በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
👉 ከቁርኣን፣
👉ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
👉 ከታማኝ ዑለማዎችና
👉ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።
ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ  @Abu_Sibewe ላይ አስፍሩት።
ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ።
ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


አስቸኳይ መልዕክት  ሼር

ከታች ያስያዝኩት ፈቶ  አንድ እህቴ ትላንት  ምሽት ትራንስፖርት ላይ  ስልክዋ በሌቦች ተቀምታ(ተሰርቃ) ነበር  ስልኩ እንዴት እንደከፈቱት ባይታወቅም በስልክዋ ያሉ ቁጥሮች(contact) ላይ ይህ መልዕክት በመላክ አለኝ ላላቸው ሰው የራሳቸው  አካውንት  እየላኩ  ብር  እያስላኩ ነበር ።
ባጋጣሚ ይህ መልዕክት እቤት ተላከ ሌሎች ጋ ደውላ ስታረጋግጥ እንደተላከ ተነገራት ሲም ካርዱ ተደውሎ ተዘጋ አሉ ግን ከ30 ደቂቃ ቦዃላ ዳግም ሚሴጅ መላክ ተጀመረ !! ዳግም ወደ ቴሌ ቢደወልም ስለ ተደጋገመ መዝጋት አንችልም አሉ!!
ተዘጋ የተባለው ሲም ካርድ ማን እንዳስከፈተው አላህ ይወቀው ??
ይህ የሌባ የስርቆት በአሁን ሰዐት የተጀመረ ሙድ እደሆነ ስሠማ ሶሞኑም እንዲ የተደረገ ሰው እንዳለ ሲነገረኝ ይህ መልዕክት ለሁሉም መሰራጨት አለበት
ስልክ መጥፋቱ አንሶ ገና ሌላ እዳ ውስጥ መግባት በጣም ከባድ ነውና
በጣም ጥንቃቄ ያስፈልጋል።

🌿ማጠቃሊያ🌿

1ኛ በተቻለን መጠን ጥንቃቄ እናድርግ ትራንስፖርት ላይ ሆነን ስልክ ስናወራ(ስንጎረጉር) የመኪና መስኮት ዝግ መሆኑን እናረጋግጥ።

2ኛ ምናውቀው ሰው ቢሆን እንኳን እንዲ ብር ላክልኝ የሚል መልዕክት ከደረሰን ደውለን እሱ መሆኑን ሳናረጋግጥ አንላክ የራሱም አካውንት ቢልክልን እንኳን

3ኛ ምን አልባት አላህ አይበለውና ስልካችን ቢሰረቅ ተሎ ለማዘጋት እንሞክር

4ኛ ስልካችን ለማዘጋት ቴሌዎች ሚጠይቁት ሲም ካርዱ ያወጣው
ስም ከነ አያት
የወጣበት አ/ምህረት
የወጣበት ቦታ
ስልኩ ሲወጣ ሌላ የተመዘገበው ስል ቁጥር
እናም ብዙ ግዜ ምንደዋወልባቸው 3/5 ስልኮች ስለ ሚጠይቁ በቃላችን  መያዝና እነዚን ማወቅ አልያም የስልካችን puk ኮድ ማወቅ አለብን።

ይህ መልዕክት ለሁሉም እንዲዳረስ ለሁሉም ሼር እንዳድርገው
ከfb የተገኘ
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


👉 በምን ሁኔታ ላይ ይሆን ይችን አለም የምንሰናበታት⁉️

ጌታችን الله ሆይ:-

👉መጨረሻችንን አሳምርልን በእስልምና በሱና ላይ ግደለን ከደጋጎች ጋር ቀስቅሰን‼

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


★﷽★

#ፋኢዳ


اختصام الجنة والنار


የጀነትና የጀሐነም ክርክር


 

الشيخ محمد آدم الإتيوبي



ሸይኽ ሙሀመድ ኣደም ኢትዮጵያዊ
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


👉🛑አይ አህባሽ እንደዚህም ቀዋዉሰዋል ههههههههه

ምግብ የማይመርጡ አላለም………

👉⭕️ቀጥሎ ያስፈገገኝ ስንኝ ተጋሩትማ:-

ከመስጊድ አዉጧቸዉ ደብድቡ በቦክስ
እንሙት ለዲናችን እንፈራከስ
ሁሉም ለበረካዉ በጥፊ አቅመስ

ههههههههه

☞ለበረካዉ ጥፊ እንዳትቀምሱ እየተጠነቀቃችሁ ኋላ አልተነገረኝም አልሰማሁም አይሰራም።


ስም ማጥፋት የምቀኞች መዳረሻ
     ትልቅ መንገዳቸው ነው። ."
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


ለአሏህ መንገር #ትተን ለሰው ነገርንና ...
ገር የነበረው ተመልሶ ጠና!!

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


Репост из: በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك
👉አንዳንድ ገጠመኞች አሉ
ልክ እንደ እርሳስ ቀለም ጠርገን እንዳልነበሩ ምናደርጋቸው።
አንዳንድ ገጠመኞች ደግሞ አሉ

👉ልክ እንደ እርሳስ ቀለም ጠራርገው እንዳልነበርን ሚያደርጉን።

አላህ መልካም ለሆነው ይግጠመን
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


🥬ምላስን መጠበቅ🥬


ምላስህ ነጃ የመውጫህ ሰበብ ነው ወይም ምላስህ የመክሰሪያህ ሰበብ ነው ይለናል ታላቁ አሊም ሸህ አቢ ሙአዝ ሁሴን አልሓጢቢይ حفظه الله


🥦ምላስን መጠበቅ ያሉት ጥቅሞችና ምላስን አለመጠበቅ ያሉት ጉዳቶች ተዳሰዋል ሰምተን እንጠቀም 🥦

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


አትደንግጡ❗️ይህ ደም የኢየሱስ ስቅለት የሚያሳየው ፊልም ላይ የተወሰደ ነው።

ይህ የኢየሱስ ሳይሆን የአንድ የፊልም አክተር እግር ነው።

በዚያ ዘመን ዲጂታል ከለርድ ካሜራ በጭራሽ አልነበረም።

ኢየሱስን አንድም ከለርድ ፎቶ ያነሳው ሰው የለም።

ክርስቲያኖች የሚያለቅሱት በሆነ አክተር ፊልም እያዩ እንጂ ኢየሱስን አይደለም።


አስቡት እስቲ አምላክ በዚህ ልክ ተቸንክሮ ደም በደም ሲሆን?


ሀሰኑ አል በስሪይ رحمه الله

ወደ እናት ፊት መመልከት በራሱ ዒባዳ
ነው ታድያ ለእርሷ መልካም መዋሉስ
እንዴት ሊሆን ነው ይላሉ።

مسند ابن المبارك👉ምንጭ


🤝
    ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን በሙሉ
:
:
:
:
:
:
:
:
.
.
.
.
.
.
🤲አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራችሁ🤲


Репост из: በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك
የቅጥፈቶች ሁሉ ቅጥፈት ጥግ!


የሰው ልጅ አእምሮ የማይቀበለው አባባል

   “ጌታ ለእኛ ሀጥያት ሲል ተሰቀለ¡”

ጌታ የእኛ ሀጥያት ሊምረን ከፈለገ ይምረናል እንጂ ለምን ይሰቀላል⁉️

             منقول








ሱረቱል ካህፍን  የቻለ ይቅራ📖 ያልቻለ ያዳምጥ

በአላህ መልዕክተኛ(ሰዐወ) ላይ ሰለዋት ማውረድ እናብዛ
قَالَ ﷺ: «مَنْ صَلَّ عَلَيَّ صَلاةً صَلَّ اللهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشَراً»

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


ሰባቱ የ‹‹ላ ኢላሀ ኢለላህ›› መስፈርቶች (ሸርጦች)
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ ናበጣም አዛኝ በኾነዉ፦
1.ዕውቀት፡- ይህም ማለት የዚህ ቃል መልዕክት እና ቃሉ ዉድቅ
የሚያደርጋቸዉንና እና የሚያፀድቃቸውን ነገሮች ጠንቅቆ ማወቅ ማለት ነው፡፡
ለዚህም ማስረጃው ቀጣዩ የአላህ ቃል ነው፡፡
ﻭَﻟَﺎ ﻳَﻤْﻠِﻚُ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﺪْﻋُﻮﻥَ ﻣِﻦْ ﺩُﻭﻧِﻪِ ﺍﻟﺸَّﻔَﺎﻋَﺔَ ﺇِﻟَّﺎ ﻣَﻦْ ﺷَﻬِﺪَ ﺑِﺎﻟْﺤَﻖِّ ﻭَﻫُﻢْ ﻳَﻌْﻠَﻤُﻮﻥَ
ﺍﻟﺰﺧﺮﻑ : ٨٦
(እነዚያም ከአላህ ሌላ የሚያመልኳቸዉ እነሱ የሚያውቁ ሆነው በእውነት
ከመሰከሩት በስተቀር ምልጃን አይችሉም) አል-ዙኸሩፍ 86
2.እርግጠኛነት፡- በአላህ ብቸኛ አምላክነት ላይ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ መሆን
ነው፡፡አላህ (ሱ.ወ)እንዲህ ይላል፡-
ﺇِﻧَّﻤَﺎ ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨُﻮﻥَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﺑِﺎﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺭَﺳُﻮﻟِﻪِ ﺛُﻢَّ ﻟَﻢْ ﻳَﺮْﺗَﺎﺑُﻮﺍ ﻭَﺟَﺎﻫَﺪُﻭﺍ ﺑِﺄَﻣْﻮَﺍﻟِﻬِﻢْ ﻭَﺃَﻧْﻔُﺴِﻬِﻢْ
ﻓِﻲ ﺳَﺒِﻴﻞِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺃُﻭﻟَﺌِﻚَ ﻫُﻢُ ﺍﻟﺼَّﺎﺩِﻗُﻮﻥَ
ﺍﻟﺤﺠﺮﺍﺕ: ١٥
({እዉነተኞቹ} ምእመናን እነዚያ በአላህና በመልእክተኛዉ ያመኑት ከዚያም
ያልተጠረጠሩት ናቸው) አል-ሑጁራት 15
የአላህ መልእክተኛም (ሰ.ዐ.ወ) ለአቡ ሑረይራ (ረዲየ አላሁ አንሁ) እንዲህ
ብለውታል፡- ‹‹ ከዚህ አጥር በስተጀርባ የአላህን ብቸኛ አምላክነት ከልቡ
በእርግጠኝነት የሚመሰክር ሰው ብታገኝ በጀነት አበስረው፡፡›› ሙስሊም
ዘግበዉታል
3.መቀበል፡- የላኢላሀ ኢለላህን መልእክት (አላህን በብቸኝነት ማምለክን)
ከልብ መቀበልና ለሌላ አካል የሚከናወኑ አምልኮቶችን መተው ነው፡፡ ይህንን
ያልተቀበለ ግን አላህ ኩራተኛነታቸውን እና አለመቀበላቸው እንዲህ በማለት
ከገለፃቸው ሙሽሪኮች መደዳ ይሰለፋል፡፡
ﺇِﻧَّﻬُﻢْ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ ﺇِﺫَﺍ ﻗِﻴﻞَ ﻟَﻬُﻢْ ﻟَﺎ ﺇِﻟَﻪَ ﺇِﻟَّﺎ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻳَﺴْﺘَﻜْﺒِﺮُﻭﻥَ
ﺍﻟﺼﺎﻓﺎﺕ: ٣٥ – ٣٦
(እነርሱ፤ ‹ከአላህ ሌላ አምልኮት የሚገባው ሆኖ የሚመለክ አምላክ የለም›
በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበር፡፡ እኛ ለእብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው
ነን ይሉም ነበር፡፡) አልሷፋት 35-36
4.መታዘዝ፡- ይህ ማለት ‹‹ላ ኢላሀ ኢለላህ›› የሚለው የምስክርነት ቃል
ለሚያመላክታቸው ትዕዛዛትና ክልከላዎች ሙሉ ታዛዥ ተከታይና ተናናሽ መሆን
ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-
ﻭَﻣَﻦْ ﻳُﺴْﻠِﻢْ ﻭَﺟْﻬَﻪُ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﻫُﻮَ ﻣُﺤْﺴِﻦٌ ﻓَﻘَﺪِ ﺍﺳْﺘَﻤْﺴَﻚَ ﺑِﺎﻟْﻌُﺮْﻭَﺓِ ﺍﻟْﻮُﺛْﻘَﻰ ﻭَﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ
ﻋَﺎﻗِﺒَﺔُ ﺍﻟْﺄُﻣُﻮﺭِ
ﻟﻘﻤﺎﻥ : ٢٢
(እርሱ መልካም ሰሪ ሆኖ ፊቱን (በመታዘዝና በመተናነስ) ወደ አላህ የሚሰጥ
ሰው ጠንካራን ገመድ በእርግጥ ጨበጠ…)
ሉቅማን 22
5. እውነተኝነት፡- የላኢላሀ ኢለላህን የምስክርነት ቃል በሚሰጥበት ጊዜ
እውነተኛ መሆን ማለት ነው፡፡ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ
‹‹ማንኛውም ከልቡ በእውነተኛነት በአላህ ብቸኛ አምላክነትና በሙሐመድ
(ሰ.ዐ.ወ) መልዕክተኝነት የሚመሰክር ሰው አላህ ከእሳት እርም ይለዋል ››
ቡኻሪ ዘግበዉታል
6. መውደድ፡- ይህ ማለት ላኢላሀ ኢለላህ የሚለውን የምስክርነት ቃል ፣ አላህን
እንዲሁም አላህን በብቸኝነት የሚያመልኩትን የተውሂድ ሰዎችን መውደድ ነው፡፡
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል ፡-
( ﻭَﻣِﻦَ ﺍﻟﻨَّﺎﺱِ ﻣَﻦْ ﻳَﺘَّﺨِﺬُ ﻣِﻦْ ﺩُﻭﻥِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺃَﻧْﺪَﺍﺩًﺍ ﻳُﺤِﺒُّﻮﻧَﻬُﻢْ ﻛَﺤُﺐِّ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﺃَﺷَﺪُّ
ﺣُﺒًّﺎ ﻟِﻠَّﻪِ
ﺍﻟﺒﻘﺮﺓ: ١٦٥
(ከሰዎችም አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን
(ጣዖታትን) የሚይዙ አሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ)
ይበልጥ የበረቱ ናቸው) አል በቀራህ 165
7. ማጥራት፡- ይህም ማለት የላኢላሀ ኢለላህን የምስክርነት ቃል የሰጠ ሰው
ስራውን ከሽርክ ማጥራት አለበት፡፡ እንዲሁም በዚህ የምስክርነት ቃል የዱንያ
ጥቅማጥቅሞችን ከመከጀል፣ ከይዩልኝ እና ይስሙልኝ መጥራት አለበት፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል ‹‹የቂያማ ዕለት የኔን ምልጃ
በማግኘት ዕድለኛ የሚሆነው ላ ኢላሀ ኢለላህን ከልቡ ያለ ሰው ነው፡፡›› ቡኻሪ
ዘግበዉታል

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


ከተውሂድና ከሱና የራቀ በሙሉ ወደ ሽርክ ፣ ወደ ቢድዐ እንዲሁም ወደ
# ቅጥፈት የቀረበ ነው።
# ሼኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሂመሁላህ

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


"አስተውሉ! ከመፀፀታችሁ በፊት መልካምን ስራ ፈፅሙ። በዱንያ አትሸወዱ።ምክንያቱም ፦
ጤነኞቿ መታመማቸው ፤ አዲሶቿ ማርጀታቸው፤ ፀጋዎቿ ማለቃቸው ወጣቶቿ ማርጀታቸው አይቀርምና።"
📚【አዙህዱልከቢር ሊልበይሀቂ (1/197)

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

Показано 20 последних публикаций.