አጅጅጅብ ነው ሱብሓነክ ያ ረብ! ለምን እርቅ አልሳካ አለ እያልኩ እጨነቅ ነበር። ለካስ ሚስጥሩ ወዲህ ነው...። ወላሂ በአሏህ ፍቃድ አሁን ገባኝ... "ማን ያርዳ? የቀበረ። ማን ይናገር? የነበረ።" ይሉሃል ይሄ ነው ሚስጥሩ። ይህንን ሸይኽ ሙሳ አልቀጧኒ የሚባሉ እስከመጨረሻ አዳምጧቸውማ እርቁን ለአሏህ ብለው በተከበረችዋ መካ ከተማ ዑለማዎች ጀምረውት ወደ ሀገራችንም ምድር ላይ ለማዋል ቀላል የማይባል መስዋዕትነት ከፍለው ነበርሳ። የሚደንቀው ሁለቱንም(እነሸይኽ ዐብዱልሐሚድንና ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወርን) አክብረውና ለማንም ሳያዳሉ በቅድሚያ እነሻኪር ሱልጣን በተገኙበት በክብር የተጋበዙት እርቁን የሚሸሹትና ናቅ ያደረጉት ቡድኖች ነበሩ። ዑለማዎቹ መቼም ጀዛሁሙሏሁ ዐና ወዐኒልኢስላም ወልሙስሊሚነ ጀሚዓን ኸይራ። እኔ የገረመኝ ቁርአን እርቅ በላጭ ነው እያለ እነ ሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ሐፊዘሁሏህ ከእርቅ መሸሽ ለምን አስፈለጋቸው? ምላሹ ከተግባራቸው እየተገለፀልን ነው። ያ ሐቅን በሐቅነቱ አሳይቶ መከተልን እንድሁም ባጢልን በባጢልነቱ አሳይቶ መራቅን በብቸኝነት ለሚወፍቀው አልሐምዱሊላህ። ብቻ ከትልቅ ሰው ይህ ባይጠበቅም ለኔ መቼም ይህ ለማስታረቅ የተደረገ ሙከራ በውስጤ የሚረብሸኝን ነገር አስወግዶ ጭንቀቴን አቅልሎልኛል። ስለኢብኑመስዑድም መርከዝ ፍትሓዊ ነው ብዬ የማምንበት ንግግር ከሸይኹ አድምጫለሁ። ዐረብኛ መሆኑ ደግሞ ምን ያክል ንግግሩን ተመስጬ እንዳዳምጠው ውብ እንዳደረገልኝ... ቀሪው ከአሏህ ውሳኔ በኋላ ነፍስያውን ጫን ብሎ እርቅን በአርዓያነት ራሱ በተግባር ከማያስተምር ቡድንተኛነትን በአፍና በፅሁፍ ከሚቃወም ነገር ግን በተግባር ራሱ ቡድንተኝነትን ከሚያንፀባርቅ በመጠንቀቅ ድኔን መጠበቅ የራሴ የቤት ስራ ሆኖልኛል። ማነህና አንተ ካላችሁኝ። እኔማ እዛው ገጠር ያለሁት ለጊዜው ግጥምን ወንድሜ ኑረድን አልዐረቢ ይግጠምበት አሏህም ይጠብቀው ብዬ የምመኝለት ደካማውና የአሏህን እዝነት ከጃዩ የአሏህ ባሪያ ነኝ እላችኋለሁ።👇
አቡሐኒፋ ዐብዱልከሪም ገበየሁ (ከገጠር)
እሁድ፣ ግንቦት 18፣ 2016 ዓ.ል.
https://t.me/Abuhanifa_2
አቡሐኒፋ ዐብዱልከሪም ገበየሁ (ከገጠር)
እሁድ፣ ግንቦት 18፣ 2016 ዓ.ል.
https://t.me/Abuhanifa_2