


➜ ክፍል ❷❼ ከ ❶⓪⓪ 👍 በኃላ ይቀጥላል...


‍ 💝💝 የልቤ ትርታ 💝💝

‍ ​​         
            ◅አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ▻

                 
#ክፍል_❷❺

➜ወዲያው ዶክተሮቹ ተሯሩጠው ህክምና አደረጉለት ብዙም
ሳትቆይ መቅደስ መጣች መታመሙን ስታይ ወዲያው ቅዱስ
እንደነገረው ገባትና አንተ ነገርከዋ አለችው ወንድሟ ቅዱስም
መቅዲ ሙች ጠይቆኝ ነው ሲላት አረ ነው እንዴ ድሮም
ጥፋተኛዋ እኔ ነኝ አንተን ሰው ብዬ አምኜህ መሄዴ አሁን ላባ
ሳልናገር ቀጥ ብለህ ውጣ አረ መቅዲ በጥፊ ያላልኩህም
ታላቄ ስለሆንክ ነው ቆይ ቢሞትስ አታስብም እንዴ ስትለው እሺ
ይቅርታ አርጊልኝ ሁለተኛ አይደግመኝም አላት ሁሌ እንዲህ
ትላለህ ግን ሁሌም ታጥቦ ጭቃ ነህ ስትለው እንደምንም
አግባብቷት ይቅርታዋን አገኘ....
......ጌዲዮ ሲነቃ መቅደስ እጆቹን ተንተርሳ ተኝታ ነበር ከዛም
እጁ ሲንቀሳቀስ ነቃች አይኖቿን በንባ ሞልታ ጌዲዬ ደናነህ
ስትለው መቅዲ እሞታለኋ አላት መቅደስ ደንዝዛ ማነው ያለው
ደሞስ ቢሉስ ሰው ፈጣሪ ነው እንዴ አትሞትም ተጋብተን ልጆች
ወልደን አርጅተን ነው የምንሞተው ጌዲዬ ትተኸኝ አትሞትም
ብላ እያለቀስች ፊቱን እየተሽከረከረች ሳመችው ጌዲዮ አለቀሰ
መቅዲ ታቂያለሽ ሁሌ ከንቅልፌ ስነሳ እንደሚጥለኝ
እንደምወድቅ አቃለሁ ግን አንድም ቀን እንኳን እሞታለሁ ብዬ
አስቤ አላውቅም መቅደስ ተስፋዋ ተሟጦ ጮኸችበት ጌዲዮ
አትሞትም አትሞትም ብላ እያለቀስች ትታው ወጣች........
.......ወዲያውም ባስ ይዛ ቀጥታ ጅማ ዩኒቨርስቲ ዋናው
አስተዳዳሪ የዲን ቢሮ ሄደች እንባዋ ያለማቋረጥ ይፈስ ነበር
ሰውነቷ ከስቶ አይኗ ጎርጉዶ ጉንጯ ሟምቶ በተስፋ ማጣት
ተጎሳቁላ ጭራሽ መቅደስ አትመስልም አስተዳዳሪው ደንግጦ
መቅደስ አላት አዎ መቅደስ ነኝ የኔ እንደዚህ መሆን ገረመህ
አዎ ሊገርምህ ይችላል ምክንያቱም አባይን ያላየ ምንጭ
አመሰገነ ጌዲን አላያችሁትማ ካልጋ ተጣብቆ ሞቱን
እየተጠባበቀ ነው አያችሁ የዚህን ዩኒቨርስቲ ስም አራት አመት
ሙሉ አስጠራ ዘንድሮ በመመረቂያው ሲጠፋ ግን ምን ሆኖ ነው
እንኳን አላላችሁትም እሱ ባመጣው ውጤት ለስማችሁ
ለማስጨብጨብ ግን አንደኞች ናችሁ አስተዳዳሪው እንደምንም
አረጋግተዋት ስለተፈጠረው ነገር ለመረዳት ጠየቋት እሷም
ሁኔታውን በሙሉ በዝርዝር ነገረቸው ከዛም የዩኒቨርሲቲው
ኮሚቴዎች ሰብስበው መልስ እንደሚሰጧት ነግረዋት ወጣች
ስትወጣ ወይንሸትና በለጠው አንድላይ እየሄዱ አገኟት
ስለጌዲዮ ሲጠይቋት ሁሉንም ነገረቻቸው ከዛም ተመልሳ አ.አ
መጣች.................
...........ከዛም ጉዋደኞቻቸው እንዳቅማቸው ገንዘብ ማሰባሰብ
ጀመሩ የዩንቨሪስቲው አስተዳዳሪ እንዳሉት ተሰብስበው አንድ
ሀሳብ ላይ በመድረስ ዩኒቨርስቲው ማስታወቂያ ለቀቀ በዚህም
የተነሳ ቤታቸውም ሳይሸጥ ሌላም ከባድ ወጪ ሳያወጡ
የጌዲዮን ሙሉ ህክምና ወጪ የሚችል እስፖንሰር ተገኘ........
......ወዲያውም መቅደስ ጋር ተደውሎ የምስራቹ ተነገራት
ሁሉም ተስፋ በቆረጠበት ሰአት አዲስ ተስፋ በእውነት ደግማ
የተወለደች ያክል ነው የተሰማት ደስታዋንም ለሁሉም አጋርታ
አንድ ላይ ጮቤ እረገጡ ....።
......ዶክተሩም ጋር ሄዳ ገንዘቡ ተገኘ ይድናል አይደል አለችው
መቅደስ ይድናል ብዬ ተስፋ እንጂ እውነታውን ልነግርሽ
አልችልም ምክንያቱም ጌዲዮ የመጨረሻ ከፍተኛውን ቀዶ ጥገና
ነው የሚያደርገው ለዚም ካስር ወር እስከ አንድ አመት
በህክምና ሊቆይ ይችላል አላት የዶክተሩ ንግግር ደስታዋን
ቢያደፈርሰውም ለዚህ ያበቃን ፈጣሪ ነገንም አይጥለንም ብላ
ተስፋዋን ፈጣሪን አደረገች......
አብሮት ለማስታመም ማን መሄድ እንዳለበትም አባቷና እናቷ
ሲጠይቁ መቅደስ እኔ ነኛ አለች ቅዱስ እንዴ አንቺማ አትሄጂም
ልታስታምሚው ነው ወይስ በለቅሶ ልትደፊው መቅደስ ተናዳ አረ
ባክህ ስትለው እህቷም ብሩክም ሁሉም እሷ መሄድ እንደሌለባት
እና የጌዲዮን ቃል ለማክበር መማር እንዳለባት ነገሯት ከዛም
እኔ እኔ በሚል ክርክር ብዙ ከቆዩ ቡሀላ ብሩክ እንዲሄድ ተወስኖ
ፕሮሰሱ ተጀመረላቸው........
........ከዛም የበረራው ቀን እቤት ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ሁሉም
ዘመድ ጓደኛ ተሰብስቦ ቤቱ በንባ ታጠበ ጌዲዮ እቤት የመጣው
ባልጋ እየተገፋ ነው ቀና ብሎ እንኳን ቻው ሊላቸው አልቻለም
ነበር መቅደስማ ደግማም የማታየው እየመሰላት ነው በተለይ
ዶክተሩ በቀዶ ጥገና ወቅት ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት
ከባድ ነው ያላት ትዝ ብሏት ለቅሶዋ እርም የምታወጣ ነበር
የሚመስለው...........
............ከዛም ጓደኞቻቸው ያሰባሰቡትን ገንዘብ አስረከቡት
ብቻ ሁሉም የበኩላቸውን እያበረከቱ ሰላም እንዲመለስ
መልካም ምኞት ተመኙለት መቅደስ ግን እንደሌሎቹ ጥቅማ
ጥቅም ሳይሆን በጀሪካን ፀበልና እምነት አርጋ ለወንድሟ አደራ
ሰጠችው.....ኤርፖርትም ስትሸኘው ያንገቷን ማህተብ አውልቃ
ሂወቴ ያላንተ ባዶ ናት እኔ የምኖረው አንተ ስትኖርልኝ ነው
ተመልሰህ ከመጣህ ይህን ማህተብ ታስርልኛለህ ያለበለዚያ
ግን እኔም ተከትዬህ በሰማይ እምነቴን ማህተቤን
ትመልስልኛለህ ብላ ባንገቱ ላይ አሰረችለት ይህን ስትለው
ጌዲዮ ከተወለደ እንደዚህ ቀን አምርሮአልቅሶ አያውቅም አለቀሰ
እጇን እንደምንም ጨብጦ አደራ እግዚያብሄር ያረገውን
ቢያረገኝም እንዳትሸነፊ ነገ አዲስ ቀን ነው ትምርትሽንም አደራ
ተምረሽ የኔን ህልም አንቺ አሳኪልኝ አላት እንኳን እናቱ እንኳን
ቤተሰቦቿ በኤርፖርቱ ዙሪያ ያሉ ሰዎች ሁሉም በንባ ታጠቡ
ወንድሟም እያለቀሰ ሁሌም በዋታሳፕ በቫይበር ሁሌም
እንደሚገናኙ ቃል ገብቶላቸው በለቅሶ ተሰናበቱት........
እውነት ጌዲዮ ድኖ ይመጣ ይሆን????........

🥀አንብበው ሲጨርሱ #LIKE ማድረግ አይርሱ


➜ ክፍል ❷❻ ከ ❶⓪⓪ 👍 በኃላ ይቀጥላል...


አንዳንድ ሰዎች ከላይ ሲታዩ እኛን ለመርዳት እየሞከሩ ይመስላል። እውነታ ግን ውድቀታችንን ነው የሚጠብቁት።


አነሆ ከለሊቱ 7:00 ሆኗል እስከአሁን ያልተኛችሁ አንድ ጊዜ 🤝 ይቺን ጠቅ እናደርጋለን !!

5.7k 0 23 20 158
Показано 20 последних публикаций.