القناة التعليمية الرسمية للدعوة السلفية في الحبشة


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


☞ዋናውን የቴሌግራም ቻናላችንን ለማግኘት @AbuYehyaAselefy በዚህ ይቀላቀሉ!!
➲የዩቲዩብ ቻናላችንን ለማግኘት እና ቤተሰብ ለመሆን ⬇️
https://youtube.com/channel/UCrHkOu8UyG5-TDewqfcQG5Q
💡☞ለአስተያየት ወይንም ለጥቆማ እንዲሁም ስህተት ካያችሁብኝ በፍጥነት በዚች ይጠቁሙኝ ☞ @AbuYehyabot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: ሙሀመድ አል―ወልቂጢይ
👌 የቢድዓ ባልተቤቶች ሸይኾቻቸው ቢድዓን ሲያስተምሯቸው አፋቸው ከፍተው ይሰሙና ይቀበላሉ። ከሱና ሲያስጠነቅቋቸው አፋቸውን ከፍተው ይሰሙና ይቀበላሉ። በተቃራኒ ደግሞ የሱና መሻይኾች ከቢድዓ እና ከቢድዓ ባልተሜት ሲያስጠነቅቋቸው ደግሞ ይንጫጫሉ። እነዚህ ሰዎች ሸይኾቻቸውን ከአላህ ውጪ ጌቶች አድርገው ይዘዋቸዋል ተጠንቀቃቸው።

قال الله تعالى "أم لهم شركاء شرعوا لهم من الدين ما لم يأذن به الله"

وقال "اتخذوا أحبارهم ورهبانهم أربابا من دون الله"


🌿አዲስና  ወሳኝ ተከታታይ ደርስ
       ❀───📖📖📖───❀

📖 اسم الكتاب:-
↩️ «المـعـتـقـد الصــحـيــح»
📖 የኪታቡ ስም፦
↪️ «አል’ሙዕተቀዱ አስ’ሶሂህ»

🏝 ⇣⇣⇣•••⇣⇣⇣ 
📢[ክፍል አስራ ሶስት]
   ➶➹➶➹➶➹
📄ሪሳላዋን በ𝕡𝕕𝕗 ለማግኘት
➘➷➴➘➷
https://t.me/AbuYehyaAselefy/11970

📝تأليف:- فضيلة الشيخ الدكتور عبد السلام بن برجس آل عبد الكريم -رحمه الله تعالى-  ١٣٨٧ - ١٤٢٥ هـ
📝ፀሐፊ፦ ሸይኽ ዶ/ር  ዐብዱሰላም ቢን በርጂስ ኣሉ ዐብዱልከሪም አላህ ይዘንላቸው!

🎙الأستاذ الفاضل أبي أنس أبي جعفر محمد أمين السلفي «حفظه الله»
🎙
በውዱ ኡስታዛችን ኡስታዝ አቡ አነስ [አቡ ጀዕፈር] ሙሐመድ አሚን አላህ ይጠብቀውና

🏠ቦታ፦ 🕌 በሰለፍዮች ፉርቃን መስጂድ [ሸዋሮቢት ከተማ] የተሰጠ ወሳኝ ትምህርት

          •┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•

ይ   ቀ   ጥ   ላ   ል
👇👇👇 ጆይን ብለው ይከታተሉ
https://t.me/+w-uAkEZwibVlNzM8

📱⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy




አያሙል ቢድ ፆም ነገ ይጀመራል የቻለ ይፁም ያልቻለ ሌሎችን ያስታውስ!
=========>

↪️ የረጀብ ወር የአያመል'ቢድ ቀናቶች ነገ ሰኞ ይጀምራሉ። በወር ውስጥ 3 ቀናቶችን መፆም ተወዳጅ ነው። አያመል'ቢድ የሚባሉትን 13፣ 14 እና 15 ቀኖችን መፆምም ለብቻው ሐዲስ መጥቶበታልና ከቻሉ ይፁሙ።

||- አያሙል ቢድ --> ሰኞ 13
||- አያሙል ቢድ --> ማክሰኞ 14
||- አያሙል ቢድ --> እሮብ 15


📱⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy


🚫 የአላህ ታአምር በአሜሪካ ምድር

አሜሪካ ትላንት በሰው ሰራሽ እሳት የፍልስጢንን ምድር ስታቃጥል አዛውንትና ህፃናትን መኖሪያቸው ቀብራቸው እንዲሆን አድርጋ ከፍርስራሽ ስር ጀናዛ ስትቀብር የምእራቡ ዐለም በድል አድራጊነት ቁጭ ብሎ እያየ ነበር ከተሞች ወደ ምድረበዳነት ሲቀየሩ እርጥብና ደረቅ ሲቃጠል ማን አለብኝ ባይዋ አሜሪካ ገና ነው ጠብቁ ትል ነበርፍልስጢናዊያን አቅመ ደካሞች ነፍሳቸውን ማዳን የቻሉት ሲሰደዱ ደካሞቹ የሰው ሰራሹ እሳት በላያቸው ላይ ሲለኮስ የዛሬዎቹ ደም እንባ አልቃሽ የሆሊዩድ አክተሮች በሉዋቸው ሲሉ ነበር። የእናታቸው ጡት እንደጎረሱ ከፍርስራሽ ስር የቀሩ ህፃናትን ጀናዛ ማውጥት እንዳይቻል የአሜሪካ የጦር ጀቶች የቦንብ ናዳ ሲያወርዱ የአሜሪካ ባለስልጣናት ውስኪ ያገሱ ነበር። የፍልስጢን ሰማይ በሰው ሰራሽ እሳትና በአቅመደካሞች ደም ከለሩ ሲቀየር የዛሬዎቹ የሆሊዩድ አክተሮች ፊልም ይሰሩበት ነበር።
ምንዳ በሰሩት ስራ ልክ ነውና ዛሬ እብሪተኛዋ፣ ትምክህተኛዋ፣ ማን አለብኝ ባይዋ ዠ፣ አንባ ገነኗ አሜሪካ የስራዋን ውጤት ለማየት ተገዳለች። ፍልስጢንን ለማውደም በቢሊየን ዶላይ የመደበው ባይደን ዛሬ የደረሰበትን ውድመት ለማስቆም የሚችል ዶላርም ዠ፣ መሳሪያም ፣ የምርምር ተቋምም፣ የጦርም ይሁን የተማረ ሀይል አጥቶ የሚሆነውን በቁጭት ለማየት ተገደደ።
ከአላህ የተላከው እሳት ሎስ አንጀለስ ላይ ከፊቱ የሚቆም ሀይል የለም በቃህ ባይ የለውም ሁሉንም ነገር ያቃጥላል ያወድማል ያከስማል፣ ከተማን ወደ አመድነት ይቀይራል ። ዝነኞቹ የሆሊዩድ አክተሮች ማን ይወዳደረዋል ከሚባልለት መኖሪያቸው ባዶ እጃቸውን ወጥተው የሲቃ እንባ እያነቡ አለኝ የሚሉት ነገር እሳት ሲበላው እያዩ ነው። የአሜሪካ ባለ ስልጣናት የስብእና ዝቅጠትና የማንነት ማዝቀጫ ፋብሪካ የሆነውን ሆሊዩድን እሳቱ ሲበላው ለማየት እየተገደዱ ነው። ያ የዝቅጠት ፋብሪካ ሆሊዩድ ያ ፈጣሪ የሚባል ነገር የለም የሚሉ አክተሮች የሞሉበት የኩፍር መናሃሪያ የሆነው ሆሊዩድ እሳቱ ደረስኩ እያለው የይድረሱልኝ ጣር እያሰማ ሲሆን ጣኦቱ ባይደን እንደ ድንጋይ ቆሞ ከመቅረት ውጪ አማራጭ አጥቷል
የትኛውን የጦር ጀት ወዴት ያሰማራ ? ወደ ማን ይተኮስ ይበል? በማን ላይ ያቧርቅ ? በድን ሆኖ መቅረትና የሚሆነውን ከማየት ውጪ መላ የለውም። ለመሆኑ ባይደን የትላንቱን የፍልስጢንንና የኑፁሃን ህዝቦቿ ዋይታና ሲቃ በአይነ ህሊናው ይቃኝ ይሆን? ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ህሊናው እብሪት ጋርዶታልና ዛሬ በንፁሀን ደም የጨቀየው እጁ የዘራውን እያጨደ ነውና ልቦናው ታውሯል። በድን ሆኖ የሚሆነውን ከማየት ውጪ አማራጭ የለውም እሱም አጋሮቹም ሺ ጊዜ አምሳያቸው ቢጨመርም ምንም ማድረግ አይችሉም ምክንያቱም የአላህን ሰራዊት የሚገጥም የለምና
የፊራኦንን ሰራዊት በውሃ ያሰመጠ፣ የኑሕ ዘመን እብሪተኞችን ከሰማይና ምድ በታዘዘ ፍል ውሃ ያጠፋ የመድየንን የሉጥንና የሰሙድን ህዝቦች በመላኢካ ጩኸት ያጠፋ አምላክ በዛሬዎቹ እብሪተኞች ላይ ከሰራዊቱ መካከል የሆነውን እሳትና አውሎ ነፋስ ልኮ አሜሪካን እያመሰ ይገኛል። የጌታህ ሰራዊት እሱ እንጂ ማንም አያውቀውም።

«وَمَا جَعَلْنَا أَصْحَابَ النَّارِ إِلَّا مَلَائِكَةً ۙ وَمَا جَعَلْنَا عِدَّتَهُمْ إِلَّا فِتْنَةً لِّلَّذِينَ كَفَرُوا لِيَسْتَيْقِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ وَيَزْدَادَ الَّذِينَ آمَنُوا إِيمَانًا ۙ وَلَا يَرْتَابَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ وَالْمُؤْمِنُونَ ۙ وَلِيَقُولَ الَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٌ وَالْكَافِرُونَ مَاذَا أَرَادَ اللَّهُ بِهَٰذَا مَثَلًا ۚ كَذَٰلِكَ يُضِلُّ اللَّهُ مَن يَشَاءُ وَيَهْدِي مَن يَشَاءُ ۚ وَمَا يَعْلَمُ جُنُودَ رَبِّكَ إِلَّا هُوَ ۚ وَمَا هِيَ إِلَّا ذِكْرَىٰ لِلْبَشَرِ »
المدثر ٣١
"የእሳትንም ዘበኞች መላእክት እንጅ ሌላ አላደረግንም፡፡ ቁጥራቸውንም ለእነዚያ ለካዱት መፈተኛ እንጅ አላደረግንም። እነዚያ መጽሐፍን የተሰጡት እንዲያረጋግጡ፣ እነዚያም ያመኑት እምነትን እንዲጨምሩ፣ እነዚያም መጽሐፍን የተሰጡትና ምእምናኖቹ እንዳይጠራጠሩ፣ እነዚያም በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው (መናፍቃን)፣ ከሓዲዎችም አላህ በዚህ (ቁጥር) ምን ምሳሌ ሽቷል? እንዲሉ (እንጅ አላደረግንም)፡፡ እንደዚሁ አላህ የሚሻውን ያጠምማል የሚሻውንም ያቀናል የጌታህንም ሰራዊት (ልክ) ከርሱ በቀር ማንም አያውቅም። እርሷም (የሰቀር እሳት) ለሰዎች መገሰጫ እንጅ ሌላ አይደለችም።"

ይህ ዛሬ በአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ ምፅዓት የሚመስለው እሳት አኼራ ላይ ከሚጠብቃቸው አንፃር ኢምንት ነው። ሩቅ ይመስላቸዋል ግን ቅርብ ነው። ወደ አላህ ተመልሰው ለአላህ ትእዛዝ እስካላደሩ ድረስ። እስኪ የዛን ቀን ሁኔታ በቁርኣን ገለፃ እናስተውለው፦

إِنَّهُمْ يَرَوْنَهُ بَعِيدًا
እነርሱ (ያንን ቀን) ሩቅ አድርገው ያዩታል።
وَنَرَاهُ قَرِيبًا
እኛም ቅርብ ኾኖ እናየዋለን፡፡
يَوْمَ تَكُونُ السَّمَاءُ كَالْمُهْلِ
ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትኾንበት ቀን
وَتَكُونُ الْجِبَالُ كَالْعِهْنِ
ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ነፋስ እንደሚያበረው) በሚኾኑበት ቀን
وَلَا يَسْأَلُ حَمِيمٌ حَمِيمًا
ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን፤ (መላሽ የለውም)
يُبَصَّرُونَهُمْ ۚ يَوَدُّ الْمُجْرِمُ لَوْ يَفْتَدِي مِنْ عَذَابِ يَوْمِئِذٍ بِبَنِيهِ
(ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡
وَصَاحِبَتِهِ وَأَخِيهِ
በሚስቱም በወንድሙም፡፡
وَفَصِيلَتِهِ الَّتِي تُؤْوِيهِ
በዚያችም በምታስጠጋው ጎሳው፡፡
وَمَن فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ثُمَّ يُنجِيهِ
በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያም ሊያድነው (ይመኛል)፡፡
كَلَّا ۖ إِنَّهَا لَظَىٰ
ይተው! እርሷ (እሳቲቱ) ለዟ ናት፡፡
نَزَّاعَةً لِّلشَّوَىٰ
የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትኾን፡፡

تَدْعُو مَنْ أَدْبَرَ وَتَوَلَّىٰ

(ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደእርሷ) ትጠራለች።

ሱረቱል መዓሪጅ ከአንቀፅ 6 –17

እነዚያ የአላህን ባሮች የሚፈትኑ አካላት ተውበት አድርገው ካልተመለሱ ምን እንደሚጠብቃቸው በሚከተለው የአላህ ቃል እናያለን፦
«إِنَّ الَّذِينَ فَتَنُوا الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ ثُمَّ لَمْ يَتُوبُوا فَلَهُمْ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَلَهُمْ عَذَابُ الْحَرِيقِ»
    البروج ١٠
"እነዚያ ምእምንንና ምእምናትን ያሰቃዩ ፣ ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አልላቸው። ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው፡፡"
     
ለማንኛውም እኛ ለእነዚህ አካላት የምንለው ሂዳያ የሚገባቸውን አላህ ሂዳያ ይስጣቸው። ሂዳያ የማይገባቸውን ደግሞ በጥበቡና ፍትሀዊነቱ የሚገባቸውን ይስጣቸው ነው

https://t.me/bahruteka


የሀጁሪና የተከታዮቹ ጉልህ ስህተቶች!
========>

↩️ « بعض ضلالات الحجوري العقدية والمنهجية والعلمية والأخلاقية»
↪️ የየህያ አል-ሀጁሪ የአቂዳ፣ የመንሃጅ፣ የእውቀት እና የስነ-ምግባር ከፊል ስህተቶች!

📢[ክፍል አራት]
   ➶➹➶➹➶➹

🎙لفضيلة الشيخ أبي طلحة أبي ذر بن حسن الولوي «حَفِظَهُ اللَّهُ»
🎙 በተከበሩ ሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን አቡ ጦልሃ አላህ ይጠብቃቸው!


        •┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•

ይ   ቀ   ጥ   ላ   ል
👇👇👇 ጆይን ብለው ይከታተሉ
https://t.me/+w-uAkEZwibVlNzM8

📱⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy


💊 ስለ ሩቃ ሰፋ ያለ ትምህርት
  💉¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯🔬

🏝 በዚህ አንገብጋቢ ትምህርት የሚከተሉት ነጥቦች ተዳሰዋል፦
🏝 أســبــاب صــرع الــجــن للإنـسـان
🏝 ጂን ሰዎችን የሚጥልበት ምክንያቶች

الــــرقــــيــــة الــــمــــشروعــــة
✅ ሸሪዓዊ የሩቅ ❴መንፈሳዊ❵ ህክምና


الــــرقــــيــــة الــــمــــحــــرمــــة
❌ እርም የሆነው መንፈሳዊ ህክምና


🚥
دخــول الجــني في بدن الإنســان
🚥 ጂን በሰዎች አካል ውስጥ ስለመግባቱ


🔍 وضــــــــرب الــــــــمــــــــصــــروع
🔎 [በጂን] የተጠቃን ሰው መደብደብ


🎙 للشيخ أبي طلحة أبي ذر بن حسن الولوي «حَفِظَهُ اللَّهُ»
🎙 በሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን አቡ ጦልሃ አላህ ይጠብቃቸው!



🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

---------------⫷⫸-----------------
🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
⫷⫸⫷~⫸⫷⫸⫷~⫸⫷⫸⫷~⫸


↪️ ለራሴ የገጠመኝ እና እውነተኛ ታሪክ

      * ክፍል አምስት

በተመሳሳይ ሁኔታ እዛው ሰፈር ከተወሰነ ጊዜ ቡሀላ መብረቅ በቤት ላይ ወረደ። እና በትንሹ ከዚህ ቤት ጋር በተያያዘ ያጋጠመኝ ነገር ልንገራችሁ። በሰዓቱ እኛ "ታርቤ ማዞሪያ መስጂድ" ቁርአን እየቀራን አንድ የሰፈር ልጅ ከኢሻ ሶላት በኋላ ደዉሎ ትንሹ ወንድሜ ከናንተ ጋር ነው ወይ ብሎ ለጓደኛችን ይጠይቀዋል። የተደወለበት ልጅ ለማናገር ውጪ ወጥቶ ከዳገት ወደታች አርጎ ሲያይ እሳቱ ይታያል። እኛም ከልጆቹ ጋር ወደዚያ ወረድን።

ቤቱ ጋር ስንደርስ ሰው በጣም ተሰብስቧል። ማታም ስለሆነ ሰው እሳት በማጥፋት እየተረባረበ ነው ስንል ነገሩ ግን እንደዛ አይደለም። በጣም አንገት የሚያስደፋ ነገር ብነግራችሁ እኛ ስንወርድ የዛ ቤት እናትና ሌላም የሰፈር እናቶች ለእሳቱ ሱጁድ ወርደው ነበር። የዛ ቤት እናት አጎንብሳ ተመልሻለሁኝ ጥፋቴ አውቄያለሁኝ ትላለች። እኛም  ኧረ አላህ ፍሩ ስንላቸው የዛ ቤት እናት ኧረ ተውኝ አለችን ሌሎችም በተመሳሳይ። ወንድሞቼ እንደነገሩኝ ለእሳቱ ሱጁድ ከወረዱ ሴቶች ጭራሽ የጁማአም ሰላትም ይሁን የኢድም ሰላት እንኳን የማይሰግዱ ነበሩ አሉኝ.... ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን። አላህ ﷻ በቁርአኑ እንዲህ ብሏል፦

{وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ} فصلت ٣٧

"ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደ ኾናችሁ (ለሌላ አትስገዱ)፡፡"

ተመልከቱ አላህ ከትላልቅ ተአምሮች ጠቅሶ ለነሱ አትስገዱ ይለናል። ከነሱ በታች ያለውማ ለሱ ሱጁድ ማድረግ የበለጠ የተከለከለ ነው። ከዛ ቀጥሎ ለነሱ ጌታ ለአላህ ብቻ ስገዱ አለ። ከአላህ ውጭ ላለ ነገር መስገድ ተዉሂድን ይንፃረራል። ነቢያች ﷺ በሀዲሳቸው፦

عن عبدالله بن أبي أوفى رضي الله عنه، قال: قال النبي ﷺ :" لو كُنتُ آمراً أحداً أن يسجُدَ لغيرِ اللَّهِ، لأمَرتُ المرأةَ أن تسجُدَ لزوجِها. والَّذي نَفسُ محمَّدٍ بيدِهِ، لا تؤدِّي المرأةُ حقَّ ربِّها حتَّى تؤدِّيَ حقَّ زوجِها "[رواه ابن ماجه (1853)، حسنه الألباني]

ከአብደላህ ቢን አቢ አውፋ እንደተዘገበው አላህ ኸይር ስራቸውን ይውደድላቸውና  ነብዩ ﷺ እንዲህ  አሉ፡- “ከአላህ ውጭ ላለ አካል እንዲሰገድ ባዝ ኖሮ ሴትን ለቧልዋ እንድትሰግድ አዛት ነበር።  የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው አላህ እምላለሁኝ አንዲት ሴት የአላህን መብት አታሟላም  የባልዋን መብት እስከምታሟላ ድረስ።)"

ከሀዲሱ የምንረዳው፦ አንድ ሰው ከአላህ ውጭ ላለ ነገር መስገድ እንደሌለበት ነው። ይህ ደግሞ ተዉሂድን ይፃረናል። እዳሳለፍነው ይህ እሳት አላህ እንደላከው አይተናል ስለዚህ የእሳቱ ጌታ ብቻ ሊሰገድለት የተገባ ነው። በጣም ሚያሳዝነው የፍጡሮች ሁሉ ጌታ የሆነው አላህ የሱ የማይሰግዱ እናቶች ለዚህ እሳት ሲሰግዱ ያሳዝናል። አለህ ቀልበቸው በተዉሂድ ያርጥብላቸው።

ቤቱ ሲነድ ምንም ዓይነት እቃ አላወጡም። እኛ ከመጣን በኋላ እናጥፋው ስንላቸው የመብረቅ እሳት እኮነው አሉን። ጆፎሮ ላይ የተሰባሰቡ ወጣቶች ነበሩ። እኔ እኛ ወጣት ነን ተባብረን እናጥፋው አልኳቸው። ከነሱ  መካከል አንድ ልጅ የመብረቅ እሳት በውሀ ለማጥፋት ትሞክራለህ ወይ!!? ኧረ ተወን አለኝ። ትንሽ ወሃ ለመድፋት ስንሞክር ሰዉ ሁሉ መጮህ ጀመረ። ሊያስጨርሱን ውሀ ይደፋሉ  በህይወታችን ሰምተን የማናቀው ነገር እያረጉ ነው ብለው ያመጣነው ጀሪካን ወሰዱብን። አንድ አብሮን የሚቀራ ጓደኛችን አሁንም ተስፋ አልቆርጥም ብሎ ተደብቆ ውሃ ማምጣት ጀመረ። ያለው ሰው ብዙ ስለነበረ አሁንም ወዲያውኑ ላይ ነጥቀው ወሰዱበት።

በጣም የሚያሳዝንና የሚያስለቅሰው ነገር የዛ ቤት እናት አንድ ጥጃ ከነህይወቱ ለሱ ፊዳ እንዲሆን ካልጨመርኩኝ አለች። በዛ ጊዜ የሰፈር ልጆችም ተባብረውን ጊደሩ ወስደንባቸው ጓደኛችን ጋር ወስደን አሰርነው። እቺ ጥጃ ምን አጥፍታ ነው በዚህ እሳት ከነ ህይወትዋ ምትጣለዉ?!! ላኢላሀ ኢለላህ!

በዚህ መልኩ ከእነሱም እየታገልን እያለን ቻይና ጋር የሚጠብቁ ልዩ ኃይሎች አመጡብን አላህ ይምራቸው። እነዚህ ልዩ ኃይሎች ማን ነው በንብረቱ የፈለገ ነገር  ለማድረግ የሚከለከለው ብለው ሲገቡ እኛ ሾልከን አመልጥናቸው። እኛ ከሄድን በኋላ ያ ውሀ ተደብቆ ሲያመጣልን የነበረው ጓደኛችን እዛው ነበር። ቤተሰብም ስለሆነ አስፈራርተውት ሰው ወደ ቤቱ ከሄደ በኃላ ቤተሰብም እቤት ከገቡ በኋላ አጠገቡ የነበረው ቆርቆሮ ቤት ክፈፉ ጫፍ እሳት ተያይዞበት  ውሃ ደፋሁበት አለን።

ከዛ በኋላ በማግስቱ ትላንት እንዳልመጣን ሰው ሆነን ከጓደኛችን ጋር ወረድን። ለዚህ ጋደኛችን ጓደኞቼ ስራ እንጀመር እንጨት እኛ እንፍለጥ እያሉ ነው በላቸው አልነው። ከአዲስ አበባ የመጡም ሰዎችም ነበሩና ይህም ሲሰሙ በጣም ተገርመው እንዴት ነው  ስራ ምንጀምረው!! (አዋእ) ጠንቋዩ መጥተው ሳይጨርስ አሉ። ከዛ እኔ ወደ መርከዝ ተመለስኩኝ። ወንድሞች ደውዪ ስጠይቃቸው ወደ (አዋእ) ጋር ሄደው አመጡትና (እንደነገርኳቹ ከመሄድ በፊት የሚሰራ ስራ ሁሉ ሰርተው ነው የሄዱት) እሱ ከመጣ በሀኃላ (አላህ ይግደለው) ስሙ ጕይታኩየ ይባላል። ጕይታ ማለት በጉራጌኛ ጌታ ማለት ነው። ከዛ መጥቶ እንዲህ አለ «በሆነ ቦታ እኔ ስልክ ጠፍቶኝ ከዛ ሲፈተሽ ታጣ። ከተወሰኑ ደቂቃ ቦሀላ ቤቴ ሄጄ ያን ስልክ የሰረቀኝ ሰውዪ የገባበት ቤቱ እዲቃጠል አድርጌ ቤቱ  ተቃጠለ አለ» ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለሂ ራጂኡን። በዚህ ንግግሩ የፈልገበት ይሄም ቤት ያቃጠልኩት እኔ ነኝ ለማለት ፈልጎ ነው። ሰውየው ክርስቲያን እኮ ነው በጣም ሚያሳዝነው ሙስሊም ሰዎች እንዲህ ሲል ማመናቸው። እስልምና የበላይ አርጓቸው ለሱ መዋረደቸው ነው። ከዛ እነዛ የተቃጠሉ እቃዎች ባጠቃላይ ንገሩኝ የኔ ናቸው ብሎ የተቃጠለ እቃ  ባጠቃላይ እቤት ውስጥ የነበሩ ፋስ፣ መቆፈሪያ በሙሉ ሳይቀር ተነግሮት ገምቶ ብሩ ስጡኝ ብሎ ተሰጠው።

የተወሰኑ የጎረቤት እንሰቶች ጭስ  ወጥቶባቸው ትንሽ ደርቀው ነበር። የነሱም ብር ስጡኝ ብሎ የእንሰቱ ባለቤት የነሱም ብር ሰጠው። ብሩ ከተሰጠው በኋላ ስራ ጀምሩ አላቸው። እነሱም በደስታ ተጨረሰ ብለው ወደ ስራቸው ገቡ። የሚያደርጉት ከላይ የጠቀስኩት ማለት ነው።

እነዚህ ሰዎች እደምሳሌ ጠቀስኩላቹ እንጂ በየግዜው መብረቅ በተለያየ ነገር ላይ ይወርዳል። ያ የወረደበት ሰው እነዚህ ሰዎች የሰሩትን የሽርክ ስራ ነው የሚሰሩት። ስለዚህ ወንድሞቼ የኔ አባትና እናት ተዉሒድ ያውቃሉ። ይህን ነገር አይሰሩም ነበር ልትሉ ትችላላቹ። ነገር ግን እነሱ ይህ ስራ አልሰራም ቢሉ እንኳን የሰፈር ሰው አይተዋቸውም ማለትም እንዲህ ካላደረጋቹህ እንዲህ ትሆናላቹ በማለት ያስገድዷቸዋል። "ሰው ያሸንፋል" የሚባል አባባል አለ። ስለዚህ ቤተሰቦቻችንን በማስተማር ላይ እንጠናከር። እነሞር ላይ ብዙ አይነት የሚሰሩ ሽርኮች አሉ።

ወንድም፦ ሰዒድ ሙሰፋ አህመድ

ክፍል ስድስት ይቀጥላል

https://t.me/Gusbajisunna
https://t.me/Gusbajisunna


🛏 ከተልቂን እስከ ጀናዛን እስከ መቅበር ድረስ ያለው ትክክለኛ ሒደት እና በውስጡ የሚሰሩ ቢድዓዎችንና ሙንከሮችን፣ እንዲሁም ለቅሶን እና ሌሎችም አሳሳቢ ነጥቦችንና ብይኖቻቸውን በመረጃ የምትዳስስ አንገብጋቢ ሪሳላ!
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼

📖 اسم الكتاب:- «سبعون سؤالا في أحكام الجنائز»
📖 የኪታቡ ስም፦
«70 ጥያቄዎች በጀናዛ ህግጋቶች ዙሪያ»
🏝 ⇣⇣⇣•••⇣⇣⇣ 
📢[ክፍል አስራ ሁለት]
   ➶➹➶➹➶➹

📄ሪሳላዋን በ𝕡𝕕𝕗 ለማግኘት
➘➷➴➘➷
t.me/AbuYehyaAselefy/11908

📝 تأليف:- فضيلة الشيخ أبي عبد الله محمد بن صالح العثيمين - رحمه الله -
🎙
በኡስታዝ አቡ አነስ [አቡ ጀዕፈር] ሙሐመድ አሚን አላህ ይጠብቀውና

🏠ቦታ፦ ሸዋሮቢት 🕌 በሰለፍዮች ፉርቃን መስጂድ የተሰጠ ወሳኝ ትምህርት
        •┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•

📱⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy




አላህ 👉 የሻውን ሰሪ ብቻውን ቀሪ ነው።
➩➩➩➩➩♻️

የአመታት ድካም በደቂቃ ውድመት

👈 ‏قبل ٢٤ ساعة كانت هذه المنطقه هي أغلى عقارات العالم لوس أنجلوس والان صارت رماد ف سبحان مغير الاحوال
👉 ከ24 ሰአት በፊት ይህ አካባቢ በአለማችን ውዱ ሪልስቴት ሎሳንጀለስ ነበር አሁን ደግሞ አመድ ሆኗል አላህ ነገሮችን እንደፈለገ ይቀያይራቸዋል መውደማቸው ባያስደስተኝም ለጋዛ ሚስኪኖች የጀሀነም በር ይከፈታል ሲሉን አላህ ጀሀነም በር ከቤታቸው ከፍቶ አቅም አጣን አስብሏቸዋል።
------------------------

📌  በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ መኖሪያ ቤቶችና ሌሎች ሕንፃዎች ተቃጥለዋል።

📌 በግዙፉ የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 10 ከፍ ብሏል።

📌 በእሳት አደጋው የደረሰው የኢኮኖሚ ጉዳት ወደ 150 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱ ተነግሯል።

🌐 አል ዐይን ኒውስ

قال‏ العلامة ربيع بن هادي المدخلي حَفِظَهُ اللَّهُ تَعَالَىٰ :
"هذه أمريكا التي عندها الأساطيل الجوية والبحرية والقوات والله لا قيمة لها عند الله تبارك وتعالى والله النعمة العظمى عندنا نحن ؛نعمة الإيمان، نعمة التوحيد ،نعمة المنهج الصحيح الواضح"
    📚 الوصايا المنهجية ص104.

https://t.me/AbuImranAselefy/9611


Репост из: ሙሀመድ አል―ወልቂጢይ
👌 አላህን መነጠልህን የተውሒድ ኪታቦችን በመቅራት እና ተግባር ላይ በማዋል አጠናክር። መልእክተኛውን መከተልህን ደግሞ የመንሀጅ ኪታብ በመቅራት እና ተግባር ላይ በማዋል አጠናክር።


የተውሂድ እና ሽርክ ዳዕዋ
በሽርክ ከምትታወቀው ሀገር
ከጉራጌ  ዞኗ ቃጥባሬ ምድር
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

🏝 በለቅሶ የታጀበ ለሙዎሂዶች እርግጠኝነትን የሚጨምር ታላቅ የተውሂድ ዳዕዋ
=> በሙሐደራው፦
የቀብር አምልኮ በቃጥባሬ
የቃጥባሬ ሸይኾች ፍጡር ናቸው አይመለኩም
➩ ታጥበው ተከፍነው ተሰግዶባቸው የተቀበሩ ፍጡር ናቸው።
የሸይኾቹ ቀብር እንደ ካዕባ ተገንብቶበት የካዕባ ልብስ ለብሶ ጠዋፍ ይደረግበታል።
ስለት ይሳሉበታል።
➪ ሰዎች ችግራቸውን በእንብርክካቸው ሄደው ለቀብር ይነግራሉ መፍትሄ ይጠብቃሉ።
እነዚህ ተግባሮች ኩፍር ናቸው ተውበት ያስፈልጋቸዋል
የቃጥባሬ አካባቢ ሙስሊሞች ይህን ማውገዝና ማስቆም አለባው።
በዚህ ላይ የሚሳተፉና የሚመሩ ሞት ሳይቀድማቸው መመለስ አለባቸው
ይህ ተግባር የነብዩን ዲን መውጋት ነው።
➩ ይህ ተግባር ሸሪዓን ማጥፋት ነብዩና ሶሓቦች ዋጋ የከፈሉለትን እስልምና ማጥፋት ነው።
በየቦታው ያሉ የሽርክ ማእበሎች አላህ ያድርቃቸው። እኛን አላህ ሰበብ ያድርገን።

👉 ይህ ዳዕዋ በትክክለኛ አገላለጽ በትክክለኛ ቦታ ተገቢ በሆነ ቦታ ቀርቧል። ይህ ዳዕዋ ለቃጥባሬ አካባቢ ህዝብ በታላቅ ስፒከር ሁልጊዜም ሊያዳምጡት ይገባል።

🎙 آلأُسْتَاذ بَحْرُو تَكَا أَبُو عٌبَيْدَة «حَفِظَهُ اللَّهُ»
🎙 በኡስታዝ ባህሩ ተካ አቡ ዑበይዳህ አላህ ይጠብቀው!


🗓 በ25/3/2015

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

---------------⫷⫸-----------------
🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
⫷⫸⫷~⫸⫷⫸⫷~⫸⫷⫸⫷~⫸


🔷 ትዝብት ነው ወገን!

ብዙ ጊዜ በሶሻል ሚዲያ ስለ ሶላት፣ ስለጋብቻ እና ፍች፣ ስለፆም፣ ስለሀጅ፣ ስለዘካ ወዘተ… ፅሁፍም ይሁን ድምፅ ሲለቀቅ የላይክ ምልክት 👍 ወይም የጭብጨባ 👏 አልያም ምርጥነው ለማለት የምንጠቀምበትን ምልክት👌 የአድናቆት አይነት በሰፊው እናገኛለን። ከዛም ባለፈ በኮሜንት ማስፈሪያ ቦታም ማሻ አላህ፣ ጥሩ ነው፣ የመሳሰሉ የአክብሮት እና የድጋፍ ቃላቶችን ማግኘት የተለመደ ነው።

ነገር ግን የሚለቀቀው ፅሁፍም ይሁን ድምፅ ተውሂድ የሚያስተምር፣ የሰለፊይ ኡለማኦችን ታሪክ ሚተርክ ከሆነ ወይም ስለ ሽርክ፣ ስለ ሙሽሪኮች፣ የሽርክ ቦታዎች ሚያመልኩዋቸውን ቅራቅንቦ  የሚከለክል የሚገስፅ ከሆነ አግርሞት በሚጭር መልኩ ተዛላፊው፣ ተቃዋሚው ይበዛል ጭቅጨቅ በሽሽ ነው። ልክ እደዛው ስለ ቢድአ እና ሙብተዲእም ከሆነ በየኮመንት መስጪያው ሙሪዶች የስድብ ውርጅብኝ ይደቀድቃሉ ወይም እነዚህን ምልክት በመጠቀም ተቃውሟቸውን ይገልፃሉ 🔥👎ያሰላም!!! 

አልያም ያች የፈረደባትን ወሃብያ፣ የአከሌ ተከታይ፣ አትሳደብ ወዘተ… ይላሉ።

"أَلَا سَآءَ مَايَحْكُمُونَ"

ንቁ የሚፈርዱት የሆነው ነገር ምንኛ ከፋ!

እውነት ሲነገረን ጣፈጠም መረረ መቀበል የኛ ሃላፍትና ነው። ከመቀበል አልፎ መካሪዎቻችንን መዝለፍ ትልቅ የሆነ ነፍስያን መበደል ነው። ስለ ሰላት እና መሰል ጉዳዮች ሲነገርህ ደስ እንደሚልህ/ ሽ ሁላ ስለ ተውሂድ እና ሽርክም ሲወራ ደስ ይበልህ /ሽ። ስለ ቢድአ እና ሙብተዲእም ሲነገር አያንገሸግሽህ/ ሽ። ከአላህ ያመጣልንን ሁሉንም ወደን እንቀበል። ያዘዘንን በቻልነው እንተግብር። የከለከለንን በሙሉ እንራቅ። አንዱን ጥሎ ሌላውን አንጠልጥሎ አይጠቅመንም።

https://t.me/sunnatewhid




የጁመዓ ኹጥባ ክፍል ❪165❫
      ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
↩️ خُطْبَةُ الْـجُمُعَةِ
↪️ የጁመዓ ኹጥባ


📍ርዕስ፦➘
↪️ «የተውሒድ አንገብጋቢነት እና የሽርክ አስከፊነት» በሚል ርዕስ የተደረገ እጅግ ወሳኝ የሆነ ኹጥባ!

🎙الأستاذ الفاضل الداعي إلى الله أبو أنس [أبو جعفر] محمد أمين السلفي «حفظه الله»
🎙በውዱ ኡስታዛችን ኡስታዝ አቡ አነስ [አቡ ጀዕፈር] ሙሐመድ አሚን አላህ ይጠብቀውና


🕌 በሸዋሮቢት ከተማ የሰለፍዮች በሆነው ፉርቃን መስጂድ የተደረገ ኹጥባ!

          •┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
||~ ሼር አድርጉት!

📱👇👇👇👇
https://t.me/Abujaefermuhamedamin

https://t.me/Abujaefermuhamedamin


👆👆👆
🔈
#አላህ በመሬት መንቀጥቀጥ ባሮቹን ያስፈራራቸዋል።

🔶
በአዲስ አበባ በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል የተደረገ ሙሐደራ።

🎙በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)

📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ
👇👇👇
🌐 https://t.me/shakirsultan


↪️ የሀዲያን ህዝብ የማክፈር ዘመቺያ በተለያዩ ዘመናት!

ክፍል ሁለት

ክፍል አንድን ለማግኘት ይህን ይጫኑ
https://t.me/sunnatewhid/222

🔷 ጦረኛ በማዝመት ሰይፍ በመምዘዝ የማክፈር ሂደት። ይህኛው ሂደት የተጀመረው የሠለሞናዊው ስርወ-መንግስት ወደ ስልጣን ከተመለሰ ወዲህ ነበር። ለጉዳዩም ትኩረት በመስጠት ክብረ-ነገስት በሚሰኘው የክርስቲያኑ መንግስት መፅሐፍ ውስጥ የክርስትያኑ መንግስት የሀዲያ ሙስሊሞችን ዘመናትን የተሻገሩ ጠላቶች ብሎ ከሌሎች ሙስሊሞችም ጋር ጨምሮ አስፍሯቸዋል። በጠላትነት ከመፈረጅም አልፎ ወደ ከፋ ጦርነት የተሻገረው ንጉስ አምደ-ፂዮን ስልጣኑን ከተቆጣጠረበት 1314-1344 E,c ጀምሮ ነበር። ከሱበፊት የነበሩ ነገስታት በውስጥ ለውስጥ የስልጣን ሽኩቻላይ ስለነበሩ በሀዲያው ሱልጣኔት ለመዝመት አላስቻላቸውም ነበር አምደ-ፂዮን ከነገሰ ወዲህ ግን የውስጥ ችግራቸውን ለግዜው ትቶት ቀጥታ ወደ ሀዲያ ሱልጣኔ ጦር አዘዘ የመጀመሪያውንም ዘመቻ 1316-1317 ነበር። በዚህ ጦርነት በሙስሊሞች ያደረሰው በደል በጥቂቱ ለመዘርዘር፦

* ብዙዎችን ጨፈጨፈ። ከዚያም ሲደክመው መሪያቸውን ጨምሮ ሽማግሌ፣ ህፃናት፣ ሴት በምርኮ ወደ ግዛቱ አጓጋዘ። በዚህ ጦርነት ክርስትያኖቹ ቢያሸንፋም ሙስሊሞችን ሀይማኖታቸውን ማስቀየር አልቻሉም። በግዜው የሱልጣኔቱ መሪ መስጅድ አታፍርስብን ሀይማኖታችንን አትንካ ግብር እንከፍላለን ብሎ ለመዋጋት አቅም ስላልነበረው ጥያቄ አቀረበለት በግብሩ አፄው ተስማማ። በተጨማሪም በየአመቱ አንዲት ውብ የሆነች ኮረዳ ሴት ከተከበረ ቤተሰብ ተመርጣ ለንጉሱ እንድትገበር አስገደዳቸው። በየአመቱ ከሀገሩ ቆንጆ የባለ-አባት ሴት ልጅ መርጠው፣ አጥበው ሳትሞት ይገንዟትና ሰላተል ጀናዛ ሰግደውባት ለንጉሱ ይገብሯት ነበር። እዛ ከሄደች መክፈሯ ስለማይቀር መክፈሯን እንደ ሞት በመቁጠር እሄን ያደርጉ ነበር። በዛን ግዜ የነበሩ የሱልጣኔቱ መሪዎችም ይሁን ተመሪው ሸሪአዊ እውቀት በጥልቅ አያውቁም ነበርና ለዚህ ነው እንደዛ ያደረጓት ይባላል። ከግብሩም በተጨማሪ ፈረስ ያለኮርቻው እንዲጋልቡ፣ ሰይፍ በፍፁም እንዳይዙም ማእቀብ ጣለባቸው።

🔷 ከሙስሊሙ መህበረሰብ ለነሱ ታመኝ መሪ ማስቀመጥ። በአፄ ዘርዓ-ያዕቆብ ግዜ ገራድ-ማኢቆ ሙሀመድ ለንጉሱ ላለመገበር ሙስሊሙን ከክርስቲያን ንጉስ ለማስጠበቅ ከአዳል ወንድም ሱልጣኔቶች ጋር ተስማምቶ ዝግጅት ላይ ነበር። ነገር ግን አፄው በአካል ግዛቱ ላይ ባይኖሩም ከሙስሊሞች በኩል ለአፄው ታማኝ ቅጥረኛ ነበረው። የሀዲያ ሌላኛው ጋራድ (መሪ) ይህንን እቅዱ ቀድሞ ለአፄ ዘረዓ-ያዕቆብ በማጋለጥና ከጎኑ በመሆን  ሙስሊም ወንድሙን ተዋጋው። አፄውም ለዚህ ተግባሩ ማመስገኛ ብዙ ስጦታ እና ጌጦችን ለገሱት። በዚህም ግዜ የሀዲያው ሙስሊሙ ሱልጣኔት በክፋኛ በወንድሙ እና በጠላትቱ ተዳከመ። የክርስትያኑ መንግስትም ከራሱ ግዛት ሹማምንት መርጦ በሙስሊሙ ግዛት አሰፈራቸው ህዝቡም በግዳጅ ለአፄው እጅ ነሳ። ሀይማኖቱን ለማስጠበቅ ሲል መገበሩንም ቀጠለ።

ክፍል ሶስት ይቀጥላል

https://t.me/sunnatewhid


🔸 ሙሀደራ #ቁጥር 014

🔊 “አደራቹን እውቀት በመማር ላይ!!”

🎙በሸይኽ አቡ ዐብዲል ወዱድ ሙባረክ ሁሰይን አል-ወልቂጢይ (ሐፊዘሁላህ)

# መስጂደል ፉሩቅ ሀሮ

https://t.me/shikmubarek
https://t.me/shikmubarek


👉ለሚስትህ የሚከሉትን ሁንላት!
     ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

1ኛ ፍቅርህን አክብሮትህን ለሷ ያለህን ቦታ ምኞትህን ወዘተ በተግባርም በቃልህም ግለፅላት!

2ኛ ከየትኛውም አካል የበለጠና የተሻለ አቀራረብ ቅረባት፤ የደስታዋም ሆነ የሀዘና የመጀመሪያ ተካፋይ ሁን!

3ኛ በአንተ እርግጠኛ እንድትሆን አድርጋት፣ ሁሌም የኔ ነው፤ ከጎኔ ነው የሚል ስሜት እንድሰማት ማድረግ አለብህ!

4ኛ ግልፅ ሁንላት የምታስበውን፣ የምታደርገውን በቃ የትኛውንም እንቅስቃሴህን ግልፅ ሁነህ አሳውቃት በአንተ እርግጠኛ ትሆናለችና

5ኛ ቃል የምትገባላትን ነገር በተግባር አሳያት ሴቶች ወሬው ከተግባሩ የሚቀድም ወንድ አይወዱም። ስለዚህ የምትችለውን ቃል ገብተህ ፈፅመህ አሳያት!

6ኛ ቋሚ የሆነ ሁኔታ ይኑርህ ማለትም ስትፈልግ አትዝጋት ስትፈልግ አትቅረባት፣ የእውነት ከፈለካት  ቋሚ ደስ የሚል ባህሪ ይኑርህ፤ ያኔ በቀላሉ መግባባት ትችላላችሁ!

7ኛ ጨዋ ሁንላት በዙሪያዋ ያሉ ሰዎችን አክብርላት ውደድላት፤ የኔ ባል ከሁሉም የበለጠ ምስጉን ጨዋ እና ክቡር ነው በማለት እስከምታምን ድረስ ተስተካከልላት!

8ኛ ትእግስተኛ ሁንላት ስትቆጣ አትቆጣ ወንድ ነኝ አትነጫነጭ የሚል ሁኔታ አይኑርህ ተረዳት፤ በተለይ በወር አበባ በእርግዝና እና በህመም ወቅቶች የተለየ ባህሪ ብታሳይህም ግን አንተ ታጋሽ ሆነህ ስሜቷን ተገንዘብላት ሲሻላት በጣም ታከብርሃለችና

9ኛ ነገሮችን ተቆጣጣሪ ሁን፤ ዝርክርክነት መለያህ እንዳይሆን ቤትህን ሚስትህን ገንዘብህን ጊዜህን እውቀትህን ወዘተ በአግባቡ ተቆጣጠር። ባሌ ካለ ምንም የሚዛባ ነገር አይኖርም እስከምትል ተቆጣጣሪ ሁን

10ኛ አክብራት ማለትም ሀሳቧን ስትነግርህ አክብርላት ሀሳቧ ስህተት እንኳን ቢሆን አዳምጣት፣ አትሳለቅባት፤ አትሳቅባት፤ እንደውም አበረታታት በሀሳቧ እንዲትሸማቀቅ ሳይሆን እንድትኮራ አድርጋት። ለሳቧን ማክበር እሷን ማክበር ነው። ሀሳቧን መንቀፍ እሷን መንቀፍ ነው። ስህተት ከሆነም በአግባቡ አስረዲተህ ግን አደናንቀህ አለፋት!

11ኛ ማንነቷን ተቀበልላት ደካማ ጎኖቿን መነሻ አድርገህ የትችት አውድማ አታድርጋት ክፍተቶቿን እንዲታስተካክል አግዛት እንጂ አታዋርዳት!

12ኛ ቆንጆ እንደሆነች ንገራት ከእርሷ ውጭ ማንንም እንደማትፈልግ ንገራት አሳያት፤ የምትተማመንብህና የምትወዳት መሆኖኑን እስከምታምን ተንከባከባት!

13ኛ ደስተኛ አድርጋት ባላችሁ ነገር ደስተኛ ሁኑ። ብዙ ሀብት ግደታ አይደለም ለምሳሌ ስጦታ በመግዛት፣ 5 ብር ከረሜላም እንኳ ቢሆን ዋናው አንተ እሷን ማሰብህ ነው።

14ኛ ወሬዋን ጆሮ ሰጥተህ እንድትሰማት ትፈልጋለች። ስለዚህ ልታወራህ ስትል አፍ አፏን አትበላት ተዋት ታውራህ! ልታስቅህ ከፈለገች ባያስቅህም ሳቅላት። ለሳቧን አታቋርጣት አታስደንግጣት። ጊዜ ሰጠህ ስታዳምጣት ትልቅ ቦታ እንደሰጠሃት ትረዳሃለች!

15ኛ በአጠቃላይ ለሚስትህ ጥሩ ባል መሆንህ እሷም ጥሩ ሚስት ትሆንልሃለችና ትኩረት ስጥ! ከላይ የተጠቀሱልህን በመተግበር ስኬታማ የትዳር ህይወት ኑሩ!!!

⚙ ከተወሰነ ማስተካከያ ጋር የቀረበ
https://t.me/AbuImranAselefy/9605

▵▮▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▯▴
⚙ 📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

---------------⫷⫸-----------------
🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
⫷⫸⫷~⫸⫷⫸⫷~⫸⫷⫸⫷~⫸

Показано 20 последних публикаций.