◉ የኔ የቂያማ እለት🔥
ህይወትን አገኘን ከአለማት ፈጣሪ
ሞትም ተዘጋጀ እንዳንሆን ዘውታሪ
እኛ ተመላሽ ነን ወደ ጀሊላችን
ተጠያቂ ልንሆን በዱንያ ስራችን
እዚህ በሰራነው በያንዳንዱ ስራ
ተጠያቂዎች ነን ያኔ በየተራ
ረቂብ እና አቲድ ስራን መዝግበዋል
ከመጥፎም ከጥሩም ሁሉንም ፅፈዋል
ጨለማን ሸፍነን ከሰራነው ወንጀል
ማንም አይኖርም የሚያድነን ሀይል
ከጀሊሉ ውጪ ስልጣን ያለው የለም
ለቅሶ ላይ ነው ያኔ ሁሉም በኒ አደም
ዋይታውን ያሰማል እርዳታን ፍለጋ
ልቡ ፍርሃት ላይ ናት ሲመሽም ሲነጋ
ማንም አይረዳውም ከአላህ በስተቀር
ምንዳውን ያገኛል ለፈፀመው ተግባር
አላህ የወደደው አላህ ያዘነለት
መኖሪያው ይሆናል ከትልቋ ጀነት
አላህ ያደርገዋል ከአርሽ ጥላ ስር
ላባችን ሲሞላን ፀሀይ ቀርባ ስንዝር
አላህን ያስቆጣ አላህ ያዘነበት
ዘውታሪ ይሆናል ከጀሀነም እሳት
ያኔ አይባልም ህያው አሊያም ሙት
ሲሰቃይ ይኖራል በእሳት እንፋሎት
አላህ ይዘንልን አብዝቶ ይውደደን
በጀነተል ፊርዶስ ዘውታሪ ያድርገን!!🤲
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik
ህይወትን አገኘን ከአለማት ፈጣሪ
ሞትም ተዘጋጀ እንዳንሆን ዘውታሪ
እኛ ተመላሽ ነን ወደ ጀሊላችን
ተጠያቂ ልንሆን በዱንያ ስራችን
እዚህ በሰራነው በያንዳንዱ ስራ
ተጠያቂዎች ነን ያኔ በየተራ
ረቂብ እና አቲድ ስራን መዝግበዋል
ከመጥፎም ከጥሩም ሁሉንም ፅፈዋል
ጨለማን ሸፍነን ከሰራነው ወንጀል
ማንም አይኖርም የሚያድነን ሀይል
ከጀሊሉ ውጪ ስልጣን ያለው የለም
ለቅሶ ላይ ነው ያኔ ሁሉም በኒ አደም
ዋይታውን ያሰማል እርዳታን ፍለጋ
ልቡ ፍርሃት ላይ ናት ሲመሽም ሲነጋ
ማንም አይረዳውም ከአላህ በስተቀር
ምንዳውን ያገኛል ለፈፀመው ተግባር
አላህ የወደደው አላህ ያዘነለት
መኖሪያው ይሆናል ከትልቋ ጀነት
አላህ ያደርገዋል ከአርሽ ጥላ ስር
ላባችን ሲሞላን ፀሀይ ቀርባ ስንዝር
አላህን ያስቆጣ አላህ ያዘነበት
ዘውታሪ ይሆናል ከጀሀነም እሳት
ያኔ አይባልም ህያው አሊያም ሙት
ሲሰቃይ ይኖራል በእሳት እንፋሎት
አላህ ይዘንልን አብዝቶ ይውደደን
በጀነተል ፊርዶስ ዘውታሪ ያድርገን!!🤲
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik