Addis Admass


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


የአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
=====
አዲስ አድማስ https://bit.ly/2V1zyZQ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2V0I6jx
ትዊተር↠ https://bit.ly/33fDhaP
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/2JgeCvG
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3q2hXiv
የእርስዎና የቤተሰብዎ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


"በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በማንኛውም ቅፅበት ጦርነት ሊነሳ ይችላል"


በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል "በማንኛውም ቅፅበት ጦርነት ሊነሳ ይችላል" ሲሉ ጄኔራል ፃድቃን ገብረትንሳይ አስጠነቀቁ።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳም፤ "በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በግልጽ የሚታይ መቃቃር አለ። የእኔ ስጋት ይህ ከቃላት አልፎ ወደ ጦርነት እንዳያድግ ነው" ብለዋል።

ጦርነቱ ለቀጠናውም ዳፋ እንደሚሆንም ጄኔራል ፃድቃን በእንግሊዝኛ ባስነበቡት ጽሑፍ አስታውቀዋል።

በሁለቱ አገራት መካከል የሚደረግ ጦርነት በሁለቱም ወገኖች እንደሚባለው "አጭርና ወሳኝ" እንደማይሆን የገለጹት ጄኔራል ፃድቃን፤ ለቀጠናው አውዳሚ እንደሚሆን ጠቅሰዋል።

"ጦርነቱ ሲያከትም አሁን የምናውቀው የአገራቱ ጂኦግራፊ ይለወጣል። በአፍሪካ ቀንድና ከቀይ ባሕር አሻግሮም ጉልህ የፖለቲካ አሰላለፍ ለውጥ ያስከትላል" ብለዋል።

በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ ያልተማከለ አስተዳደርና ዴሞክራታይዜሽን ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ፣ ሌተናንት ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳይ፣ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የሚቀሰቀሰው ጦርነት "የሱዳንና የቀይ ባሕር ደኅንነት ላይ በቀጥታ ተጽዕኖ ያሳድራል" ብለዋል።

"በጦርነቱ ማዕከላዊ የምትሆነው በደንብ የሠለጠነና ልምድ ያካበተ ከፍተኛ የወታደር ቁጥር ያላት ትግራይ ናት" ሲሉም አክለዋል፡፡ (ቢቢሲ እንደዘገበው።)




የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዛሬ የሰጠው መግለጫ

" ... አንዳንድ የኦርቶዶክስ ክርስትና አማኝ ነን የሚሉ ግለሰቦች፣ የእስልምና ሃይማኖት ነቢይ በሆኑት በነቢዩ መሐመድ (የአላህ እዝነትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁንና) ላይ ድፍረት የተሞላበት ክብረ ነክና ጸያፍ ንግግር ሲያደርጉ ታይተዋል፡፡ ይህም ሙስሊሙን ወገን ብቻ ሳይሆን ሰላም ወዳዱን ወገን ሁሉ አሳዝኗል፡፡

ጉባኤችንም ይህ ዓይነቱ ኢ-ሥነምግባራዊና ሕገ ወጥ ተግባር የትኛውንም የሃይማኖት ተቋም የማይወክል፣ ይልቁንም የሚወገዝ ተግባር መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም አንዳንድ የኦርቶዶክስ አማኝ ነን የሚሉ ወንድሞችና እህቶች፤ የግለሰቡን ሕገ-ወጥ ተግባር ተቋማዊ ለማድረግ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያጤኑና ግለሰብንና ተቋምን እንዲለዩ እንመክራለን፡፡

በአንፃሩ አንዳንድ ሙስሊም ነን የሚሉ ግለሰቦች፣ ተደፈርን በሚል ስሜት የክርስትና አስተምህሮንና የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር የሚነቅፍና የሚያጠለሽ፣ መላውን ክርስቲያን በሚያዋርድ መልኩ ምላሽ ሲሰጡና ድርጊቱን በፈፀመው ግለሰብ ላይ የደቦ ፍርድ ሲያስተላልፉ ይታያሉ፡፡

ይህም ሕገ-ወጥነትን ከማስፋፋት ባለፈ ጥፋትን በሌላ ጥፋት ማረም ፈጽሞ የማይቻል መሆኑን ተገንዝበው፣ ከድርጊታቸው በመታረም፣ የሕግ የበላይነትን እንዲያስቀድሙ ጉባኤያችን በአጽንኦት ይመክራል፡፡

በየትኛውም አካል የተፈፀሙትና የሚፈፀሙት ይህን መሠል ሕገ-ወጥ ተግባራት በሁሉም ሃይማኖቶች አስተምህሮ ተቀባይነት የሌላቸው ብቻ ሳይሆን፣ የሚወገዙ ተግባራት መሆናቸውን ጉባኤያችን እያስገነዘበ፣ ድርጊቱ በወንጀል የሚስጠይቅ ስለመሆኑም ለማስታወስ ይወዳል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝኃ ሀይማኖት መገኛና መኖሪያ ከመሆኗ አንፃር የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የትኛውንም ዓይነት የሃይማኖት ተቋማትን፣ አስተምህሯቸውንና መገለጫዎቻቸውን የሚያንቋሽሹና የሚያዋርዱ ንግግሮችንም ሆነ ተግባራትን በጽኑ ያወግዛል። "⬇️⬇️


የፊልሙ ቀረጻ እዚሁ አዲስ አበባ የተከናወነ ሲሆን፤ ከ65 በመቶ በላይ በሪፌንቲ ሞል ህንጻ ላይ መቀረጹ ተነግሯል፡፡

እንግዱ የተባለው ገጸባህርይ 7 ዓይነት ማንነቶችን ወይም ሰብዕናዎችን የያዘ መሆኑ ፊልሙን ለየት ያደርገዋል ያለው ደራሲና ዳይሬክተሩ ሳዳም ነጌሶ፤ የዚህን መነሻ ሃሳብ የወሰደው እ.ኤ.አ በ2016 ዓ.ም ከተሰራው Split የተሰኘ የሆሊውድ አስፈሪ ትሪለር ፊልም መሆኑን ጠቁሟል፡፡

በፊልሙ ላይ እንግዱን ሆኖ የተወነው ጌዲዮን ፍቃዱ በሰጠው አስተያየት፤ "ስክሪፕቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ሳነበው ልሰራው የማልችለው ነበር የመሰለኝ፡፡ በአንደ ሰው ላይ ሰባትና ከዚያ በላይ ማንነቶችን ማሳየት ፈታኝ ነበር፡፡ እንደምንም ግን ተወጥቼዋለሁ" ብሏል፡፡

"እንግዱ" ፊልም በትላንትናው ዕለት በዓለም ሲኒማ ለአርቲስቶችና ለፊልሙ ቤተሰቦች ለዕይታ የበቃ ሲሆን፤ መጋቢት 5, 6 እና 7 እንዲሁም መጋቢት 12, 13 እና 14 ቀን 2017 ዓ.ም በሁሉም ሲኒማ ቤቶች በይፋ እንደሚመረቅ ታውቋል፡፡


"እንግዱ" የተሰኘ ልብ አንጠልጣይ ትሪለር ፊልም ሊመረቅ ነው

• 2.5 ሚሊዮን ብር ፈጅቷል ተብሏል

በአጠቃላይ 2.5 ሚሊዮን ብር እንደፈጀ የተነገረለት "እንግዱ" የተሰኘ ልብ አንጠልጣይ ትሪለር ይዘት ያለው አዲስ ፊልም፣ ከመጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚመረቅ ተገለጸ፡፡

በሳዳም ነጌሶ ተደርሶ ዳይሬክት የተደረገው ፊልሙ፤ በልባም ፒክቸርስ ተዘጋጅቶ በሳዳም ፊልም ፕሮዳክሽንና በሶሎዳ ስቱዲዮ መቅረቡ የተነገረ ሲሆን፤ የ1 ሰዓት ከ32 ደቂቃ እርዝማኔ ያለው ነው ተብሏል፡፡

ዛሬ ጠዋት ረፋዱ ላይ በፊልሙ ዙሪያ ፕሮዲዩሰሮቹና ተዋናዮቹ በሪፌንቲ ሞል (ቦሌ ቡልቡላ) ለሚዲያ ባለሙያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ በጋራ ሰጥተዋል፡፡

"እንግዱ" የተሰኘውን ፊልም ሰርቶ ለማጠናቀቅ ከ8 ወር በላይ እንደፈጀ የተገለጸ ሲሆን፤ በፊልሙ ላይ ከ35 በላይ ታዋቂና አጃቢ ተዋናዮች እንደተሳተፉበት ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከፊልሙ መሪ ተዋናዮች መካከል፡- አንጋፋው ተዋናይ ሰለሞን ሙሄ፣ ኤደን ገነት፣ ታዋቂው ኮሜዲያን ደረጄ ሀይሌ፣ ጌዲዮን ፍቃዱና አሰፋ ገ/ሚካኤል ይገኙበታል፡፡

⬇️⬇️


ታዋቂው ሙዚቀኛ አቶ አለማየሁ ፋንታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡


ዩክሬን በሞስኮ ላይ መጠነ ሰፊ የድሮን ጥቃት ማድረሷን ሩሲያ አስታወቀች


አሜሪካ እና ዩክሬን በሳዑዲ ዓረቢያ የሚያደርጉት የሰላም ንግግር በሚጠበቅበት ሰዓትምሽቱን ዩክሬን የድሮን ጥቃት በሞስኮ ላይ መፈፀሟን ሩሲያ ገልፃለች፡፡

ዩክሬን ወደ ሞስኮ ከሰነዘረቻቸው ድሮኖች መካከል 73 ድሮኖችን ሩሲያ መታ መጣሏን የሞስኮው ከንቲባ ሰርጌይ ሶቢያኒን ገልፀዋል፡፡

የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር ተከትሎም አራት በሞስኮ ከተማ የሚገኙ አየር መንገዶች በረራዎችን ሰርዘዋል፡፡

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ማምሻውን ዩክሬን የከፈተችው ጥቃት ከእስካሁኑ የከፋ ሲሆን በጥቃቱ የሁለት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡






ሻል ሲል በታተመበት ቀን 4 ኪሎ ጆሊ ባር ለተወሰነ ደቂቃ ተከራይቼ ማንበብ ጀመርኩ። አከራዬ ሰውዬ ቦቸራ ይባል ነበር፣ ባለውለታዬ ነው፤ አንዳንዴ ሌላ ጊዜ ትከፍላለህ ይለኝና ያልፈኝ ነበር።

በጣም ሻል ሲል አዲስ አድማስን እየገዛሁ ማንበብ ጀመርኩ። አዲስ አድማስን ማንበብ ሌሎች የህይወት ድርጊቶቼን ደማቅ አድርጎልኛል።

ለምሳሌ፡- አንድ ቦታ፣ ቤት ወይም ከቤት ውጪ ለረጅም ሰዓት መቆየት አሰልቺ ነው። የሳምንቱን አዲስ አድማስ ይዤ በነበርኩበት ሁሉ ግን አስደሳች ጊዜ አሳልፍ ነበር።

የሳምንቱን መረጃ ይዤ ከሰዎች ጋር አፌን ሞልቼም እከራከር ነበር። ማሳረጊያ ማጣቀሻዬ "አዲስ አድማስ ላይ ተፅፏል" የሚል ነበር። አዲስ አድማስ፤ መፎከሪያችን ነበረች።

በጣም በጣም ሻል ሲል፣ የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ሰብሳቢ (Collector) ለመሆንም ታድዬ ነበር።

በኋላም ፅሁፍ መላክ ጀምሬ ተለማማጅ ዓምደኛ ለመሆንም ችዬአለሁ። እስከ 2000 ዓ.ም. ድረስ 3 ፅሁፎቼ በአዲስ አድማስ ታትመዋል። የበለጠ ፍቅር ያሳድራል።

ዛሬ ጊዜው ተቀይሮ ስልካችን ውስጥ ብንደበቅም፣ አዲስ አድማስ ጋዜጣ የሁልጊዜ የልብ ወዳጃችን ናት።
እናመሰግናለን። መልካም 25ኛ ዓመት!

ብርሃኑ /Abt/


አዲስ አድማስ የዛሬ 25 ዓመት ስትጀመር---

አዲስ አድማስ የዛሬ 25 ዓመት ስትጀመር፣ እኔና እኩዮቼ ለዓቅመ ጋዜጣ ልንደርስ አካባቢ ነበር፡፡ እናም በሠርቶ አደር ጋዜጣ በተለጠፈ ግርግዳ የንባብ ክህሎትን ያዳበርን እኛ፣ እንዲሁም ቅዳሜን ከእኛ ጋር፣ እሁድን ላንድ አፍታ፣ ለወጣቶችና፡ የመሳሰሉትን የለገዳዲና የኢትዮጵያ ሬድዮ ፕሮግራሞች እየሰማን ላደግን እኛ፣ ከግል ጋዜጣና ሬድዮ ጋር በጥሩ የወጣትነት ዘመናችን ላይ ተገናኝተናል፤ 1990ዎቹ መጀመርያና አጋማሽ አካባቢ።

አዲስ አድማስ ጋዜጣ፣ ኤፍ ኤም 97.1፣ በኋላም ሸገር ሬድዮ በተሻለ የመዝናኛና የዕውቀት ይዘት ወጣትነታችንን ያደመቁ የዘመን ቅርሶች ናቸው።

በግሌ አዲስ አድማስን ማንበብ የጀመርኩት 1996 ዓ.ም. ላይ ነው። ችስታ ስለነበርኩ ከታተመ ሳምንት ወይም ከዚያ በላይ ያለፈው፣ ሌሎች ሰዎች ገዝተው አንብበው ሲጨርሱ በተውሶ አንብቤ በክብር እመልሳለሁ።

⬇️⬇️


በሁለቱ ወገኖች መካከል የተፈጠረው ልዩነት በእርቅ መፈታቱን ያደነቁ የተለያዩ ማህበራት ተወካዮች፤ ሌሎችም በክስ ሂደት ላይ ያሉ ማህበራት ችግራቸውን በእርቅ የሚፈቱበት ሁኔታ ይመቻች ዘንድ ሃሳብ ሰንዝረዋል፡፡

ከኦክሎክ ሞተርስ ጋር የእርቅ ስምምነት ላይ መድረሳቸው የተገለጸው ከ60 ማህበራት ውስጥ 16 ያህሉ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከ20 ዓመት በፊት የተመሰረተውና በተለያዩ ዘርፎች ላይ የተሰማራው ኦክሎክ ሞተርስ፤ በትግራይ መቀሌ ከተማና በአዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ ባስገነባቸው የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካዎቹ ከ16 በላይ የተለያዩ ሞዴል ተገጣጣሚ ተሽከርካሪዎችን ከውጭ በማስመጣት እየገጣጠመ ለደንበኞቹ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡


በእርቅ ስምምነት ላይ የደረሱት የማህበራት ተወካዮች በሰጡት አስተያየት፤ "ወደ ህግ መሄድ ጊዜ የሚፈጅና አላስፈላጊ ወጪ የሚያስከትል በመሆኑ ችግራችንን በእርቅ ለመፍታት ተስማምተናል" ብለዋል፡፡

በኦክሎክና ማህበራቱ መካከል እርቅ ለማድረግ ተነሳሽነቱን የወሰዱት የሽማግሌዎቹ ተወካይ እንደገለጹት፤ መጀመሪያ ላይ ከሁለቱም ወገኖች ተቀባይነት አላገኙም ነበር፡፡ "በተለይ ማህበራቱ ከኦክሎክ የተላክን መስሏቸው ዕርቁን አሻፈረን ብለው ነበር፤ ዓላማችን በሁለቱ መካከል ሰላምና እርቅ መፍጠር መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ ነው የተስማሙት" ብለዋል፤ በሰጡት መግለጫ፡፡

የኦክሎክ ሞተርስ ሥራ አስኪያጅ አቶ ታመነ ካሣሁን በበኩላቸው፣ መጀመሪያ ላይ በማህበራቱ በኩል ስለድርጅቱ የተሳሳተ መረጃ ይሰራጭ እንደነበር አንስተዋል፡፡ ለአብነት ያህልም፡- ኦክሎክ ከማህበራቱ አባላት 1.2 ቢሊዮን ብር ሰብስቦ አንድም መኪና አላስመጣም የሚለው ነው ብለዋል፡፡ ሌላው ደግሞ በራሱ በድርጅቱ የተመዘገበ የመኪና መገጣጠሚያ ፈቃድ የለውም የሚል እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

"እውነቱ ግን ኦክሎክ ሞተርስ በመቀሌና በአዲስ አበባ በስሙ የተመዘገበ የመኪና መገጣጠሚያ ያለው ሲሆን፤ ከመኪና ፈላጊዎች የማህበራት አባላት የተሰበሰበው ገንዘብ 1.2 ቢሊዮን ብር ሳይሆን 41 ሚሊየን ብር ነው፡፡" ብለዋል፤ ሥራ አስኪያጁ፡፡

ኦክሎክ ከአባላቱ ገንዘብ ሰብስቦ ምንም መኪና አላመጣም የሚለውም ትክክል አይደለም ያሉት አቶ ታመነ ካሣሁን፤ የማህበሩ አባላት እስካሁን 800 ተሽከርካሪዎችን በካሽና በብድር ወስደዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የሽማግሌዎቹ ቡድንም እኒህን የተሳሳቱ መረጃዎች በራሳቸው መንገድ አጣርተው፣ እውነታው ላይ መድረሳቸውን በራሳቸው አንደበት ያረጋገጡ ሲሆን፤ እርቅ ላይ የተደረሰውም ከዚህ ሁሉ ሂደት በኋላ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡


ኦክሎክ ሞተርስና ማህበራቱ ችግራቸውን በእርቅ መፍታታቸውን አስታወቁ

ኦክሎክ ሞተርስና አንዳንድ ማህበራት በመካከላቸው ተፈጥሮ የነበረውን አለመግባባት በእርቅ መፍታታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ይሄ ይፋ የተደረገው ዛሬ ጠዋት ረፋድ ላይ የኦክሎክ ሞተርስ ሥራ አስኪያጅ፣ እንዲሁም የሽማግሌና የማህበራቱ ተወካዮች በተገኙበት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡

ኦክሎክ ሞተርስ ባሰራጨው መግለጫ እንዳመለከተው፤ ከጥቂት ወራት በፊት በተሳሳተ መረጃና ጉዳዩን በጥልቀት ካለመረዳት የተነሳ ከድርጅታችን ጋር የሽያጭ ውል በመግባት ተሽከርካሪዎችን ለመግዛት ተስማምተን በጋራ እየሰራን ካሉ በርካታ ማህበራት ውስጥ በተወሰኑ ማህበራትና ግለሰቦች አማካኝነት በድርጅቱ ላይ የስም ማጥፋት ተግባር ተፈፅሞ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ማህበራቱና አባላቱ ጉዳዩን በጥልቀት ከመረመሩና በጊዜው የተነገራቸውን መረጃዎች መለስ ብለው በማጣራትና ከድርጅታችን ጋር በመነጋገር፣ በሀገራችን ባህል ወግ መሰረት፣ ችግሩን በእርቅ ፈተን በመስማማት ወደ ትግበራ ስራ ገብተናል ብሏል፤ ድርጅቱ በመግለጫው።

ኦክሎክ ሞተርስና ማህበራቱን በሽምግልና ለማስታረቅ እልህ አስጨራሽ ጥረት መደረጉ የተገለጸ ሲሆን፤ የማታ ማታ ስምምነት ላይ መደረሱ ይፋ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሰረት ገንዘብ የሚፈልጉ ገንዘብ፣ መኪና የሚፈልጉ ገንዘብ እንዲወስዱ የተስማሙ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት 20 ያህል አባላት መኪና እንደሚረከቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ገንዘብ የሚፈልጉ ደግሞ በ45 ቀናት ውስጥ ገንዘባቸውን እንደሚወስዱ ተነግሯል፡፡


አዲሱ የካናዳ ጠ/ሚኒስትር የትራምፕን ታሪፍ እንደሚፋለሙ ቃል ገቡ

የካናዳ ገዥው ሊበራል ፓርቲ መሪ ለመሆን በተደረገው ውድድር የቀድሞው የማዕከላዊ ባንክ ሃላፊ ማርክ ካርኒ ማሸነፋቸውን ትላንት እሁድ የወጡ ይፋዊ ውጤቶች አረጋግጠዋል፡፡

ካናዳ ከአሜሪካ ጋር የንግድ ጦርነት ውስጥ በገባችበት በዚህ ወቅት ወደ ስልጣን የመጡት ማርክ ካርኒ፤ በቅርቡ አጠቃላይ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ የአገሪቱ መሪ ሆነው ይቆያሉ ተብሏል፡፡

ለ9 ዓመታት ካናዳን የመሩት ጄስቲን ትሩዶ፣ በህዝባቸው ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን ተከትሎ፣ የስራ መልቀቂያ ካስገቡ በኋላ፣ ፓርቲያቸው እሳቸውን ለመተካት ምርጫ አካሂዷል፡፡

የ59 አመቱ ማርክ ካርኒ በምርጫ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር፤ “ኢኮኖሚያችንን ለማዳከም የሚሞክር አንድ ሰው አለ፤ የካናዳ ሰራተኞችን፣ ቤተሰቦችንና የንግድ ድርጅቶችን እያጠቃ ነው፣ እንዲሳካለት ልንፈቅድለት አይገባም" ሲሉ ዶናልድ ትራምፕን ነቅፈዋል፡፡

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ትራምፕ እያደረሱ የሚገኙትን ተጽዕኖ ለመቋቋም ከተለመደው የተለየ አካሄድን መከተል እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

ትራምፕ በካናዳ ላይ ለጣሉት የ25 በመቶ ታሪፍ፣ የጀስቲን ትሩዶ አስተዳደር 30 ቢሊዮን የካናዳ ዶላር ዋጋ ባላቸው የአሜሪካ ምርቶች ላይ የታሪፍ ጭማሪ በማድረግ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

የኢኮኖሚ ልምድ እንዳላቸው የሚነገርላቸው አዲሱ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ከትራምፕ ጋር በእኩል ቋንቋ ለመነጋገር ትክክለኛው ሰው ናቸው ተብለዋል፡፡


"የአማጽያኑን አመራሮች በማሰር ለሚያግዘኝ 5 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት እሰጣለሁ"

-የኮንጎ መንግሥት-

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት በአብዛኛው የአገሪቱን ምስራቃዊ ክፍል የተቆጣጠሩት አማጽያን ሦስት አመራሮች በቁጥጥር ስር ለማዋል እገዛ ለሚያደርግ አካል የ5 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት እሰጣለሁ ብሏል፡፡

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የምርጫ ኮሚሽን ኃላፊ የነበሩት ኮርኔይ ናንጋ የኤም23 አማጺ ቡድንን ጨምሮ ሌሎች ታጣቂዎችን አጣምሮ የያዘውን የኮንጎ ሪቨር አሊያንስ ይመራሉ።

መሪው በቁጥጥራቸው ስር ካሉ ከተሞች በአንዷ በነበረ ከፍተኛ የድጋፍ ስብሰባ ላይ ከሰሞኑ ንግግር አድርገዋል።

ከኮርኔይ በተጨማሪ ይህ ሽልማት የሚሰጠው የኤም23 መሪ የሆኑትን ሱልጣን ማኬንጋ እና በርትራንድ ቢስምዋን በቁጥጥር ስር ለማዋል በሚደረገው እገዛ ነው።

ባለፈው ዓመት ሶስቱ አመራሮች በሌሉበት በወታደራዊ ፍርድ ቤት ተከሰው የሞት ፍርድ ተበይኖባቸዋል። በተጨማሪም በግዞት ላሉ ሁለት ጋዜጠኞችና ሌሎች የአማጽያኑ ተባባሪ ተብለው የተፈረጁ ጋዜጠኞችን ለእስር በመዳረግ ለሚያግዙ ተጨማሪ 4 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ቀርቧል።

⬇️⬇️


ነገር ግን በዚህ መንገድ የትኛውም አመራር የመታሰር እድሉ ኢምንት ይመስላል። ባለፉት ሳምንታት በሩዋንዳ የሚደገፉት አማጺያን በማዕድን የበለጸገችውን ምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊን ኮንጎ ግዛትን ጨምሮ የክልሉን ሁለት ታላላቅ ከተሞች፣ ጎማ እና ቡካቩን የአገሪቱን ጦር በማሸነፍ መቆጣጠር ችለዋል።

በዚህም የተነሳ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኪዲ ሩዋንዳ ለአማጽያኑ በምትሰጠው ድጋፍ ምክንያት ማዕቀብ እንዲጣልባት ዓለም አቀፍ ጫና ለመፍጠር እየሞከሩ ይገኛሉ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሙያዎች ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት ባወጣው ሪፖርት፤ እስከ 4 ሺህ የሚደርሱ የሩዋንዳ ወታደሮች ከኤም23 ጋር ተሰልፈው በዲሞክራቲክ ኮንጎ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተቀሰቀሰው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ቀያቸውን ጥለው ሸሽተዋል።

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሞባይል ስልኮች እና ኮምፒውተሮች እንደ ግብዓቶች የሚጠቀሙባቸውን ወርቅ እና ኮልታን ጨምሮ የአገሪቱን ማዕድናት ለመቆጣጠር ሩዋንዳ እየሞከረች ነው ስትል ትከሳለች።

ኮንጎ አማጽያኑን ለመዋጋት ከአሜሪካ ወታደራዊ ድጋፍ ለማግኘት ስትል በምላሹ ማዕድኗን ለመስጠት ማቅረቧን አስመልክቶ የፕሬዚዳንቱ ቃል አቀባይ ቲና ሳልማ ምላሽ ሰጥተዋል።

"የአሜሪካ ኩባንያዎች መሰረታዊ የሚባሉ ጥሬ ማዕድናትን ከሩዋንዳ ይገዛሉ። እነዚህ ማዕድናት ከኮንጎ ተዘርፈው ወደ ሩዋንዳ በህገወጥ መንገድ የተዘዋወሩ ናቸው። እናም ፕሬዚዳንቱ ከዋናው ምንጩ (ባለቤቱ) ኮንጎ እንዲገዙ ነው ሃሳብ ያቀረቡት" ብለዋል።

ሩዋንዳ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ማዕድናትን እየዘረፈች ነው መባሏን አስተባብላለች። ሩዋንዳ አማጽያኑን ኤም23 መደገፏን የማትክድ ሲሆን፤ ነገር ግን ግጭቱ ወደ አገሬ እንዳይዛመት ለማድረግ እየተከላከልኩ ነው የሚል ምክንያትን ትሰጣለች።

በተጨማሪም ሩዋንዳ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መቀመጫቸውን ያደረጉ በአውሮፓውያኑ 1994 ከተፈጸመባት የዘር ጭፍጨፋ ጋር ግንኙነት ያላቸው ቡድኖችን መንግሥቱ ይደግፋል ስትል ትተቻለች፡፡
(ቢቢሲ)


ለከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ለቀጣይ ሦስት ዓመታት በየዓመቱ 15 ቢሊየን ብር መመደቡን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ገልጸዋል።

የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት የተጠቃሚዎች ሽግግር እና የማስጀመር መርሐ-ግብር በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት÷ በከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና የሥራ ፕሮጀክት ከ1 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።

መንግሥት ተግባራዊ ያደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መሰረት በማድረግ በገጠር እና በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ሥራዎች ዜጎችን ለመደጎምና በዘላቂነት ኑሯቸውን ለማሻሻል ለቀጣይ ሦስት ዓመታት በየዓመቱ 60 ቢሊየን ብር መመደቡንም አመልክተዋል።

ከዚህም ውስጥ በየዓመቱ 15 ቢሊየን ብር ለከተማ ሴፍቲኔት አንደተመደበ ጠቁመዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ በሁሉም ክልሎች እና በነባር የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ከተሞች ውስጥ 143 ሺህ 26 የቤተሰብ አባላት ወደ ዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ የሚሸጋገሩበት እና 699 ሺህ 112 ዜጎች በቀጥታ ድጋፍና በአካባቢ ልማት ወደ ፕሮጀክቱ እንደሚቀላቀሉ ገልጸዋል።


ለኮሪደር ልማት አገልግሎት ላይ የዋሉ መብራቶችን የሰረቀው ተከሳሽ እጅ ከፈንጅ ተይዞ በ5 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱን የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ፡፡
***
ወንጀሉ የተፈጸመው የካቲት 18 ቀን 2017 ዓ/ም ከሌሊቱ 8:00 ሠዓት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አዋሬ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

ተከሳሽ ሄኖክ መኮንን የተባለው በተጠቀሰው ቀንና ሠዓት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኤኒሼቲቭ በተሠራው የኮሪደር ልማት ላይ የተገጠሙ መብራቶችን ቆርጦና ነቅሎ በመውሰድ ሊያመልጥ ሲል በወቅቱ ስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር መዋሉን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል።

ተከሳሽ ላይም ተገቢው የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች በማደራጀት ምርመራ ተጣርቶበት በአቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል፤

የተከሳሽን መዝገብ የተከታተለው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት የካቲት 26 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ሄኖክ መኮንን ጥፋተኛ መሆኑን በማስረጃ በማረጋገጥ ተከሳሽን ያርማል ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ያስተምራል በማለት በ5 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል።



Показано 20 последних публикаций.