Репост из: Amharic Bible Study Head 📚
🆃🅷🅴 🅻🅰🆂🆃 🅿🅰🆁🆃
🔥🔥"የሚያየኝን ፊት ለፊት አየሁት "(የራሽያ ወጣት ኮሚኒስት)😱🔥
ክፍል :13
✍.......ኮሚኒስቶች ሀገር እያለን እንደ ሌለን ፣ዜግነት እያለን እንደ ሁለተኛ ዜጋ ቢቆጥሩንም ለእኛስ ሀገር አለች በእጅ ያልተሰራች ግንበኞች የምድር ጠቢባን ያላዩዋት ከአመታት ከዘመናት ከአባቶቻችን ከነአብረሀም ያቆም ይስሀቅ በፊት የተሰራች። በበጉ ደም የተጠራች ቅድስት ሀገር አለችን።ከሞት ወዲያ ለኛ መጠለያ ሆና አልፈን ከአምላካችን እና ከጌታችን ጋር እንደ ገና መኖር የምንጀምርበት ሀገር አለችን።
ከባእድ ከዚህ ጊዜያዊ ድንኳን መጠለያ አልፈን በልኡል ዙርያ ከበን እፎይ የምልበት በክርስቶስ ላመኑ ወደ በጉ እራት የሚታደሙበት ሀገር አለችን፣#መንግስተ ሰማይ። መጠለያችን ርስታችን ቀንና ለሊት ሳያቋርጥ የመልአክት ዝማሬ ሽብሸባ የምንሰማበት እኛም እንደ መለአክት ሆነን በዙፋኑ ፊት የምንሆንበት።ግርፋት ስቃይ መከራ መራርነት ምቀኝነት ሰው በሰው ወገን በወገኑ የማይጨካከንበት ሀገር ርስት አለን። በምስክርነታቸው አለምን ድል የነሱ በበጉ ደም ልብሳቸውን አጥበው ያነፁ የሚያዜሙ ቅዱሳን ወገን አለን ሊያውም ሰማያዊ ወገን። ትምህርት እና እውቀት እያለን እንደ መሀይም ምንም እንደማናውቅ ቢቆጥሩንም እኛስ ለአለም ሞኝነት የመሰላት ግን በብዙ ጥበብ እና ድካም ሳይሆን አመታት ሳንቆጥር ዝቅ ብለን በዙፋኑ ስር ተንበክከን ታላቁን ጌታ የጥበብ መጀመሪያውን አውቀናል። በማመን መዳንን ከነሱ ሰውሮ ለኛ ገልፆአልና።
ዛሬ ውበት እያለን ስለ እምነት የምንከፍለው ስቃይ መከራ ፣ጭንቀት ፊታችንን ቢያበልዘውም ከሰው መልክ ወጥተን ብንጎሳቆልም በሰማይ የለው አባታችን ከፊቱ በሚወጣው ብረሀን ፀዳል የውበትና የእውነት ጨረር ለነብሳችን ሲፈነጥቅ ልዩ ሰዎች እንሆናለን።ያለማቋረጥ ቁፋሮ አታካች ስራ ቅዝቃዜ እና ብርዱ ቢገለንም ጌታን ስናስብ የአሁኑ መከራችንን እንረሳለን። አንድ ጊዜ ያለወትሮአችን በዚያ ቅዝቃዜ እና ብርዱን መግለፅ በሚያስቸግረው ለሊት ጠሩን። የተለመደውን ስቃይ ከተቀበልን በኋላ ወደ አንድ ሜዳ ወሰዱን። ጨለማ ነው ቦታው ሜዳ መስሎን ስንራመድ ይዞን ወደ ታች ሁለት ሜትር ያህል ገባ። ከታላቅ ድንጋጤ የተነሳ የሞትን ያህል ሆነን ወደቅን። ከስሩ ቅጠል የሚመስል የተቆራረጠ ነገር ተቀብሎ አሰመጠን። እንደምንም ብለን ስንነሳ ያ ቅጠል ስስ እሾህ መሳይ ነገር ሰውነታችንን ወጋግቶ ከመቅፅበት ፊታችንን ና እጅ እግራችንን በአንድ ጊዜ አሳብጦ ያሳክከን ጀመር።(እንደኛ ሀገር ሳማ መሆኑ ነው) ኡኡኡኡኡኡ አልን። በመሬት ተንከባለልን። ያው ቅጠሉ ተመልሶ ይወጋናል።ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ እየጎተቱ አወጡን በዚያን ጊዜ የማልረሳው ሁላችንም በሹክሹክታ ""አይዞህ አይዞሽ ጌታ ይመጣል ""እየተባባልን ስንፅናና ያሳለፍነው ለሊት አይረሳኝም።ያበጠው አይናችን አፍንጫችን እስከማይለይ አድበልብሎናል።ማን ማን መሆኑ እስከማይለይ ድረስ ይህን በመሰለ ስቃይ ውስጥ እያለን ወታደሮቹ ትተውን ሔዱ።
ያን ግዜ በዛ ጭለማ ስፍራ ያየነው መለአክ እስከአሁን ያስደንቀናል። ቁመቱ ረዘም ያለ ልብሱ በታላቅ ብረሀን ነፀብራቅ የተከበበ የሚመስል አሁን ከፀጉር ቤት ተሰርታ የወጣች ዘይት የበዛበት ፀጉር ሆኖ እስከአንገቱ ጫፉ በጥንቃቄ የተጠቀለለ የወርቅ ዘንግ ሚመስል የያዘ ታላቅ የብረሀን ነፀብራቅ የተሞላ ፊቱ ርህራሄ የሚነበብበት ትኩር ብለው የማይንቀሳቀሱ አይኖች ሽፋሽፍቶቹም ችፍግ ብለው የበቀሉ ሲሆን ያጠለቀው ጫማ ወርቅ የሚመስል ባለ ልዩ ውበትና ድምቀት ያለው አንድ መለአክ ከፊት ለፊታችን በመሬትና በአየር መካከል ቆሞ አየን። ይህን ስናይ ሁላችንም ካለንበት ስፍራ ጩኸን ወደ ኋላ ወደቅን። እሱ ግን እጁን ዘርግቶ ንፁህ በሆነ የመስኮብ ቋንቋ እንደ ባለስልጣን መስሎ ""እናንተ #የልዑል አምላክ ታማኝ ባርያዎች ሰላም ለናንተ ይሁን""አለን። ማን ደፍሮ ይመልስለት። ያ ከደቂቃዎች በፊት ድካም ግርፋት ያቆሰለው ሰውነታችን በዚያ በሰማነው ቃል ተበረታታና ምንም እንዳልተፈፀመብን ሆነን ብድግ ብድግ አልን።ቢሆንም ወደኋላችን እያፈገፈግን መሔድ ጀመርንና ካለንበት ሆነን ወደ ምድር ወድቀን ሰገድንለት። እርሱ ግን በታላቅ ድምፅ ቁጣ በሚመስል ""እንዳታደርጉት ተጠንቀቁ ""አለን።ይቀጥላል.........
🔥🔥ይቀጥላል የቀሩትን ገፅ ለማግኘት join ይበሉ🔥🔥
🔥🔥 @AmharicBSH 🔥🔥
🔥🔥join👆👆👆👆🔥🔥