“በፌዴሬሽን ስለመመረጤ የማውቀው ነገር የለም”
የአዲስ አበባ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን በትላንትናው ዕለት በጊዮን ሆቴል ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሄደ ሲሆን፤ ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚመሩትን ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ፕሬዚዳንትና የሥራ አስፈጻሚዎች መርጧል፡፡
ፌዴሬሽኑ ሁለት ታዋቂ ሴት አርቲስቶችን በአመራርነት ማካተቱም ይታወቃል፡፡
በሥራ አስፈጻሚ ውስጥ ከተካተቱት አንዷ ታዋቂዋ አርቲስት ሐረገወይን አሰፋ ስትሆን፤ እርሷ ግን በሥራ አስፈጻሚነት ስለመመረጧ የምታውቀው ነገር እንደሌለ ገልጻለች፡፡
“እስከ እኩለ ለሊት ድረስ የቆየ ቀረፃ ጨርሼ ስልክ ስከፍት፣ በርካታ ወዳጆቼ ተመረጥሽ የሚል ነገር ሰምተን ነው የሚል መልእክት ልከዋል።“ ያለችው አርቲስቷ፤ ”በወዳጆቼ ጥቆማ ወደ ማህበራዊ ሚዲያ ስገባ ተሰራጭቶ ያየሁት መረጃ በፍፁም የማላውቀውና ከሌላው ሰው ዘግይቶ የደረሰኝ ነበር” ብላለች፤ በማህበራዊ ትስስር ገጽዋ ባጋራችው ጽሁፍ፡፡
በግሌ በፕሮሞሽን፣ መድረክ በመምራትና መሰል ጉዳዮች በሙያዬ እንዳግዝ በስልክ ተጠይቄ፣ “ፍቃደኛ ነኝ በሙያዬ አግዛችኋለሁ” የሚል ምላሽ ሰጥቻለሁ ያለችው ሃረገወይን፤ መረጃዎችን ላኪልን ስባልም በፍቃደኝነት ልኬያለሁ ብላለች፡፡
“ከዚህ ውጭ ግዮን ሆቴል ተካሄደ ስለተባለው ስብሰባ የማውቀው ነገር አልነበረም፤ በቦታውም አልነበርኩም፤ጥሪም አልደረሰኝም።” ብላለች፤ አርቲስት ሃረገወይን አሰፋ፡፡