ጨው ውሀ ሊቀዳ ሔዶ በዛው ቀረ
ምን ሆኖ?
#ሟሙቶ
🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊
ብዙ የሚያሟሟ ነገር በሞላበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው።
social media ያሟሟል
የትምህርት ቤት ጓደኛ ያሟሟል
የሰፈር ጓደኛ ያሟሟል
የስራ ባልደረባ ያሟሟል
የቲቪ ፕሮግራሞች ያሟሟሉ
መጽሐፍት ያሟሟሉ ብዙ ብዙ
ውሀ ሊቀዳ ሔዶ እንዳንሟሟው ጨው እንዳንሟሟ ራሳችንን ከውሀ ከሚያሟሟ ነገር እንጠብቅ
"ቀዳሁ ብሎ #መቀዳት አለና።"
አተረፍኩ ብሎ መክሰር አለ
ክፉ ወደበዛበት ሀጢያት ወደ ነገሰበት ወደ ሚያሟሟው አንሂድ አንጠጋ አንቅረብ እንሽሸው
ጨው አንዴ ከሟሟ በኋላ ጨዉን ለይቶ ማውጣት ከባድ ነው ብዙ ጊዜ እና አቅም energy ይፈልጋል::
🌊🌊🌊🌊🌊🌊🌊🌊🌊🌊🌊🌊
ጨው ውሀ ውስጥ ለመሟሟት ጥቂት ደቂቃ ይፈጅበታል
ከወሀው ለመለየት ግን በchemistry ቀመር boiling process ያስፈልጋል።
🔬🔬🔬🔬🔬🔬🔬🔬🔬🔬🔬🔬🔬🔬🔬🔬🧪🧪🧪🧪🧪🧪🧪🧪🧪🧪🧪🧪
boiling ደግሞ እሳት አለው መቃጠል አለው መንደድ አለው።
በሀጢያት መንደር ከሟሟን እና ከተገኘን በኋላ ወደ ቀደመው መልካም ማንነታችን ለመመለስ ብዙ ጊዜ እና ብዙ እሳት እናልፋለን። የዘራውን ማጨድ ስላለብን
ከዚህ ሁሉ በፊት ግን አስቀድመን ራሳችንን ከሚውጡን ነገሮች እንጠብቅ
መጽሐፍ እንዲህ ይላልና
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
1ኛ ጴጥሮስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ ሕይወትን #ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች #ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤
¹¹ ከክፉ #ፈቀቅ ይበል፥ መልካምንም ያድርግ፥ ሰላምን ይሻ ይከተለውም፤
¹² የጌታ ዓይኖች ወደ #ጻድቃን ናቸውና፥ ጆሮዎቹም #ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፥ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው።
@AmharicBSH