በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
📖📖መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት ላንብብ📖📖
ክፍል ፪(2)
#የመጽሐፍ #ቅዱስ #አከፋፈል
መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ለሚሻ ሰው አከፋፈሉን ማወቅ ግድ ይለዋል የመጽሐፍ ቅዱስ አከፋፈል ሳይታወቅ የሚደረግ የንባብ ሂደት ወደማያውቁት ሀገር ገብቶ እንደ መቸገር ይቆጠራል።የንባብን አካሄድ ለማወቅ የመጀመሪያው በር የመጽሐፍ ቅዱስን አከፋፈል ማወቅ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ በሁለት ይከፈላል
1. ብሉይ ኪዳን(የቆየ ስምምነት)
2. ሐዲስ ኪዳን(አዲስ ስምምነት)ይባላሉ
እነዚህ በሁለት ተከፍለው የምናያቸው ብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳን የሰው ልጅ የሕይወቱ ምስጢር መገኛ ናቸው።ብሉይ ኪዳንን ለብቻው ከፍለን ስናይ፦
ብሉይ ኪዳን በአራት ይከፈላል
1. የሕግ ክፍል
2. የታሪክ ክፍል
3. የመዝሙርና የጥበብ መጻሕፍት
4. የትንቢት መጻሕፍት
ብሉይ ኪዳንን ስናነብ እነዚህን አራት ዓይነት በብሉይ ኪዳን የሚገኝ የመንፈስ ምግቦችን ለይቶ ማስተዋል ያስፈልጋል።በትክክለኛ አከፋፈላቸው ሲነበቡ አይደባለቁም ግብና አቅጣጫ ያለው ንባብ እናነባለን።በአራት የከፋፈልናቸውን የብሉይ ኪዳን አከፋፈል እንመልከት!
ብሉይ ኪዳን
1. የሕግ መጻሕፍት፦
=>ኦሪት ዘፍጥረት
=>ኦሪት ዘጸዓት
=>ኦሪት ዘሌዋውያን
=>ኦሪት ዘኁልቅ
=>ኦሪት ዘዳግም
2. የታሪክ መጻሕፍት
=>መጽሐፈ ኢያሱ
=>መጽሐፈ መሳፍንት
=>መጽሐፈ ሩት
=>1ኛ ሳሙኤል
=>2ኛ ሳሙኤል
=>1ኛ ነገስት
=>2ኛ ነገስት
=>1ኛ ዜና መዋዕል
=>2ኛ ዜና መዋዕል
=>መጽሐፈ ዕዝራ
=>መጽሐፈ ነህምያ
=>መጽሐፈ አስቴር
3. የመዝሙርና የጥበብ መጻሕፍት
=>መጽሐፈ ኢዮብ
=>መዝሙረ ዳዊት
=>መጽሐፈ ምሳሌ
=>መጽሐፈ መክብብ
=>መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን
4. የትንቢት መጻሕፍት
=>ትንቢተ ኢሳይያስ
=>ትንቢተ ኤርምያስ
=>ትንቢተ ሕዝቄል
=>ትንቢተ ዳንኤል
=>ትንቢተ ሆሴዕ
=>ትንቢተ አሞፅ
=>ትንቢተ ሚክያስ
=>ትንቢተ ኢዩኤል
=>ትንቢተ አብድዩ
=>ትንቢተ ዮናስ
=>ትንቢተ ናሆም
=>ትንቢተ ዕንባቆም
=>ትንቢተ ሐጌ
=>ትንቢተ ዘካርያስ
=>ትንቢተ ሚልክያስ
ናቸው!ይሄ የብሉይ ኪዳን አከፋፈል በ66ቱ መጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ነው።
ሐዲስ ኪዳንም እንደ ብሉይ ኪዳን በአራት ይከፈላል።
1. የወንጌል ክፍል
2. የታሪክ ክፍል
3. የመልዕክት ክፍል
4. የትንቢት ክፍል ናቸው
እነዚህንም እንደብሉይ ኪዳን በዝርዝር ስናይ
ሐዲስ ኪዳን
1. የወንጌል ክፍል
=>የማትዮስ ወንጌል
=>የማርቆስ ወንጌል
=>የሉቃስ ወንጌል
=>የዮሐንስ ወንጌል
2. የታሪክ ክፍል
=>የሐዋርያት ሥራ
3. የመልዕክት ክፍል
=>ከሮሜ መልዕክት እስከ ዕብራውያን ያሉት 14 መጻሕፍት
=>1ኛ እና 2ኛ ጴጥሮስ
=>1ኛ, 2ኛ እና 3ኛ ዮሐንስ
=>የያዕቆብ መልዕክት
=>የይሁዳ መልዕክት
በአጠቃላይ ቁጥራቸው 21 ነው።
4. የትንቢት ክፍል
=>የዮሐንስ ራዕይ
ከላይ እንደተገለጸው ብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳን እንዴት እንደሚከፈል ግንዛቤ በሚሰጥ መልኩ አይተናል።መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነብ በመጀመሪያ ሊረዳ የሚገባው መጽሐፍ ቅዱስ በሥርአቱና በየክፍሉ የተቀመጠ መሆኑን ነው።በመቀጠል የሚያነበው ክፍል ምን እንደሆነ ከአከፋፈሉ በስፋት መረዳት መቻል ነው።የሐዲስ ኪዳንና የብሉይ ኪዳንን አከፋፈል አጠቃለን ስንደምራቸው 8 ናቸው።
ሁለቱንም በተነጻጻሪነት ስንመለከት
ብሉይ ኪዳን ሐዲስ ኪዳን
1. የህግ ክፍል 1. የወንጌል ክፍል
2. የታሪክ ክፍል 2. የታሪክ ክፍል
3. የመዝ. የጥበብ 3. የመልዕክት ክፍል
4. የትምቢት ክፍል 4. የትንቢት ክፍል
የብሉይ ኪዳንና የአዲስ ኪዳንን መጻሕፍት አከፋፈል ለይቶ የሚያውቅ መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ የሚሄድበትን አቅጣጫ የሚያውቅ ሰው ይመስላል። መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ ከላይ ከተገለጸው አከፋፈል ተረድቶ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ወደ ብዙ እውቀትና ጥበብ ያሻግራል።
በቀጣይ
📖የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎም
📖የመጽሐፍ ቅዱስ ዘይቤ
📖የመጽሐፍ ቅዱስ ህዳግ አወጣጥ
📖የግዕዝ ቁጥር
📖መጽሐፍ ቅዱስን በጊዜና በሰዓት ከፋፍሎ የማንበብን ስልት እናያለን
ይቀጥላል
https://t.me/Abalibanos333